Skip to main content
x

ሜቴክ በያዛቸው የስኳርና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ላይ መንግሥት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በተደጋጋሚ ጊዜ ቢራዘምለትም ሊያጠናቅቅ ያልቻላቸውን አንድ የስኳርና አንድ የአፈር ማዳበሪያ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ፣ መንግሥት ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄ መቅረቡ ተገለጸ፡፡ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ግርማ አመነቴ (ዶ/ር) ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለፓርላማ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት፣ የጣና በለስ ቁጥር ሁለት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ከሜቴክ ተነጥቆ በአዲስ ኮንትራክተር ሥራውን ለማስቀጠል እየተመከረ ነው፡፡

2.5 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር የሚያመርተው ኦሞ ኩራዝ ሁለት ፋብሪካ ሥራ ጀመረ

ከ6.67 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደወጣበት የተገለጸው የኦሞ ኩራዝ ሁለት ስኳር ፋብሪካ የምርት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ፡፡ ባለፈው ዓመት ፋብሪካው የምርት ሙከራ ጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም በድንገተኛ ዝናብ ምክንያት ሙከራው ቢቋረጥም፣ ከታኅሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ ማምረት እንደጀመረ የስኳር ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጋሻው አይችሉህም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ፋብሪካው መጋቢት 14 ቀን 2009 ዓ.ም. የሙከራ ምርት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የለስላሳ መጠጦች አምራች ኩባንያ ኦሮሚያ ውስጥ 720 ኩንታል ስኳር ተወረሰበት

በኢትዮጵያ ሦስት ከተሞች ኮካ ኮላና ሌሎች ለስላሳ መጠጦችን የሚያመርተው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ኩባንያ፣ ለባህር ዳር ፋብሪካው ሲያጓጉዘው የነበረው 720 ኩንታል ስኳር በኦሮሚያ ክልል ጎሃፅዮን ከተማ ተወረሰበት፡፡

ግልብ ገበያ

በአንድ ሳምንት ውስጥ ሦስት ገጠመኞች አስተናግጃለሁ፡፡ ገጠመኝ አንድ! በአውሮፓውያን አቆጣጠር ተሠልታ፣ የመንግሥት ታክስና ሌሎች ክፍያዎች ተቀናንሰውላት ከምትደርሰኝ ደመወዜ አስቤዛ ለመግዛት ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. (ኦክቶበር 29) በከተማችን ከሚታወቁ ሱፐር ማርኬቶች ወደ አንዱ ጎራ አልኩ፡፡ የምፈልጋቸውን ዕቃ መራርጬ ወደ ገንዘብ ተቀባይዋ አመራሁ፡፡

በዘገየው የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት ያረጀው የሸንኮራ አገዳ የ7.4 ቢሊዮን ብር ኪሳራ አስከተለ

በጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት የተተከሉ የሸንኮራ አገዳ በአብዛኛው በማርጀቱ የ7.4 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንዳስከተለ ተገለጸ፡፡  የጣና በለስ ስኳር ፕሮጀክት በማሳው ከተከለው 13,147 ሔክታር አገዳ መካከል በ12,206.6 ሔክታሩ ላይ ያለው አገዳ አርጅቷል፡፡ አገዳው ከተተከለ ከ31 እስከ 51 ወራት ተቆጥረዋል፡፡

የጣና በለስ ስኳር የአገዳ ምርት በጊዜው ባለመሰብሰቡ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ እያሳጣ ነው

ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት 12,206.6 ሔክታር ላይ ያለ አገዳ አርጅቶብኛል አለ፡፡ አገዳው ያረጀው ወቅቱን ጠብቆ ባለመሰብሰቡ ነው፡፡ አገዳውን ከማሳው ለማስወገድና መሬቱን ለመንከባከብ 1.06 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

ያጣ የነጣው የስኳር ፈላጊ ድምፅ!

ዛሬም ስለስኳር እጥረት ልናወራ ነው፡፡ የስኳር ገበያ መላ ቅጡን እያጣ ነው፡፡ የመፍትሔ ያለ ያልተባለበት ጊዜ ግን የለም፡፡ ዛሬም ችግሩ ብሶበታልና የመፍትሔ ያለ የሚል ድምፅ ማሰማት ተገቢ ነው፡፡ ስኳር የተረጋጋ ገበያ ኖሮት ሸማቹ ያለ አቅርቦትና ያለ ዋጋ ችግር የተገበያየበትን ወቅት ማሰብ ከባድ እየሆነ ነው፡፡

ከኬንያ ድንበር የተመለሰው ስኳር ለአገር ውስጥ እንዲቀርብ ሊወሰን ይችላል ተባለ

ወደ ኬንያ ኤክስፖርት ለማድረግ ታስቦ ሞያሌ ድንበር ደርሶ የነበረው 4,400 ቶን ስኳር፣ ለአገር ውስጥ ገበያ እንዲቀርብ ሊወሰን እንደሚችል ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የተገለጸውን መጠን ስኳር አግሪኮሞዲቲስ ኤንድ ፋይናንስ ለተባለ ኩባንያ ከሸጠ በኋላ፣ ኩባንያው ወደ ኬንያ የሚገባበትን ሁኔታዎች ባለማመቻቸቱ በሞያሌ ድንበር በእርጥበታማ ሙቀት ለሁለት ወራት በተሽከርካሪዎች ላይ ለመቆየት ተገዷል፡፡