Skip to main content
x

የበረራ አስተናጋጇን ገድላለች የተባለችው ተከሳሽ እንድትከላከል ብይን ተሰጠ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ የበረራ አስተናጋጅና ወደ ሌላ ሥራ ተሰማርታ የነበረችውን የስምንት ወር ነፍሰ ጡር በፍልጥ እንጨት ቀጥቅጣ ገድላለች የተባለችው የቤት ሠራተኛ፣ የቀረበባትን ክስ እንድትከላከል ብይን ተሰጠ፡፡

በጠና መታመማቸው ታውቆ የ390 ሚሊዮን ብር ዋስትና የተፈቀደላቸው ተከሳሽ አረፉ

ከታክስና ግብር ጋር በተገናኘ በሙስና ወንጀል ተከሰው ላለፉት አራት ዓመታት በእስር ላይ ሆነው ሲከራከሩ የነበሩት አቶ ታደለ ብርሃኑ፣ የካቲት 11 ለ12 ቀን 2010 ዓ.ም. አጥቢያ ሕይወታቸው ማለፉ ተገለጸ፡፡ የ390 ሚሊዮን ብር ዋስትና የተፈቀደላቸው በጤና መታመማቸው ከታወቀ በኋላ ነው፡፡

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና የንግሥት ይርጋ ክስ ተቋረጠ

በወልቃይት ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብና ግጭት የሽብር ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው በሒደት ላይ የነበሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ንግሥት ይርጋ ክሳቸው ተቋረጠ፡፡ ከስምንት ዓመታት በፊት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ጽጌ፣ ኮሎኔል ደምሰው አንተነህና ሌሎች ፍርደኞች በይቅርታ እንዲፈቱ፣ የፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ወስኖ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ተላለፈ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ሠራተኛ ከግብረ አበሮቹ ጋር በከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ተከሰሰ

የማይገባ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኛነቱን በመቀጠም፣ ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ከባድ የማታለል የሙስና ወንጀል ፈጽሟል የተባለው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሠራተኛ ክስ ተመሠረተበት፡፡

ክሳቸው የተቋረጠው እነ አቶ በቀለ ገርባ ከእስር ተለቀቁ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ከየካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ክሳቸው እንዲቋረጥ ያደረገላቸው አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሰባት ተጠርጣሪዎች፣ ማክሰኞ የካቲት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ከእስር ተለቀቁ፡፡ በተጨማሪም ከ340 በላይ ተጠርጣሪዎች ረቡዕ የካቲት 7 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚፈቱ ታውቋል፡፡

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በመከላከያ ምስክርነት ተቆጠሩ

በአማራ ክልል በጎንደር ከተማና ሰሜን ጎንደር በተለያዩ ወረዳዎች ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ ከግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አመፅ በማስነሳትና በመምራት በግልና በመንግሥት ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው እነ ንግሥት ይርጋ፣ የክልሉን ፕሬዚዳንት ጨምሮ በርካታ ባለሥልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ቆጠሩ፡፡

በጉራፈርዳ 55 ሰዎች መግደላቸው የተረጋገጠባቸው ተከሳሾች የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተወሰነባቸው

በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ መለያ፣ ኮመታ፣ ጋቢቃ፣ ኩኪ፣ ኡይቃ፣ ቢቢታ፣ ስመርታና ከነዓን ቀበሌዎች በሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆችና በፌዴራል ፖሊሶች ላይ በድምሩ የ55 ሰዎችን ሕይወት ማጥፋታቸው የተረጋገጠባቸው 18 ተከሳሾች፣ በዕድሜ ልክና ከሦስት ዓመታት ከሦስት ወራት እስከ 22 ዓመታት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ተሰጠ፡፡

ፍርደኞችና ክሳቸው የተቋረጠ እስረኞች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው እንዲፈቱ ተወሰነ

በተከሰሱበት ወንጀል የተፈረደባቸውና ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ በመንግሥት የተወሰነላቸው 746 እስረኞች የሚፈቱት፣ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቦ ከፀና በኋላ የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው ነው፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ሐሙስ የካቲት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዳስታወቀው፣ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ከተፈረደባቸው ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ 417 ፍርደኞች ይቅርታ እንዲደረግላቸው በፌዴራል ይቅርታ ቦርድ ተወስኖ ለአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ቀርቧል፡፡ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕጉ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረትም ጉዳያቸው በመታየት ላይ የነበረ የ329 ተጠርጣሪዎችን ክስ ይቋረጣል፡፡

የፍርድ ቤት ዕግድ የጣሱ የሥራ ኃላፊዎች ወንጀል መፈጸማቸውን ፍርድ ቤት አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦስት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ፍርድ ቤት የሰጠውን የዕግድ ትዕዛዝ በመተላለፍ የግል ይዞታን ‹‹የመንግሥት ይዞታ ነው›› በማለት የባለይዞታዎችን ቤት በማፍረሳቸው ‹‹ወንጀል ፈጽመዋል›› ሲል፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 13ኛ ይግባኝ ሰሚ ፍትሐ ብሔር ችሎት ውሳኔ  ሰጠ፡፡