Skip to main content
x

ሊቢያ የሚገኙ ዜጎች ሊመለሱ ነው

ሊቢያ ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች በመጀመርያው ዙር 21 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ምሽት ከትሪፖሊ ሊመለሱ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው፣ ተመላሾቹ ዛሬ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ይደርሳሉ፡፡

በቀጣዩ ዙር 45 ዜጎች ከትሪፖሊና ከቤንጋዚ የጉዞ ሰነድ ተሰጥቶአቸው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ዝግጅት መጠናቀቁን ጽሕፈት ቤቱ ገልጾ፣ ዜጎችን ከሊቢያ ለመመለስ የተጀመረው ጥረት ከዓለም የስደተኞች ድርጅት ጋር መንግሥት ባደረገው ቅንጅት መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ መሪዎች በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ በአዲስ አበባ ይመክራሉ

ከጥር 14 እስከ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ፣ ኢትዮጵያም ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስከብርባቸው ውይይቶች እንደሚደረጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት ወደ ሥልጣን ከመጡ ለመጀመርያ ጊዜ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ነው፡፡ በአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የአኅጉሪቱን የተለያዩ ችግሮች ከመፍታት አንፃር ጠቃሚ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ገልጸው፣ መሪዎቹም በዋነኝነት በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የተወሰነው በውጭ ተፅዕኖ እንዳልሆነ ተገለጸ

ኢሕአዴግ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የወሰነው፣ በውጭ ተቋማትና መንግሥታት ተፅዕኖ እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ኢሕአዴግ የወሰዳቸው ዕርምጃዎች በተፅዕኖ የመጡ አይደሉም፡፡

የደቡብ ሱዳን አዲሱ የተኩስ አቁም ስምምነትና የተደቀነው ሥጋት

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት ካመሩ አራት ዓመታት አለፉ፡፡ ይህ ግጭት ቆሞ በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ሁለቱ ኃይሎች ያነገቡትን መሣሪያ በመጣል፣ ወደ ጠረጴዛ ውይይት እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጥረት በማድረግ ተጠቃሽ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ ከግብፅ ጋር ብቻ የሁለትዮሽ ምክክር አይደረግም አለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሲወያዩ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን ያልተካተተችበት የሁለትዮሽ ምክክር በህዳሴ ግድቡ ላይ እንደማታደርግ አስታወቁ፡፡

ግብፅ የህዳሴ ግድቡን ቦንድ ለመግዛት ጥያቄ አቅርባ እንደነበር ታወቀ

ከስድስት ዓመት በፊት መሠረቱ ተጥሎ በመገንባት ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቦንድ ለመግዛት፣ የግብፅ መንግሥት ጥያቄ አቅርቦ እንደነበር ታወቀ፡፡ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ግብፅ የህዳሴ ግድቡን ቦንድ ለመግዛት ጥያቄ ብታቀርብም፣ ኢትዮጵያ ግን ውድቅ አድርጋዋለች፡፡ እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ ግብፅ ቦንድ ለመግዛትና የግብፅ ኢንጂነሮች ግንባታውን እንዲያግዙ ጥያቄ ብታቀርብም ውድቅ ሆኖባታል፡፡

ከ660 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮችን ለመርዳትና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ አሜሪካ እገዛ አደርጋለሁ አለች

በመስከረም ወር በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተቀሰቀሰ ግጭት ለተፈናቀሉ ከ660 ሺሕ በላይ ዜጎች፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማድረግና ግጭቱ ዕልባት እንዲያገኝ እገዛ ለማድረግ ፍላጎቱ መሆኑን የአሜሪካ መንግሥት አስታወቀ፡፡

‹‹የግብፅ የፓርላማ አባላት ፊርማ ማሰባሰብ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ላይ አንዳችም ለውጥ አያመጣም›› የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የግብፅ የፓርላማ አባላት ፊርማ ማሰባሰብ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የግብፅ ጉብኝት ላይ አንዳችም ለውጥ እንደማያመጣ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ግብፅ በህዳሴ ግድቡ ላይ እያራመደች ያለችውን አቋም ኢትዮጵያ እንደማትቀበል አስታወቀች

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ባለፈው ሳምንት፣ ‹‹የግብፅን የዓባይ የውኃ ድርሻ ማንም እንደማይነካው ለግብፃውያን ላረጋግጥላቸው እወዳለሁ›› የሚል መልዕክት በማስተላለፋቸው፣ በመግለጫቸው ማግሥትም የግብፅ የመንግሥትና የግል ሚዲያዎች የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ እያወጡዋቸው ያሉ ዘገባዎችንና ግብፅ በዚህ ላይ እያራመደች ያለችውን አቋም ኢትዮጵያ እንደማትቀበል አስታወቀች፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲስተካከል እንግሊዝ ጥያቄ አቀረበች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ እየተፈጠሩ ያሉ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች እንዲስተካከሉ እንግሊዝ ጠየቀች፡፡   ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ እየተከሰተ ካለው ቀውስ ጋር ተያይዞ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግር እንዳለ፣ ኢትዮጵያም ይህን ችግር እንድታስተካክል እንግሊዝ ምክረ ሐሳብ ማቅረቧ ታውቋል፡፡