Skip to main content
x

የቀንጢቻ የታንታለም ማዕድን ማውጫን በጋራ ለማልማት ጨረታ ወጣ

የመንግሥት ልማት ድርጀቶች ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን የሚገኘውን የቀንጢቻ ታንታለም ማዕድን ማውጫ፣ ከመንግሥት ጋር በጋራ ማልማት ለሚፈልጉ የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች በድጋሚ ጨረታ አወጣ፡፡ ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ሦስት ጊዜ ጨረታ ቢያወጣም ሒደቱ መሳካት ባለመቻሉ፣ ጨረታውን በመተው ከተለያዩ ኩባንያዎች ጋር ድርድር ሲያደርግ ቆይቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ድርድሩ አሁንም ባለመሳካቱ በድጋሚ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ጨረታ ያወጣ ሲሆን፣ ጨረታው ሚያዝያ 8 ቀን 2010 ዓ.ም. እንደሚከፈት ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ አስተዳደር በስድስት ወራት 60 ሔክታር መሬት ለጨረታ ለማቅረብ የያዘው ዕቅድ ሳይሳካ ቀረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 ካወጣ በኋላ ለአገልግሎት መስጫ ግንባታዎች መሬት የሚቀርበው በጨረታ ብቻ መሆን ቢደነግግም፣ ባለፉት ስድስት ወራት ምንም ዓይነት መሬት አላቀረበም፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነሐሴ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ካወጣው 28ኛ ዙር ሊዝ ጨረታ ውጪ ባለፉት ስድስት ወራት በጨረታ መሬት አልቀረበም፡፡

ሃያ ሦስት ሺሕ ቶን ብረት ለመግዛት የወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተሰረዘ

የመከላከያ ፋውንዴሽን 23 ሺሕ ሜትሪክ ቶን አርማታ ብረት ለመግዛት አውጥቶት የነበረውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ለመሰረዝ ተገደደ፡፡ በምትኩ ተቋሙ የአገር ውስጥ ጨረታ እንደሚያወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡  ስድስት ያህል ዓለም አቀፍ የዓርማታ ብረት አቅራቢዎችን ሲያሳትፍ የነበረው ጨረታ የቴክኒክ ግምገማው ሲደረግ ቢቆይም፣ ተቋሙ በመጨረሻ ብረቱን ለመግዛት የሚያስችለውን የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻሉ ጨረታውን መሰረዙ ተገልጿል፡፡