Skip to main content
x

የእሳት ቃጠሎ በሰሜን ማዘጋጃ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና በቀለመወርቅ ትምህርት ቤት በስተጀርባ (ሰሜን ማዘጋጃ) የሚገኘው፣ በተለምዶ ዶሮ ተራ ተብሎ በሚታወቀው ሥፍራ ሰኞ የካቲት 12 ቀን 2010 ዓ.ም በደረሰ የእሳት ቃጠሎ የንግድ መደብሮች ወደሙ፡፡

የመሬት ሊዝ ጨረታ ሳይወጣ ስድስት ወራት ተቆጠሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየወሩ መሬት በሊዝ ለማስተላለፍ ጨረታ እንደሚያወጣ የደነገገ ቢሆንም፣ ላለፉት ስድስት ወራት አንድም የመሬት ሊዝ ጨረታ አልወጣም፡፡ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ሥር የሚገኘው የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ለመጨረሻ ጊዜ የመሬት ሊዝ ጨረታ ያወጣው፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር፡፡

የኦሮሚያ ክልል አምስት በካይ ፋብሪካዎችን ዘጋ

ከአዲስ አበባ ዙሪያ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ አምስት በካይ ፋብሪካዎች መዝጋቱን የኦሮሚያ ክልል የአካባቢ ጥበቃ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን በበኩሉ ከተማውንና ዙሪያውን የሚገኙ የኦሮሚያ አካባቢዎችን የሚበክሉ ፋብሪካዎችን ቢያግድም፣ ዕግዱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ ተነስቶ፣ ተጨማሪ የዕፎይታ ጊዜ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

ግንባታ ባላጠናቀቁ አልሚዎች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የውሳኔ ሐሳብ ቀረበ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ከሚያዝያ 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ለመጨረሻ ጊዜ ለአንድ ዓመት የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ ከተራዘመላቸው ፕሮጀክቶች መካከል፣ አሁንም ሊጠናቀቁ ያልቻሉ በርካታ ፕሮጀክቶች በመኖራቸው ዕርምጃ መውሰድ የሚያስችል የውሳኔ ሐሳብ አቀረበ፡፡ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽሕፈት ቤት ጥር 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ለመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ባቀረበው የውሳኔ ሐሳብ፣ በከተማው ውስጥ በሊዝ ቦታ ወስደው ከሚያዝያ 2008 ዓ.ም. በኋላ የሊዝ ውል ማሻሻያ የተደረገላቸውና ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ዓመት የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ የተራዘመላቸው አሁንም ግንባታ ያላጠናቀቁ አልሚዎች በሁሉም ክፍላተ ከተሞች ተንሰራፍተው ይገኛሉ፡፡

ከውል ውጪ ግንባታ ያካሄዱ አዲስ የይቅርታ ቅጽ እንዲሞሉ የሚያስገድድ አሠራር ይፋ ሆነ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ከገቡት ውል ውጪ ግንባታ ያካሄዱ ባለሀብቶች፣ አማካሪ ድርጅቶችና ኮንትራክተሮች ይቅርታ እንዲጠይቁ ያዘጋጀው አዲስ ቅጽ እያነጋገረ ነው፡፡ ባለሀብቶቹ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከውል ውጭ ላካሄዱት ግንባታ ዕውቅና ለማግኘት ወደ ባለሥልጣኑ በሄዱበት ወቅት እንዲሞሉ በተሰጣቸው አዲስ የይቅርታ ፎርም ግራ መጋባት እንደፈጠረባቸው፣ ወደፊት ሊያመጣባቸው የሚችለውን ችግር ከወዲሁ በመሥጋት ፎርሙን በመሙላትና ባለመሙላት መካከል እየዋለሉ እንደሚገኙ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የፍርድ ቤት ዕግድ የጣሱ የሥራ ኃላፊዎች ወንጀል መፈጸማቸውን ፍርድ ቤት አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦስት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ፍርድ ቤት የሰጠውን የዕግድ ትዕዛዝ በመተላለፍ የግል ይዞታን ‹‹የመንግሥት ይዞታ ነው›› በማለት የባለይዞታዎችን ቤት በማፍረሳቸው ‹‹ወንጀል ፈጽመዋል›› ሲል፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 13ኛ ይግባኝ ሰሚ ፍትሐ ብሔር ችሎት ውሳኔ  ሰጠ፡፡

በዓለም ባንክ ድጋፍ 200 ሺሕ አቅመ ደካሞች በምግብ ዋስትና ፕሮግራም ሊታቀፉ ነው

የዓለም ባንክ ከመደበው 450 ሚሊዮን ዶላር በጀት 70 በመቶ ድርሻ የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በተያዘው በጀት ዓመት ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ 200 ሺሕ ነዋሪዎችን በምግብ ዋስትና ፕሮግራም እንደሚያቅፍ አስታወቀ፡፡ አስተዳደሩ ከተያዘው በጀት 32 ሺሕ ለሚጠጉ ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ አቅመ ደካሞች ቀጥታ ወርኃዊ ክፍያ ለመፈጸም፣ 168 ሺሕ የሚሆኑ ነዋሪዎች ደግሞ በማኅበረሰብ አቀፍ ፕሮግራም ታቅፈው የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተው ወርኃዊ ክፍያ እንዲያገኙ ዕቅድ አውጥቷል፡፡

ከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር እስከ ሰኔ መጨረሻ 32 ሺሕ የጋራ ቤቶች ይጠናቀቃሉ አለ

በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ በተለያዩ ችግሮች እየተንጓተተ ቢሆንም፣ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ 32 ሺሕ ቤቶች እንደሚጠናቀቁ ተመለከተ፡፡ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) የሚመራ ቡድን ሐሙስ ጥር 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በተለያዩ ሳይቶች ጉብኝት አድርጓል፡፡ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ከሚገነቧቸው 94,070 ቤቶች ውስጥ በመጋቢት 2010 ዓ.ም. 22 ሺሕ ቤቶችን፣ ሰኔ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ደግሞ 50 ሺሕ ቤቶችን የማጠናቀቅ ዕቅድ ነበረው፡፡

ከመሀል አዲስ አበባ በልማት ምክንያት የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን በድጋሚ ለማቋቋም ጥናት ተካሄደ

በልማት ምክንያት በቂ ካሳና ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ከመሀል አዲስ አበባ የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን በድጋሚ ለማቋቋም ጥናት መካሄዱ ተገለጸ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከመሀል ከተማ የተነሱትን ከማቋቋም አኳያ ራሱን የቻለ ጥናት መካሄዱን አመልክቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛው፣ በመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ አማካይነት የመሀል ከተማ የልማት ተነሺዎችን ማቋቋም የሚያስችል ጥናት መካሄዱን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ቢሮ በስድስት ወራት ብቻ በ1,439 ጉዳዮች ላይ የሕግ ጥሰት ተፈጽሟል አለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ባላቸው አገልግሎቶች ላይ ባካሄደው ኦዲት፣ 1,439 ጉዳዮች የአሠራርና የመመርያ ጥሰት ያለባቸው መሆኑን ማረጋገጡን አስታወቀ፡፡ የከተማው መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ያካሄዳቸውን ሥራዎች በገመገመበት ሪፖርት ላይ እንዳስታወቀው፣ በ2010 በጀት ዓመት በመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት 4,736 አገልግሎት አሰጣጦችን ኦዲት አድርጓል፡፡