Skip to main content
x

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግርና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚኖረው ተፅዕኖ

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ከሚሠሩ አገሮች አንዷ ነች፡፡ በሶማሊያ የመሸገውንና ራሱን ‹‹አልሸባብ›› ብሎ የሚጠራውን ቡድን ከመመከትና ከማዳከም ባሻገር፣ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ከላይ ታች ስትል ነበር፡፡

ኤርትራን የሚወክሉ ዲፕሎማቶች የሚሳተፉበት ስብሰባ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

በዓለም አቀፍ ተቋማትና በተለያዩ አገሮች የኤርትራን ሕዝብ በመወከል የሚደራደሩና የሚከራከሩ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች የሚገኙበት ስብሰባ፣ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡ ስብሰባው ቅዳሜ የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የታወቀ ሲሆን፣ የስብሰባው ዋና ዓላማም በኢትዮጵያና በኤርትራ ሰላም ላይ ለመምከር እንደሆነ ታውቋል፡፡ ተወካዮቹ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት የፖለቲካ ልዩነት በሰላም እንዲፈታ፣ የሁለቱ አገሮች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲቀጥል ለመምከር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

አወዛጋቢው የኤርትራ ፕሬዚዳንት መግለጫና የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ

አክብረት ጎይቶም (ስሟ ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል) ተወልዳ ያደገችው በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ነው፡፡ በ1988 ዓ.ም. የስምንተኛ ክፍል ተማሪ እንደነበረች ታስታውሳለች፡፡ አባቷ በአስመራ ከተማ በመንግሥት ትምህርት ቤት መምህር፣ እናቷ ደግሞ የቤት እመቤት እንደነበሩ ትገልጻለች፡፡ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ጎበዝ ተማሪ እንደነበረችና ዶክተር ሆና አገሯን የማገልገል ሕልም እንደነበራት ትናገራለች፡፡

የኤርትራ ፕሬዚዳንትን መግለጫ መንግሥት አጣጣለው

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡትን መግለጫ መንግሥት አጣጣለው፡፡ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈጠረው ቀውስ የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 ምክንያት መሆኑን ገልጸው፣ የሻዕቢያ መንግሥት የኢትዮጵያን መንግሥት አፍርሶ የሽግግር መንግሥት እንደሚያቋቁም ገልጸዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም የፕሬዚዳንቱ መግለጫ ፍሬ አልባና ትኩረትን ከመፈለግ የመጣ ነው ብለው፣ ፕሬዚዳንቱ አልሞትኩም ብዬ አልዋሽም ለማለት ፈልገው መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ግብፅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የለኝም አለች

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በቀጥታ በቴሌቪዥን ለግብፃውያን ባስተላለፉት መልዕክት፣ አገራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመድፈር ዕቅድ የላትም ማለታቸው ተሰማ፡፡ ‹‹በቀጣናው ያለውን የፖለቲካ ቀውስ ጠንቅቀን የምናውቅ በመሆኑ ግብፅ በኢትዮጵያና በሱዳን የውስጥ ጉዳይ በመግባት የአገሮችን ሉዓላዊነት አትደፍርም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ግብፅ ከወንድሞቿ ጋር ወደ ጦርነት አትገባም፡፡ ምክንያቱም ሰላም አንዱ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው፤›› ማለታቸው በተለያዩ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡ ‹‹ከማንኛቸውም ጎረቤቶቻችን ጋር ወደ ጦርነት ለመግባት ዕቅዱም ሆነ ፍላጎቱ የለንም፤›› ሲሉ በቀጥታ በተላለፈው የቴሌቪዥን ሥርጭት መናገራቸውን የዜና አውታሮች ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያና የግብፅ አዲሱ አሠላለፍ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የህዳሴ ግድቡን አሞላልና አለቃቀቅ፣ እንዲሁም አካባቢያዊ ተፅዕኖ በተመለከተ የሦስትዮሽ ውይይት ማድረግ ከጀመሩ ከሁለት ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡ ሦስቱ አገሮች የጋራ የአጥኚዎች ቡድን በማቋቋም የሦስትዮሽ ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የህዳሴ ግድቡ የሚኖረውን ተፅዕኖ እንዲያጠና የቀጠሩት የፈረንሣዩ ‹‹ቢአርኤል›› የተሰኘው ተቋም የሚሠራበትን የመነሻ ሐሳብ ለማርቀቅ ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ቢሆንም ግን በውይይት መነሻ ሐሳቡ ላይ ግብፅና ኢትዮጵያ ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ይታወቃል፡፡

ከሃያ በላይ ኤርትራዊያን የተሳተፉበት የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ተደረገ

በኢትዮጵያና በኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ ከሃያ በላይ ኤርትራውያን አዲስ አበባ መጥተው ውይይት ተካሄደ፡፡ ሴሌብሪቲ ኢቨንትስ የተሰኘ አገር በቀል ተቋም ያዘጋጀው የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መድረክ ባለፈው ሳምንት በሐርመኒ ሆቴል ተካሂዶ ነበር፡፡ ከአሁኖቹ በተጨማሪ ወደ ፊት ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብለው ከሚታሰቡ ኤርትራዊያን ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ሰፋፊ ስብሰባዎችና ውይይቶች እንደሚደረጉ ተጠቁሟል፡፡ በእነዚህ ግለሰቦች አማካይነትና በሴሌብሪቲ ኢቨንትስ አስተባባሪነት በኤርትራ ተመሳሳይ ውይይት ለማካሄድ መታቀዱም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ ሕዝቦችን ለማቀራረብ ያለመው ሌላው አማራጭ

የኢትዮጵያና የኤርትራ ምሁራን በሁለቱ አገሮች ጉዳይ ላይ ሐሙስ ኅዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋራ ውይይት አድርገው ነበር፡፡ በውይይቱ ላይ ኤርትራን በመወከል ለረዥም ዓመታት በአውሮፓና በአሜሪካ የሚኖሩ፣ እንዲሁም ከኤርትራ ሸሽተው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ኤርትራውያን፣ ከስደተኛ ካምፖች ተወክለው የመጡ ኤርትራውያን ምሁራን፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ሲገኙ፣ ኢትዮጵያን በመወከል ደግሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ውጭ አገር የቆዩ ዳያስፖራዎች፣ የሚዲያ ኃላፊዎችና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተው ነበር፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበር ፕሬዚዳንት ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔዎች ማኅበር (አሜሰያ) /Association of Member Episcopal Conferences in Eastern Africa (AMECEA)/፣ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ ምሁራን በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ተወያዩ

የኢትዮጵያና የኤርትራን ሕዝብ የወደፊት ግንኙነት በተመለከተ ከሁለቱ አገሮች የተወከሉ ምሁራን በአዲስ አበባ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ‹‹የሰላም መዝሙር ለኢትዮጵያና ለኤርትራ ሕዝቦች›› በሚል መሪ ቃል ሐሙስ ኀዳር 7 ቀን 2010 ዓ.ም. በሐርመኒ ሆቴል በተካሄደው ውይይት ላይ፣ ኤርትራን በመወከል ከአውሮፓ የመጡና በአዲስ አበባ የሚኖሩ ምሁራን ተገኝተዋል፡፡ በውይይቱም የሁለቱን አገሮች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የገቱ ጉዳዮች ተነስተው ተመክሮባቸዋል፡፡