Skip to main content
x

በይግባኝ ችሎት በነፃ የተሰናበቱት ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጣታቸውን አፀናው

በሙስና ወንጀል ተከሰው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አራት ዓመታት ከስምንት ወራት ፅኑ እስራትና 60,000 ብር የገንዘብ ቅጣት የተወሰነባቸው ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ በይግባኝ ሰሚው ችሎት በነፃ የተሰናበቱ ቢሆንም፣ የሰበር ሰሚ ችሎት የይግባኝ ሰሚ ችሎቱን ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አፀናው፡፡

በእነ አቶ መላኩ ፈንታ መዝገብ በሙስና የተከሰሱት አቶ ከተማ ከበደ ለፍርድ ተቀጠሩ

በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በመዝገብ ቁጥር 131452 ከእነ አቶ መላኩ ፈንታ ጋር በ2006 ዓ.ም. ክስ ተመሥርቶባቸው ሲከራከሩ የከረሙት፣ የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ከፍተኛ ባለድርሻና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ከተማ ከበደ ለፍርድ ተቀጠሩ፡፡ ድርጅቱና ሥራ አስኪያጁ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲያደርጉት የነበረው ክርክር የተጠናቀቀው፣ ዓርብ ጥር 25 ቀን 2010 ዓ.ም ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ በመከላከያ ምስክርነት ላቀረቧቸው ምስክር መስቀለኛ ጥያቄ አቅርቦ ካጠናቀቀ በኋላ ነው፡፡

የቀረጥ ነፃ መብት የፖሊሲ ማስተካከያ ሊደረግበት ነው

ከውጭ አገሮች ለሚገቡ ዕቃዎች ለባለሀብቶችና ለተቋማት ሲሰጥ የቆየው የቀረጥ ነፃ መብት፣ የፖሊሲና የአፈጻጸም ማስተካከያ ሊደረግበት መሆኑ ተገለጸ፡፡ ማክሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነበር ይኼ የተገለጸው፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ ባልቻ ለምክር ቤቱ እንደገለጹት፣ መንግሥት ለባለሀብቶችና ለተለያዩ ተቋማት በሰጠው የቀረጥ ነፃ መብት በአብዛኛው የሚገቡ ዕቃዎች ለታለመላቸው ዓላማ ቢውሉም፣ ጥቂት የማይባሉ ባለሀብቶች (ግለሰቦች) መብቱን ያላግባብ እየተጠቀሙ መሆናቸውን በባለሥልጣኑ በተደረገው የኢንተለጀንስ ጥናት መረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

እየቀነሰ የመጣው የገቢ ንግድ

በአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም፣ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው ወጪ ቅናሽ እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፡፡ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ ዓመታዊ ተከታታይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በተለይ ባለፉት አሥር ዓመታት የገቢ ንግዱ በአማካይ ከ20 በመቶ እያደገ ቢሆንም፣ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው የውጭ ምንዛሪ በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ ነው፡፡ ሰሞኑን ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የ2009 ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውም፣ በ2009 በጀት ዓመት ለወጪ ንግድ የወጣው ወጪ ከቀደመው በ5.5 በመቶ ቀንሷል፡፡ 

ኮንትሮባንዲስቶች እነማን እንደሆኑ ለፓርላማው በግልጽ እንዲናገሩ የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች ተጠየቁ

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባለፈ የፖለቲካ ቀውስ እየፈጠሩ ናቸው የሚባሉ ‹‹ኮንትሮባንዲስቶች›› ማንነት በግልጽ ለፓርላማው እንዲቀርብ፣ የፓርላማው አባላት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ የፓርላማው አባላት በከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ሳይቀሩ በአገሪቱ ለሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ጣታቸውን የሚቀስሩት ‹‹ኮንትሮባንዲስት›› በተባሉ ማንነታቸው በማይታወቅ ኃይሎች ላይ ስለሆነ፣ የእነዚህን ማንነት ፓርላማው በግልጽ የማወቅ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ማንነታቸው እንዲገለጽላቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አመራሮችን ጠይቀዋል፡፡

ውዥንብር የፈጠረው የቀረጥ ነፃ መመርያ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ታኅሳስ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. አወጣ የተባለውና ለመንገደኞች የቀረጥ ነፃ መብት የሚሰጠው መመርያ ያልታሰበ ነበር ሊባል የሚችል ነው፡፡ ሹልክ ብሎ ዱብ ያለ የሚመስለው ይህ መመርያ፣ እውነት መሆኑን ለማመን ብዥታ ውስጥ  ገብተው ከነበሩት አንዱ ነኝ፡፡ ግን ትክክል መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ መመርያው እንዲተገበር ከተፈለገበት ምክንያቶች አንዱ ‹‹ላልረባ ቀረጥ›› የመንገደኞችን ሻንጣ እየበረበሩ ላለመጉላላት የሚለው ነጥብ ጎልቶ ወጥቷል፡፡ የረባና ያልረባ ቀረጥ ብሎ ነገር ያለ ባይመስለኝም ስለመመርያው መውጣት በተገቢው መንገድ ሳንሰማ ከመመርያው ጋር ተያይዞ ተፈጠረ ስለተባለው ቀውስ ጎልቶ ሰማን፡፡

በወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት ቻይናዊ ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ለመንግሥት አቤቱታ አቀረቡ

ሕግን በመጣስ ከ2003 ዓ.ም. እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የግብር ዘመናት አሳውቆ መክፈል የነበረበትን 4,013,586 ብር የትርፍ ገቢ ግብርን ባለመክፈሉ ክስ ከተመሠረተበት ሲሲኤስ ኮም ሰርቪስ ሶሉዩሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር ክስ የመሠረተባቸው ቻይናዊ፣ ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ለመንግሥት አቤቱታ አቀረቡ፡፡

አየር መንገዶች ከሚፈቅዱት የመንገደኞች ሻንጣ በላይ የሚይዙ ሙሉ የቀረጥ ነፃ መብት ተጠቃሚ እንደማይሆኑ ተገለጸ

ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ኢትዮጵያውያን መንገደኞች በተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የቀረጥ ነፃ መብት እንዲያገኙ በቅርቡ ከተወሰነ በኋላ የቀረጥ ነፃ መብቱን የመመዝበር ሙከራ በመታየቱ፣ በአየር መንገዶች ከሚፈቀደው የመንገደኞቹ የሻንጣ ክብደት በላይ የያዙ ቀረጥ የመክፈል ግዴታ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ዋና ኦዲተር ታክስና ግብር መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን እንዳልተሰጠው ለፍርድ ቤት ተነገረ

ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኩባንያዎችን ሒሳብ መርምሮ የግብርና የታክስ ውሳኔዎችን ለመስጠት ሥልጣን እንደሌለውና ግብር ከፋዩ በግብር አዋጅ ላይ የተሰጡትን መብቶች እንዳይጠቀም የሚያግድ መሆኑን፣ አንድ የተፈቀደለት የሒሳብ አዋቂና የታክስ አማካሪ ኤክስፐርት ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡

ትምባሆ ድርጅትን ከገዛው የጃፓን ኩባንያ ጋር ምክክር ሳይደረግ በሲጋራ ላይ የታሰበው ከፍተኛ ታክስ እንዳይጣል ትዕዛዝ ተሰጠ

ብሔራዊ ትምባሆ ድርጅትን በከፍተኛ ዋጋ ከገዛው የጃፓን ኩባንያ ጋር ምክክር ሳይደረግ በሲጋራ ምርቶች ላይ ታክስ እንዳይጣል፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ትዕዛዝ ማስተላለፉን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡