Skip to main content
x

‹‹የኦሮሚያን ተማሪዎች ከጅግጅጋ የሶማሌን ክልል ተማሪዎች ከኦሮሚያ ውጪ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች መመደብን አላምንበትም››

አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ናቸው፡፡ ክልሉን ላለፉት ስድስት ዓመታት መርተዋል፡፡

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ማብራሪያ ተሰጠ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ፣ ማክሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተዘጋጀ መድረክ ማብራሪያ ሰጡ፡፡

የኦሕዴድ ኮንፈረንስ የአሥር ዓመት ድርጅታዊ ስትራቴጂ በማውጣት ተጠናቀቀ

በአዳማ ከተማ ገልማ አባ ገዳ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ኮንፈረንስ፣ የአሥር ዓመት ድርጅታዊ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ተጠናቀቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ለሪፖርተር እንደተናገሩት የክልሉን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ የአሥር ዓመት የድርጅቱ ስትራቴጂ ይፋ ሆኗል፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ስምንት ሰዎች እንደ ሞቱ ክልሉ አስታወቀ

ሌሎች ምንጮች ቁጥሩን ከፍ አድርገዋል ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን ሃሮ ዴዴሳ ቀበሌ በተነሳው ግጭት ስምንት ሰዎች መሞታቸውን ክልሉ አስታወቀ፡፡ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ቴሶ የሟቾች ቁጥር ስምንት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስምንት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በነቀምቴ ከተማ ሦስት ሰዎች ተገደሉ

ሁለት ባጃጆች ሙሉ በሙሉ ሲቃጠሉ በአንድ ሆቴል ላይ ጉዳት ደርሷል በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ወርቁ ጫላ ማክሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ እሑድ ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በከተማዋ የኢሬቻ በዓል ሲከበር ቦምብ ይዘው የመጡ ወጣቶች አሉ በሚል ሰበብ በተነሳው ግጭት ሁለት ሰዎች ሞተዋል፡፡ ሟቾችም በእውቀቱ ውበት ሙሉጌታ፣ ደገባስ ፈቃደ ካባና ኤርሚያስ ባዩ ምትኬ እንደሚባሉ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱን ሰንገው ስለያዟት ግጭቶች ማብራሪያ የሰጡበት የፓርላማ ውሎ

መስከረም 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመኑን በአገሪቱ ፕሬዚዳንት የመክፈቻ ንግግር የጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባውን ለማካሄድ፣ ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ተሰይሟል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሰዎች ሞተዋል

240 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል በኦሮሚያ ክልል በቡኖ በደሌ ዞንና በአምቦ ከተማ በአንድ ሳምንት ውስጥ 30 ሰዎች ሲሞቱ፣ 37 ያህል ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቡኖ በደሌ ዞን በገቺ፣ በደሌ፣ ጮራና ዴጋ ወረዳዎች ጥቅምት 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ግጭት መቀስቀሱ የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱ ተገልጿል፡፡

የኦሮሞ ወጣቶች ሰንደቅ ዓላማ ይዞ ከወጣው ጋር ሁሉ መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት አሳሰቡ

14 ሰዎች የሞቱበትና በሺሕ የሚቆጠሩ የተፈናቀሉበት ግጭት መቆሙ ተገልጿል የኦሮሞ ወጣቶች የተለያዩ ሰንደቅ ዓላማዎችን አንግቦ ከሚንቀሳቀሰው ጋር ሁሉ መንቀሳቀስ እንደሌለባቸው፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ አሳሰቡ፡፡

የኦሮሚያና የሶማሌ ግጭት በወጪና በገቢ ንግድ መተላለፊያ መስመር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት፣ በወጪና በገቢ ንግድ መተላለፊያ መስመር ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡