Skip to main content
x

የአሜሪካ ኤምባሲ በኢትዮጵያ የሚታየው ግጭት አሳስቦኛል አለ

የአሜሪካ ኤምባሲ በጨለንቆና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በተነሱ ግጭቶች የሰዎች ሕይወት በመጥፋቱና የአካል ጉዳት በመድረሱ እጅግ እንዳሳሰበውና እንዳዘነ ገለጸ፡፡ ኤምባሲው በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ለተጎጂ ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰው የተማሪዎች ግጭት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተዛምቷል

የሦስት ተማሪዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ20 በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል በትግራይ ክልል በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተቀሰቀሰ ግጭት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መዛመቱ ተገለጸ፡፡ በሕይወትና በአካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ተማሪ ሲሞት፣ ከ20 በላይ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዩኒቨርሲቲም በተመሳሳይ በተፈጠረ ግጭት ሁለት ተማሪዎች ሕይወታቸው ማለፉን፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል፡፡

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሞተ

በአዲግራት ዩኒቨርሲቲ አርብ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በተነሳ ግጭት የአንድ ተማሪ ሕይወት ሲጠፋ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎች እንደተጎዱ ታውቋል፡፡ የግጭቱ መነሻ በሁለት ተማሪዎች መካከል የነበረ ጥል እንደሆነና ይህም ወደ ብሔር ግጭት እንዳደገ ታውቋል፡፡

የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ራሱን ያየበት መነጽር

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ለ35 ቀናት የግምገማ ስብሰባ ላይ ከርሟል፡፡ በግምገማውም የድርጅቱ ስትራቴጂካዊ አመራር ክልላዊና አገራዊ ተልዕኮውን ከመወጣት አንፃር ያለበትን ቁመና ለማየት የሚያስችል ሥር ነቀል ግምገማ ማካሄዱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ለ35 ቀናት ግምገማ ላይ የቆየው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀረ

ለ35 ቀናት በግምገማ ላይ የከረመው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት (ትግራይ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚው ኮሚቴውን እንደገና በማዋቀር ተጠናቀቀ፡፡ ሐሙስ ኅዳር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአንድ ወር በላይ የፈጀ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ዘጠኝ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል፡፡ ባወጣው የአቋም መግለጫም ራሱ ላይ አካሂጃለሁ ያለውን ሥር ነቀል ግምገማ በዝርዝር አስታውቋል፡፡

በወ/ሮ አዜብ መስፍን ዕግድ ላይ የሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ እንደሚወስን  ተጠቆመ

ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማና አቶ ዓለም ገብረዋህድ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ናቸው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) በማዕከላዊ ኮሚቴ እያካሄደ በሚገኘው ጥልቅ ግምገማ ከሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ለጊዜው ታግደው እንዲቆዩ በተደረጉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጉዳይ ላይ፣ የሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ የመጨረሻውን ውሳኔ እንደሚሰጥ ምንጮች ገለጹ፡፡

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ ተገለጸ

የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት አተትን መከላከል እንዳልቻለ የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ይህ የተገለጸው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ጉባዔውን ከጥቅምት 28 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት የአተት በሽታ በአገሪቱ ከፍተኛ ጉዳት እንዳደረሰም በጉባዔው ተጠቁሟል፡፡

የትግራይ ክልል ለወጣቶች ከተመደበለት 562 ሚሊዮን ብር ውስጥ 105 ሚሊዮን ብር ብቻ መጠቀሙን አስታወቀ

የፌዴራል መንግሥት ያለውን የወጣቶችን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ የአሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ፈንድ በጅቶ ለክልሎች እያከፋፈለ ቢሆንም፣ ከዚህ ውስጥ የትግራይ ክልል 562 ሚሊዮን ብር እንደተመደበለት ተገልጿል፡፡ ከዚህ ውስጥ ክልሉ እስካሁን ድረስ 105 ሚሊዮን ብር ብቻ መጠቀሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የትግራይ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብረሚካኤል መለስ ዓርብ ጥቅምት 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የተበጀተው ገንዘብ የሚለቀቀው በሁለት ዓመት በመሆኑ ባለፈው ዓመት 205 ሚሊዮን ብር የፌዴራሉ መንግሥት እንዳላከና መጠቀም የተቻለው 105 ሚሊዮን ብር ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡