Skip to main content
x

በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወጣቱ ተሳታፊ ባለመደረጉ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወጣቱ ትውልድ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ባለመደረጉ፣ አሁን አገሪቱን ዋጋ እያስከፈለ ነው ሲሉ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ርስቱ ይርዳ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፣ ወጣቱ በአገሪቱ የለውጥ ጉዞ ባለቤትና ተጠቃሚ ባለመሆኑ በፖለቲካዊ ጉዳዮችም ንቁ ተሳታፊ እንዳይሆን እንዳደረገው አስረድተዋል በዚህ የተነሳም ዛሬ ዋጋ እያስከፈለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ፓርላማው ከዕረፍት መልስ መደበኛ ስብሰባውን ሐሙስ ይጀምራል

የ2010 ዓ.ም ግማሽ የሥራ ዘመኑን መጠናቀቅ ተከትሎ ለዕረፍት ዝግ ሆኖ የከረመው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ከአንድ ወር በኋላ መደበኛ ስብሰባውን ከሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚጀምር የምክር ቤቱ ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ፓርላማው በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ እንዲወስን በአስቸኳይ ተጠራ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአስቸኳይ አዋጁ ላይ እንዲወስኑ ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ፡፡ ከየካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ዕረፍት የወጡት የፓርላማ አባላት ለአስቸኳይ ስብሰባ በመጠራታቸው ምክንያት፣ ከማክሰኞ የካቲት 20 ቀን 2010 ጠዋት ጀምሮ ሪፖርት ሲያደርጉ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሊቀመጥ ነው

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከረቡዕ የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚሰበሰብ ታወቀ፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ምክር ቤት በቅርቡ ይሰበሰባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የስብሰባዎቹ ዓላማም ተተኪውን የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ለመምረጥ ነው፡፡

አዳዲስ ውሳኔዎችን ያካተተው የኦሕዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ አንድምታ

የኦሮሚያ ክልል ከዘጠኝ ክልሎችና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች ሰፊ የቆዳ ስፋትና ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር አለው፡፡ የክልሉ የቆዳ ስፋት 284,538 ካሬ ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2017 መረጃ መሠረት የክልሉ የሕዝብ ቁጥር 36 ሚሊዮን ነው፡፡ ክልሉ ከአገሪቱ ክልሎች የበለጠ ሰፊ የቆዳ ስፋት ያለው ከመሆኑ ባሻገር፣ ከጎረቤት አገሮች ጋር በቀጥታ በድንበር ይዋሰናል፡፡ በደቡብ አቅጣጫ ከኬንያና በምዕራብ በኩል ደግሞ ከሱዳን ጋር ወሰንተኛ ነው፡፡

የቀረጥ ነፃ መብት የፖሊሲ ማስተካከያ ሊደረግበት ነው

ከውጭ አገሮች ለሚገቡ ዕቃዎች ለባለሀብቶችና ለተቋማት ሲሰጥ የቆየው የቀረጥ ነፃ መብት፣ የፖሊሲና የአፈጻጸም ማስተካከያ ሊደረግበት መሆኑ ተገለጸ፡፡ ማክሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነበር ይኼ የተገለጸው፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሞገስ ባልቻ ለምክር ቤቱ እንደገለጹት፣ መንግሥት ለባለሀብቶችና ለተለያዩ ተቋማት በሰጠው የቀረጥ ነፃ መብት በአብዛኛው የሚገቡ ዕቃዎች ለታለመላቸው ዓላማ ቢውሉም፣ ጥቂት የማይባሉ ባለሀብቶች (ግለሰቦች) መብቱን ያላግባብ እየተጠቀሙ መሆናቸውን በባለሥልጣኑ በተደረገው የኢንተለጀንስ ጥናት መረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

ኮንትሮባንዲስቶች እነማን እንደሆኑ ለፓርላማው በግልጽ እንዲናገሩ የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች ተጠየቁ

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባለፈ የፖለቲካ ቀውስ እየፈጠሩ ናቸው የሚባሉ ‹‹ኮንትሮባንዲስቶች›› ማንነት በግልጽ ለፓርላማው እንዲቀርብ፣ የፓርላማው አባላት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡ የፓርላማው አባላት በከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ሳይቀሩ በአገሪቱ ለሚታየው የፖለቲካ ቀውስ ጣታቸውን የሚቀስሩት ‹‹ኮንትሮባንዲስት›› በተባሉ ማንነታቸው በማይታወቅ ኃይሎች ላይ ስለሆነ፣ የእነዚህን ማንነት ፓርላማው በግልጽ የማወቅ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ ማንነታቸው እንዲገለጽላቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን አመራሮችን ጠይቀዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ መጓተቱን የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለማግኘት ተመዝግበው በየወሩ እየቆጠቡ የሚገኙ ቢሆንም፣ ግንባታው ግን አዝጋሚ መሆኑ በፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ተገለጸ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ በ20/60 እና በ40/80 ቤቶች ፕሮግራም ሳይቶች ላይ ባካሄደው ቅኝት  ግንባታው በተያዘለት ዕቅድ ከመሄድ ይልቅ እየተጓተተ መሆኑን አስታውቋል፡፡