Skip to main content
x

ሃያ ሦስት ሺሕ ቶን ብረት ለመግዛት የወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተሰረዘ

የመከላከያ ፋውንዴሽን 23 ሺሕ ሜትሪክ ቶን አርማታ ብረት ለመግዛት አውጥቶት የነበረውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ለመሰረዝ ተገደደ፡፡ በምትኩ ተቋሙ የአገር ውስጥ ጨረታ እንደሚያወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡  ስድስት ያህል ዓለም አቀፍ የዓርማታ ብረት አቅራቢዎችን ሲያሳትፍ የነበረው ጨረታ የቴክኒክ ግምገማው ሲደረግ ቢቆይም፣ ተቋሙ በመጨረሻ ብረቱን ለመግዛት የሚያስችለውን የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ባለመቻሉ ጨረታውን መሰረዙ ተገልጿል፡፡

ብሔራዊ ባንክ አዲስ የባንኮች የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምና አስተዳደር መመርያ አወጣ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሁሉም የአገሪቱ ባንኮች የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምና አስተዳደራቸውን በጥብቅ ለመቆጣጠር ያስችላል ያለውን አዲስ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምና አስተዳደር መመርያ አወጣ፡፡ የውጭ ምንዛሪ ጥያቄያቸው በቅድሚያ መስተናገድ ይገባል ያላቸውን የገቢ ምርቶችም ይፋ አድርጓል፡፡ አዲሱ መመርያ ቁጥር 51/2017 ይባላል፡፡

ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ንግድ ባንክ ያስቀመጠውን ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማንቀሳቀስ አልቻልኩም አለ

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስቀመጠውን ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ማንቀሳቀስ አለመቻሉ፣ በሚሰጠው የሎጂስቲክስ አገልግሎት ላይ እንቅፋት እንደሆነበት አስታወቀ፡፡

ከአገር ሲወጣና ሲገባ በሚያዝ የብርና የውጭ ምንዛሪ መጠን ላይ ማስተካከያ ተደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማንኛውም ግለሰብ ወደ አገር ውስጥ ሲገባ ወይም ሲወጣ መያዝ የሚችለው የኢትዮጵያ ብርና የውጭ ምንዛሪ መጠን ላይ ማስተካከያ ማድረጉ ታወቀ፡፡ ከሳምንታት በፊት ባወጣው የማሻሻያ መመርያው መሠረት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡም ሆነ የሚወጡ ተጓዦች፣ በእጃቸው እንዲይዙ የሚፈቀድላቸው የኢትዮጵያ ብርም ሆነ የውጭ ምንዛሪ መጠን ላይ ጭማሪ አድርጓል፡፡ ከዚህ ቀደም የነበረው ተመሳሳይ መመርያ የወጣው በ1999 ዓ.ም. ነበር፡፡

ሜቴክ የያዛቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መጓተት የፈጠረው ውዝግብ

• ‹‹አሻጥሮች እየተፈጸሙብኝ ነው›› ሜቴክ • ‹‹ይህንን መስማት ያማል›› ስኳር ኮርፖሬሽን • ‹‹ሕዝቡም እምነት እያጣ ነው እኛም ወደ መሰልቸት ደርሰናል›› የፓርላማ አባል የኢትየጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የያዛቸው ግዙፍ የስርኳና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተት ላለፉት ዓመታት ሲፈጥር የነበረው ውዝግብ አሁንም መፈታት ባለመቻሉ፣ የፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች በሆኑት የመንግሥት ተቋማትና በሜቴክ መካከል ውዝግቡ በድጋሚ ባለፈው ሳምንትም ተደምጧል፡፡

ከ107.9 ሚሊዮን ብር በላይ የውጭ ምንዛሪ አሳጥተዋል የተባሉ ቡና ነጋዴዎች ተከሰሱ

ግንዛቤውና ዕውቀቱ የሌላቸውን ሰዎች ስም በመጠቀምና በሐሰተኛ ሰነድ የቡና ላኪነትን ንግድ ፈቃድ በማውጣት ከ2.7 ሚሊዮን ቶን በላይ ቡና በሕገወጥ መንገድ በመሸጥ፣ 7.9 ሚሊዮን ዶላር ወይም 107.9 ሚሊዮን ብር የውጭ ምንዛሪ መንግሥትን አሳጥተዋል የተባሉ ቡና ነጋዴዎችና ተባባሪዎቻቸው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለማስቀጠል ከ700 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንቶች እንደሚያስፈልጉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ አስታወቁ

የአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዳይገታ ከ700 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቨስትመንቶች በኤክስፖርት ተኮር ዘርፎች እንደሚያስፈልጉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ገለጹ፡፡ የባንኩ ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፣ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ያህል አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በተለይ ኤክስፖርት ተኮር በሆኑ ዘርፎች ማከናወን ስላልተቻለ የኢኮኖሚው ዕድገት ሊገታ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የውጭ ምንዛሪ ለውጡ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ወጪን አናረ

በቅርቡ በውጭ ምንዛሪ ላይ በተደረገው የ15 በመቶ ለውጥ ምክንያት፣ በየካቲት 2010 ዓ.ም. ለሚደረገው አራተኛው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ እንዲያገለግሉ የተገዙ 180 ሺሕ ታብሌት ኮምፒዩተሮችና 128 ሺሕ ፓወር ባንኮች ዋጋ በ144 ሚሊዮን ብር አደገ፡፡

‹‹የዓለም የነዳጅ ዋጋ ካልጨመረ በስተቀር በምንዛሪ ለውጥ ምክንያት ዋጋ አይጨምርም››

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ካልጨመረ በስተቀር የአገር ውስጥ የነዳጅ መቸርቸሪያ ዋጋ በብር የዶላር ምንዛሪ ለውጥ ምክንያት ጭማሪ እንደማይደረግበት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

መንግሥት የገንዘብ ተመን ለውጡ ያመጣውን የገበያ ቀውስ ለማብረድ ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርጓል

ብር ከዶላር ጋር ያለው የውጭ ምንዛሪ ተመን 15 በመቶ እንዲዳከም ከተደረገ በኋላ የተፈጠረውን የገበያ ዋጋ ቀውስ ለመቆጣጠር መንግሥት ዘግይቶ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር ተወያየ፡፡ መንግሥታዊው የንግድ ኩባንያ አለ በጅምላ የውጭ ምንዛሪ በልዩ ሁኔታ እንዲፈቀድለት ጠየቀ፡፡