Skip to main content
x

አቶ መላኩ ፈንታ አፋጣኝ ውሳኔ ለማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ አልጠብቅም አሉ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ አራት ዓመት ከሰባት ወራት ሲታሰሩ የፍትሕ ፍንጭ ስላላሳያቸው ፈጣሪያቸውንም እንደሚጠራጠሩ ገልጸው፣ የተፋጠነ ውሳኔ ማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ እንደማይጠብቁ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ክስ ተመሠረተባቸው

96.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ እንዲከፍሉ ጥያቄ ቀርቧል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በገቡት ውል መሠረት ግዴታቸውን አልፈጸሙም ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በሁለቱም ላይ የፍትሐ ብሔር ክስ የመሠረተው ሲንጋፖር የሚገኘው ዊልማር ትሬዲንግ ቻይና ፒቲኤ ሊሚትድ ነው፡፡

የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማስገደል ሙከራ አድርገዋል የተባሉት የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አዲስ ክስ ቀረበባቸው

አራጣ ማበደርና ሌሎች የተለያዩ 39 የወንጀል ድርጊቶችን ፈጽመዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን የማስገደል ሙከራ ፈጽመዋል ተብለው አዲስ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ከ107.9 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ ቡና ነጋዴዎች ተከሰሱ

ግንዛቤውና ዕውቀቱ የሌላቸውን ሰዎች ስም በመጠቀምና በሐሰተኛ ሰነድ የቡና ላኪነትን ንግድ ፈቃድ በማውጣት ከ2.7 ሚሊዮን ቶን በላይ ቡና በሕገወጥ መንገድ በመሸጥ፣ 7.9 ሚሊዮን ዶላር ወይም 107.9 ሚሊዮን ብር የውጭ ምንዛሪ መንግሥትን አሳጥተዋል የተባሉ ቡና ነጋዴዎችና ተባባሪዎቻቸው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ መጥሪያ ሊደርሳቸው ነው

ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ፡፡

አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላ በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሩዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳና ምክትላቸው አቶ አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ምስክሮቹ ያልቀረቡበት ምክንያት ሬጅስትራር ማዘዣ ወጪ ሳያደርግ በመቅረቱ እንደሆነ አስረድቶ አሁን ግን ማዘዣ ወጪ እንዲሆን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

መከላከያ ምስክሮቹም ታህሳስ 17፣ 18 እና 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀርበው እንዲሰሙ መጥሪያ እንዲደርሳቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የቀድሞ የአንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ኃላፊዎችና ሠራተኞች በ55.7 ሚሊዮን ብር የሙስና ወንጀል ተከሰሱ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የነበሩ 11 ሰዎች፣ በሕዝብና መንግሥት ላይ ከ55.7 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው የሙስና ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ከአይኤስ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በተባሉ 26 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሠረተ

በኢትዮጵያ የጅሐድ ጦርነት ለማወጅ ዝግጅት እያደረጉ ነበር ተብሏል አይኤስ ከሚባለው የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉና በአዲስ አበባ፣ በሐረርና በአላባ ከተሞች ውስጥ ቡድን በማደራጀትና በማስተባበር ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው የተገለጸ 26 ተጠርጣሪዎች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ኃላፊዎች በ81.2 ሚሊዮን ብር የሙስና ወንጀል ተከሰሱ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከፍተኛ ኃላፊነት የነበራቸው ሰባት ሠራተኞችና ሁለት አማካሪዎች (በሌሉበት)፣ በሕዝብና መንግሥት ላይ በድምሩ ከ81.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው፣ ሐሙስ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 15ኛ ወንጀል ችሎት የሙስና ወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት የማዕድን ሚኒስቴር አምስት ሠራተኞች ዋስትና ተፈቀደላቸው

ለአፋር ክልል ከተገዛ የሮለር ፕላስቲክ ፖሊሺት ግዥ ጨረታ ጋር በተገናኘ፣ ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩት የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ሠራተኞች ዋስትና ተፈቀደላቸው፡፡

የሚኒስቴሩ ሠራተኞች የግዥ ኮሚቴ አባልና ጸሐፊ አቶ የሰውዘር ንጋቱ፣ አባል አቶ ፈቃዱ ራሱና አቶ ዳኛቸው ክንዴ፣ የግዥ ክፍል ባለሙያ አቶ ቴዎድሮስ እማኝና አካውንታንት አቶ ፈለቀ ገብረ ማርያም ናቸው፡፡

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ኃላፊዎች ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረስ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ከባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ግለኃላፊዎች ሰቦች ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረስ ክስ ቀረበባቸው፡፡ ክሱ የቀረባባቸው ከመርከብ፣ የጭነት መኪናዎችና ከኮንቴይነሮች ግዥዎች ጋር በተያያዘ ነው፡፡