Skip to main content
x

በአትሌቲክስ ዝቅተኛ ውጤት በሚታይባቸው ርቀቶች ሻምፒዮና ሊዘጋጅ ነው

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት የሚካሄድ ዝቅተኛ ተሳትፎና ውጤት የሚታይባቸውን የአትሌቲክስ ተግባራት ለማጠናከር ሻምፒዮና ሊዘጋጅ እንደሆነ ተጠቆመ፡፡ ከጥር 15 እስከ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. የአጭር፣ የመካከለኛ፣ የዕርምጃና የሜዳ ተግባራት የሚያጠቃልለውን የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚካሄድ የፌዴሬሽኑ ድረ ገጽ አስታውቋል፡፡

የ2017 የአትሌቲክስ ትውስታዎች

ዓለም ታኅሣሥ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. በተጠናቀቀው የአውሮፓውያኑ 2017 በአትሌቲክሱ አዳዲስ ክስተቶችን አስተናግዳለች፡፡ የተከናወኑት የረዥም ርቀት ውድድሮች የሁሉንም ቀልብ መግዛት ችለዋል፡፡ በተለይ በ5ሺሕ ሜትር ርቀት ላይ ፉክክሩ ልዩ ነበር፡፡ ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማኅበር ኤይኤኤኤፍ የ2017 የአትሌቲክስ ቅኝት መሠረት በተለይ ረዥም ርቀቱን ይበልጥ ተመልክቶታል፡፡

የታላቁ ሩጫ የክልል ጉዞ ከሐዋሳ ጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ክብረ በዓልን በማስመልከት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በክልሎች ሊያከናውን ካቀዳቸው የጎዳና ውድድሮች ቀዳሚውን በሐዋሳ አከናወነ፡፡ እሑድ ታኅሣሥ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ውድድሩን የጀመረው ታላቁ ሩጫ የተለያዩ የክለብ አትሌቶች የከተማዋ ነዋሪና የንግድ ባንኩ ደንበኞችን አሳትፏል፡፡

ለባለቤቶቹ ጥያቄ እጁን የሰጠው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሸን በጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ፣ የሴት አመራሮችን ለኃላፊነት በማብቃትና የተለያዩ ደንብና መመርያዎችን በማጽደቅ ተጠናቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ ኅዳር 17 ቀን 2010 ዓ.ም. በአራራት ሆቴል በጠራው አስቸኳይ ጉባዔ በኦሊምፒክ ለጥቁር አፍሪካውያት በፈር ቀዳጅነቷ የምትታወቀው ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉን የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት እንድትሆን በሙሉ ድምፅ ተቀብሏታል፡፡

ትውፊታዊው ሩጫ

የዛሬ 17 ዓመት ‹‹ሀ›› ብሎ የጀመረው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በተሳታፊዎች ቁጥርና በሚያበረክተው ማኅበራዊ አስተዋጽኦ ዕድገት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡ ይህ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው ባሻገር ብዙዎችን በአንድ መድረክ የሚያሰባስብ የመዝናኛ ትውፊት እየሆነ መምጣቱ በሩጫው የሚሳተፉም ሆነ ሌሎች የሚስማሙበት ሆኗል፡፡

በዘንድሮ ታላቁ ሩጫ 48 ሺሕ ተሳታፊዎች ይሮጣሉ

ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች 1.6 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዷል በየዓመቱ በኅዳር ወር የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እንደ ወትሮው በመፀው ወቅት 48 ሺሕ ተሳታፊዎችን ያካተተ ቶታል የ2017 የጎዳና ሩጫውን ያስተናግዳል፡፡ የዘንድሮ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ትኩረት ከሰጣቸው ማኅበራዊ ጉዳዮች መካከል፣ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊና ወሲባዊ ትንኮሳዎችን ለመግታት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ ይገኙበታል፡፡