Skip to main content
x

የዓለም ባንክ የ13 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው ፕሮጀክቶች አማካይነት ድጋፍ እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

የዓለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ያደረገውን የኢትዮጵያ የአጋርነት ማዕቀፍ የድጋፍ ሰነድን በማስመልከት ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የ13 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው ፕሮጀክቶች አማካይነት ለአገሪቱ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡

ላቀረቡት ምርት ክፍያ ያጡ አገር በቀል ኩባንያዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቀረቡ

ለቱርክ ኩባንያ ኤልሲ አዲስ ኢንዱስትሪያል ዴቨሎፕመንት ጥጥ በብድር ሲያቀርቡ የቆዩ 12 አገር በቀል ኩባንያዎች ክፍያ ስላልተፈጸመላቸው ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን በመግለጽ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ዕቅድ ውጤታማነት ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ኃላፊ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) መፍትሔ እንዲሰጧቸው ጠየቁ፡፡

የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ተቃጠለ

የጋምቤላ ከተማ መምህራን ሥራ አቁመው ነበር የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት፣ ቅዳሜ ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ለእሑድ አጥቢያ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በተነሳ ቃጠሎ ወደመ፡፡ የክልሉ ፖሊስ የጠረጠራቸውን አሥር ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተገልጿል፡፡ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አከነ ኦፓዳ ለሪፖርተር እንደገለጹት በቃጠሎው ኮምፒዩተሮች፣ ሰነዶችና የቢሮ ዕቃዎች ወድመዋል፡፡ ከቃጠሎው ጋር በተገናኘ አሥር ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ቃላቸውን እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡  

ለጋምቤላ እርሻዎች የተሰጠው ብድር የልማት ባንክን መመለስ ያልቻሉ ብድሮች ወደ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር አድርሷል ተባለ

በመንግሥት ድጋፍ የግል አልሚዎች በጋምቤላ ክልል ለጀመሯቸው ሰፋፊ እርሻዎች የተለቀቀው ብር የኢትዮጵያ ልማት ባንክን የማይመለስና መመለሳቸው አጠራጣሪ የሆኑ ብድሮች መጠን፣ 8.6 ቢሊዮን ብር እንዲደርስ ምክንያት ሆነዋል ተባለ፡፡ ይኼንን ያሉት የአገሪቱ የገንዘብ ተቋማትን የሚቆጣጠረው ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ናቸው፡፡

በሰፋፊ እርሻዎች የተንሰራፋውን ችግር ለመፍታት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሳተፉ ተጠየቀ

በተለያዩ ክልሎች በሰፋፊ እርሻ ሥራ የተሰማሩ ኢንቨስተሮች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያወጣው የብድር ፖሊሲ ሊያሠሯቸው እንዳልቻለ በተደጋጋሚ ቢገልጹም፣ ልማት ባንክ ጉዳዩ የፋይናንስ አቅርቦት ብቻ ስላልሆነ ችግሩን ለመፍታት የሚመለከታቸው አካላት መሳተፍ ይኖርባቸዋል አለ፡፡

ካሩቱሪ ንብረቱን ለማስወጣት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቀረበ

መንግሥትና ባለሥልጣናትን እንደሚከስ አስታወቀ የህንዱ ካሩቱሪ ግሩፕ በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ ችግር ውስጥ በመግባቱ ምክንያት ባለፈው ሳምንት ሙሉ ለሙሉ ነቅሎ መውጣቱን ባስታወቀ ማግሥት፣ በአገሪቱ ያሉትን ንብረቶች ለማስወጣት እንዲችል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤቱታውን አቀረበ፡፡

ካሩቱሪ ኩባንያ ከኢትዮጵያ ጠቅልሎ መውጣቱን ይፋ አደረገ

የኩባንያው ባለቤት ‹‹ተስፋ ቆርጫለሁ ተሸንፌያለሁ›› አሉ ለሰባት ዓመታት ያህል በጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ከመቶ ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት የእርሻ ቦታ በመያዝ የሜካናይዝድ ግብርናን ለማካሄድ ሲሞክር የቆየው የህንዱ ካሩቱሪ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ሙሉ በሙሉ ከኢትዮጵያ ለቆ መውጣቱንና ኢንቨስትመንቱን ማቋረጡን ለሪፖርተር ይፋ አደረገ፡፡