Skip to main content
x

የብሔራዊ ባንክ ውሳኔን የሚጠብቀው የባንክ ዳይሬክተሮች ሹመት

የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት በአገሪቱ ሕግ መሠረት ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴያቸውን የሚያሳይ ሪፖርት በማጠናቀር በውጭ ኦዲተሮች ተመርምሮ የተመሰከረ የሒሳብ ሪፖርታቸውን ባለአክሲየኖች ለሚታደሙበት ጠቅላላ ጉባዔ ያሰማሉ፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱ ከሌሎች የአክሲዮን ኩባንያዎችና በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ከተመለከተው ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕግጋትና መመርያዎችን የተከተሉ ጉባዔዎችን የማካሄድ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ በማኅተም የተደገፈ የውጭ ምንዛሪ ምዝገባ ቁጥር ለአመልካቾች እንዲሰጥ የሚያሳስብ ማስታወቂያ አወጣ

የውጭ ምንዛሪ ጥያቄን በግልጽነት ለማዳረስና ለማስተዳደር በማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ዓመት በፊት ያወጣውና በየጊዜው ሲያሻሽለው የቆየውን መመርያ በቅርቡ ከማማሻሉም በላይ፣ ይህንኑ መመርያ መሠረት ያደረገና የውጭ ምንዛሪ ጥያቄ የሚያቀርቡ ደንበኞች ላቀረቡት ጥያቄ በማኅተም የተደገፈ ተራ ቁጥርን ጨምሮ ሌሎች መብቶችና ግዴታዎቻቸውን የሚገልጽ ማስታወቂያ በየባንኮች መለጠፍ ጀመረ፡፡

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ባለ 18 ፎቅ ጊዜያዊ የዋና መሥሪያ ቤት ለመገንባት ስምምነት ተፈራረመ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ባለ 18 ፎቅ ጊዜያዊ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ለማስገንባት፣ ቻይና ውይ ከተባለ የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡ ሕንፃው የሚገነባው ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ያተረፈው ደቡብ ግሎባል ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ለማሟላት እንደሚሠራ ገለጸ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪውን ዘግይቶ የተቀላቀለው ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ በ2009 ዓ.ም. ከታክስ በፊት 67.7 ሚሊዮን ብር አተረፈ፡፡ የተከፈለ ካፒታሉ ግማሽ ቢሊዮን ብር እንደሚያደርስ አስታወቀ፡፡ ቅዳሜ ታህሳስ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. ባንኩ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሠረት፣ ከታክስ በፊት ያስመዘገበው ትርፍ ከ2008 ዓ.ም. አኳያ ከ253 ሺሕ ብር በላይ ወይም የ0.4 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ በቀደመው ዓመት ባንኩ ከታክስ በፊት ያገኘው ትርፍ 67.9 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡ ይህም ትርፍ ቢሆን ከሌሎች ባንኮች አንፃር አነስተኛ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡

የአክሲዮን ገበያ አለመጀመሩ ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነ ተገለጸ

የአክሲዮን ገበያ ቢቋቋም 200 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማመንጨት እንደሚቻል ተጠቆመ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም በመለየት ብሔራዊ የአክሲዮን ገበያ (Stock Market) አለማቋቋሟ፣ በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ የፋይናንስ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ ማክሰኞ ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በተከፈተው ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ባለመቋቋሙ ምክንያት ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልግ ካፒታል ማመንጨት አለመቻሉን፣ በዚህም አገሪቱን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች እያሳጣት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የአክሲዮን ገበያ አለመጀመሩ ዋጋ እያስከፈለ እንደሆነ ተገለጸ

የአክሲዮን ገበያ ቢቋቋም 200 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማመንጨት እንደሚቻል ተጠቆመ ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም በመለየት ብሔራዊ የአክሲዮን ገበያ (Stock Market) አለማቋቋሟ፣ በኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ የፋይናንስ ባለሙያዎች አስታወቁ፡፡ ማክሰኞ ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ በተከፈተው ሁለተኛው የምሥራቅ አፍሪካ የፋይናንስ ጉባዔ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ባለመቋቋሙ ምክንያት ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልግ ካፒታል ማመንጨት አለመቻሉን፣ በዚህም አገሪቱን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች እያሳጣት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት ተደጋጋሚ ጥሪ ያቀረበባቸውን የተከማቹ ኮንቴይነሮች መውረስ ጀመረ

በሞጆ ደረቅ ወደቦች ለረዥም ጊዜ የተከማቹ ኮንቴይነሮችን ባለቤቶቻቸው እንዲያነሱ ተደጋጋሚ ጥሪ አቅርቦባቸው ባለመነሳታቸው መንግሥት መውረስ ጀመረ፡፡ ከውጭ አገሮች ገብተው በሞጆ ደረቅ ወደብ የተከማቹ ከ8,100 በላይ ኮንቴይነሮችን በተመለከተ አስተዳደሩ የሰጠው የአሥር ቀናት ጊዜ ገደብ ረቡዕ ታኅሳስ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ አብዛኞቹ ምላሽ አለመስጠታቸውን የሞጆ ደረቅ ወደብ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አዲስ አየለ ዓርብ ታኅሳስ 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ በጊዜ ገደቡ ውስጥ አስመጪዎች ያለባቸውን የመንግሥት ዕዳ ከፍለው እንዲያነሱ፣ ያልተነሱትን ደግሞ እንደሚወርስ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር፡፡

ደቡብ ግሎባል የተከፈለ ካፒታሉን 620 ሚሊዮን ብር አድርሳለሁ አለ

ከ16ቱ የግል ባንኮች የባንክ ኢንዱስትሪውን ዘግይቶ የተቀላቀለው ደቡብ ግሎባል ባንክ በ2009 ሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 67.7 ሚሊዮን ብር እንዳተረፈ አስታወቀ፡፡ የተከፈለ ካፒታሉንም ወደ 500 ሚሊዮን ብር አደርሳለሁ ብሏል፡፡

ብርሃንና ቡና ባንክ የምርት ገበያን ሥርዓት ተቀላቀሉ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ክፍያና ርክክብ ለሚያስፈጽሙ ሁለት ባንኮች ተጨማሪ ባንኮች ዕውቅና ሰጠ፡፡ ዕውቅና የተሰጣቸው ባንኮች ቁጥር 12 ማድረሱንና ለተመሳሳይ ሥራ አምስት ባንኮች ጥያቄ ማቅረባቸውን ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

ብርሃን ባንክ የተከፈለ ካፒታሉን ወደ 1.4 ቢሊዮን ብር አሳደገ

ከፍተኛ ባለአክሲኖችን በማሰባሰብ ቀዳሚ ሆኗል ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ በተጠናቀቀው የ2009 የሒሳብ ዓመት ብቻ ከአምስት ሺሕ በላይ አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን በማሰባሰብ የባለአክሲዮኖቹን ቁጥር ከ14 ሺሕ በላይ እንዳደረሰና የተከፈለ ካፒታሉን 91 በመቶ በማሳደግ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ እንዳሳደገ ተገለጸ፡፡