Skip to main content
x

ዓቃቤ ሕግ አቶ በቀለ ገርባ ለሰበር ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ሕግን ያልተከተለ ነው አለ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የፈቀደላቸውን የ30 ሺሕ ብር ዋስትና በማገድ፣ አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡ በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት መልሳቸውን ያቀረቡት አቶ በቀለ ገርባ፣ ያቀረቡት አቤቱታ (መልስ) ሕግን ያልተከተለ ነው በማለት ዓቃቤ ሕግ የመልስ መልስ ሰጠ፡፡

በአቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ የተካተቱት የኬኬ ድርጅት ባለቤት የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተው አጠናቀቁ

ከግንቦት ወር መጀመርያ ጀምሮ በቁጥጥር ሥር በዋሉትና በመዝገብ ቁጥር 141356 ነሐሴ 22 ቀን 2005 ዓ.ም. በእነ አቶ መላኩ ፈንታ የክስ መዝገብ የተካተቱት፣ የሙስና ተግባር ወንጀል ክስ የተመሠረተበት የኬኬ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ከተማ ከበደ፣ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተው አጠናቀቁ፡፡

የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ዶ/ር መረራ ለብይን ተቀጠሩ

ዓቃቤ ሕግ እንዲከላከሉ ብይን ይሰጥልኝ ብሏል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 01/2009 አንቀጽ 12(1) ሥር የተደነገገውንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዕርምጃ አፈጻጸም አንቀጽ 2(1)ን በመተላለፍ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለማስወገድ ሙከራ ወንጀል የተከሰሱት ዶ/ር መረራ ጉዲና ለብይን ተቀጠሩ፡፡

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ቅጣታቸው በሦስት ዓመት ቀነሰ

ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የሽብር ተግባር ወንጀል ፈጽመዋል በማለት ክስ መሥርቶባቸውና እንደ ክሱ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል ተብሎ የስድስት ዓመታት ከስድስት ወራት ጽኑ ቅጣት ተወስኖባቸው የነበሩት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ የተቀጡበት አንቀጽ ተቀይሮ ቅጣታቸው በሦስት ዓመት ዝቅ አለ፡፡

በአማራ ክልል ከነበረው ግጭት ጋር በተገናኘ የሽብር ተግባር ወንጀል ክስ የቀረበባቸው ችሎት በመድፈር ተቀጡ

አንድ ተከሳሽ ልብሱን በማውለቅ የደረሰበትን ጉዳት ለችሎት አሳይቷል ዳኛው በወልቃይት ጉዳይ ሊዳኙ አይገባም ያሉ ተከሳሾች መቃወሚያቸውን አስገብተዋል በጎንደር ከተማ፣ በተለያዩ በክልሉ ከተሞችና በባህር ዳር ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት በሽብር ተግባር ወንጀል ክስ ከተመሠረተባቸው 35 ተከሳሾች ውስጥ፣ አራቱ ችሎት በመድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ቅጣት ተጣለባቸው፡፡

በኖክ ነዳጅ ማደያና በሰላም ባስ ጋራዥ ላይ የቦምብ ጥቃት አድርሰዋል የተባሉ ተከሰሱ

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙት በኖክ ነዳጅ ማደያና በሰላም ባስ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ጋራዥ ላይ ቦምብ በመጣል ጉዳት አድርሰዋል የተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች፣ ዓርብ ኅዳር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

አቶ በቀለ ገርባ በዋስትና ጉዳይ ላይ ለሰበር ሰሚ ችሎት መልስ ሰጡ

የተከሰሱበት የሽብር ተግባር ወንጀል በመደበኛ ወንጀል የተቀየረ ቢሆንም፣ የዋስትና መብት የተነፈጋቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ ዋስትናቸውን ላገደው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ምላሻቸውን ሰጡ፡፡

ክስ የተመሠረተባቸው የወልቃይት ሕዝብ ማንነት አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በዳኛ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ፍርድ ቤቱ ተቃውሞአቸውን በጽሑፍ እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል በሽብር ተግባር ወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ ወይም ፍትሕ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ሰኞ ኅዳር 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ለማየት ከተሰየሙት ሦስት ዳኞች መካከል በአንደኛው ዳኛ ላይ ተቃውሞአቸውን አሰሙ፡፡

አቶ መላኩ ፈንታ አፋጣኝ ውሳኔ ለማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ አልጠብቅም አሉ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ አራት ዓመት ከሰባት ወራት ሲታሰሩ የፍትሕ ፍንጭ ስላላሳያቸው ፈጣሪያቸውንም እንደሚጠራጠሩ ገልጸው፣ የተፋጠነ ውሳኔ ማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ እንደማይጠብቁ ተናገሩ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ክስ ተመሠረተባቸው

96.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ እንዲከፍሉ ጥያቄ ቀርቧል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በገቡት ውል መሠረት ግዴታቸውን አልፈጸሙም ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በሁለቱም ላይ የፍትሐ ብሔር ክስ የመሠረተው ሲንጋፖር የሚገኘው ዊልማር ትሬዲንግ ቻይና ፒቲኤ ሊሚትድ ነው፡፡