Skip to main content
x

ሦስቱ አገሮች ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ሊወያዩ ነው

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ውይይት ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርጉት ውይይት ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካርቱም ይካሄዳል፡፡ 

ግብፃዊያን በህዳሴ ግድቡ ግንባታ ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ ነው

ግብፃዊያን ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የተለያየ አመለካከት እንዳላቸው፣ ይህንን አመለካከት ወደ አንድ ሐሳብ ለማምጣትና የጋራ አቋም ለመያዝ ውይይት ሊያደርጉ መሆኑ ታወቀ፡፡ 30ኛውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመካፈል የመጡና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ የግብፅ ዲፕሎማት ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አብዛኛው የግብፅ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳል፡፡ የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስና ሁሉም ግብፃውያን የጋራ አቋም እንደሚኖራቸው ለማድረግ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ የአገሪቱ ሕዝብ ከመንግሥት አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የግብፅ ጉብኝት ፋይዳ

የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ገጽታዎች እንደነበራት ታሪክ ያስረዳል፡፡ ሁለቱ አገሮች ጥንት የጦር መሣሪያ የተማዘዙት ጊዜ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ በ2003 ዓ.ም. የህዳሴ ግድቡን የመሠረት ድንጋይ ከጣለችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ግብፅ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ስትከተልና የተለያዩ ሐሳቦችን ስታራምድ መቆየቷን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በፊት የነበሩት መሐመድ ሙርሲ መሪዎች ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን ግንባታ እንድታቆም ከማስፈራራት ባሻገር፣ ግብፅ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ብድርም ሆነ ድጋፍ እንዳያደርጉ ስትወተውት ቆይታለች፡፡ አብዱልፈታህ አልሲሲ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህም ቢሆን የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የተለያዩ አወዛጋቢ አስተያየቶችን ሲሰጡ ተደምጧል፡፡ ‹‹የናይል ወንዝ ለግብፃውያን የሞትና ሽረት ጉዳይ ነው፤›› ከማለት ባሻገር፣ ‹‹በግብፅ የውኃ ሀብት ላይ ማንም ጣልቃ እንዲገባ አልፈቅድም፤›› ሲሉ መደመጣቸው አይዘነጋም፡፡

ግብፅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የለኝም አለች

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በቀጥታ በቴሌቪዥን ለግብፃውያን ባስተላለፉት መልዕክት፣ አገራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የላትም ማለታቸው ተሰማ፡፡ ‹‹በቀጣናው ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ጠንቅቀን የምናውቅ በመሆኑ ግብፅ በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአገሮችን ሉዓላዊነት አትደፍርም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ግብፅ ከወንድሞቿ ጋር ወደ ጦርነት አትገባም፡፡ ምክንያቱም ሰላም አንዱ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው፤›› ማለታቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ‹‹ከማንኛቸውም ጎረቤቶቻችን ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ዕቅዱም ሆነ ፍላጎቱ የለንም፤›› ሲሉ በቀጥታ በተላለፈው የቴሌቪዥን ሥርጭት መናገራቸውን የዜና አውታሮች ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያውያን የህዳሴ ግድቡን ለመገንባት ጫናውን ለብቻቸው ስለተሸከሙ ዕዳ አለብን››

የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በመገንባት ጫናውን ለብቻቸው እንደተሸከሙ፣ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል በሽር ተናገሩ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን መልዕክት ሲያደርስና በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ በተነጋገረበት ወቅት መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያና የግብፅ አዲሱ አሠላለፍ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴ ግድቡን አሞላልና አለቃቀቅ፣ እንዲሁም አካባቢያዊ ተፅዕኖ በተመለከተ የሦስትዮሽ ውይይት ማድረግ ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ሦስቱ አገሮች የጋራ የአጥኚዎች ቡድን በማቋቋም የሦስትዮሽ ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የህዳሴ ግድቡ የሚኖረውን ተፅዕኖ እንዲያጠና የቀጠሩት የፈረንሣዩ ‹‹ቢአርኤል›› የተሰኘው ተቋም የሚሠራበትን የመነሻ ሐሳብ ለማርቀቅ ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ቢሆንም ግን በውይይት መነሻ ሐሳቡ ላይ ግብፅና ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ይታወቃል፡፡

የዓለም ባንክ በታላቁ ህዳሴ ግድብ አደራዳሪ እንዲሆን በግብፅ መጠየቁ ሥነ ሥርዓት የጣሰ መሆኑ ተገለጸ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የዓለም ባንክ አደራዳሪ እንዲሆን ግብፅ ያቀረበችው ጥያቄ ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የተስማሙበትን የውይይት ሥነ ሥርዓት የጣሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ግብፅ ለመጪዎቹ 20 ዓመታት ለምትተገብራቸው የግብርናና የውኃ ሀብት ዕቅዶቿን ይፋ አደረገች

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሻኩሪ በናይል ጉዳይ ለመነጋገር ሰኞ፣ ታኅሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ፣ የመስኖ ሚኒስትር ሞሐመድ አብደል አቲ ለግብፅ ፓርላማ የ20 ዓመታት የመንግሥታቸውን የውኃና የመስኖ አጠቃቀም ዕቅድን አሰምተዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ ከግብፅ ጋር ብቻ የሁለትዮሽ ምክክር አይደረግም አለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሲወያዩ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን ያልተካተተችበት የሁለትዮሽ ምክክር በህዳሴ ግድቡ ላይ እንደማታደርግ አስታወቁ፡፡

የግብፅ ፓርላማ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጉብኝት ላይ የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ አደረገ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በግብፅ ፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዳያደርጉ የግብፅ ፓርላማ አባላት ያቀረቡትን ተቃውሞ፣ የአገሪቱ ፓርላማ ውድቅ ማድረጉ ተሰማ፡፡ በግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱፈታህ አልሲሲ የተጋበዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በሚቀጥለው ሳምንት በግብፅ ፓርላማ ተገኝተው፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የመንግሥታቸውን አቋምና በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ላይ ንግግር እንዲያቀርቡ መጋበዛቸው ይታወቃል፡፡ ይህንን በመቃወም 19  የግብፅ ፓርላማ አባላት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጉብኝት፣ እንዲሁም በግብፅ ፓርላማ ንግግር እንዲያደርጉ የተያዘውን ፕሮግራም በመቃወም የተቃውሞ ፊርማቸውን ለአፈ ጉባዔው አቅርበው ነበር፡፡