Skip to main content
x

ለሕገ መንግሥት ሕልውና የሕገ መንግሥታዊ ማሻሻያ ሚና

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀበትን 23ኛ ዓመት የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በማክበር በአፋር ክልል ዋና ከተማ በሆነችው በሰመራ ባለፈው ዓርብ ኅዳር 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ተከብሯል፡፡ በ1987 በኅዳር ወር ፀድቆ በዚያው ዓመት በነሐሴ ወር ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

ስለዳኝነት ሥልጣን የሰበር ውሳኔዎችና ፍትሕ የማግኘት መብት

የፍትሕ ተደራሽነት መብት የሚያጠነጥነው ፍትሕ በሚፈልገው ሰው ዙርያ ነው፡፡ የፍትሕ ተደራሽነት ሲባል አንድ ነጠላ የፍትሕ ዘሃ ላይ ብቻ ሙጥኝ ያለም አይደለም፡፡ ይልቁንም ፍትሕ የሚፈልገው ሰው መብቱን በማስከበር ረገድ ተገቢ የሆነ እልባት ለማግኘት የሚከተለውን ሥርዓትና ሒደት በሙሉ ያካልላል፡፡

የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ውሳኔዎች ሕጋዊነታቸውና ሕገ መንግሥታዊነታቸው ሲፈተሹ

መኖሩ ጭምር በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ ሊባል በሚችል መልኩ በቅርቡ የታወቀውና የተለያዩ ውሳኔዎች ያሳለፈው ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በብዙ ሰዎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል፡፡ ይህንን ግርታ ያስከተለው ምክር ቤት ሕጋዊ መሠረት ምን እንደሆነ መቃኘት እንዲሁም ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ከሕገ መንግሥቱ ጋር የመስማማት ወይም አለመስማማታቸውን መፈተሽ የዚህ ጹሑፍ ትኩረት ነው፡፡

ተለዋዋጩ የፌዴራል ድጎማ በፌዴራል ሥርዓቱ ላይ የሚኖረው አንድምታ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የፌዴራል መንግሥት ለክልሎች የሚሰጠውን ድጎማ የትኛው ክልል ምን ያህል ሊያገኝ እንደሚገባ ለመወሰን የሚረዳውን ቀመር እያሻሻለ መሆኑን ከመገናኛ ብዙኃን ሰምተናል፡፡ ቀመሩ በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ኮሚቴዎች እየተጠና ተከልሷል፡፡ የኮሚቴዎቹን የጥናት ውጤትም መሠረት በማድረግ ምክር ቤቱ የተለያዩ ቀመሮችን አጽድቋል፡፡

የፖሊስ ተቋማት አወቃቀር ሕግጋትና እንከናቸው

የፖሊስ ሥልጣንና አወቃቀር፣ የፌዴራልና የክልሎች የፌዴራል የፖሊስ ኃይል የማቋቋም ሕገ መንግሥታዊ ሥልጣን፣ የፖሊስ ኃይሎቹ ስያሜና የመሳሰሉት ጉዳዮች ለሚዲያዎች መነጋገሪያ መሆን ከጀመሩ ሰንብተዋል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የፖሊስ ተቋማቱ ካሉባቸው መዋቅራዊ ቸግሮች በመነሳት የሰብዓዊ አያያዝና ሕገ መንግሥቱ ላይ ያላቸውን አንድምታ በአጭሩ እንቃኛለን፡፡

የብሮድካስት አገልግሎት ሕግና አተገባበር ለፌ ወለፌነት

ሰሞኑን የመገናኛ ብዙኃን አጀንዳ ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ራሱ የመገናኛ ብዙኃን አጠቃቀም የሚመለከት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የመንግሥት ባለሥልጣናት በፌስቡክ ገጻቸው የሚያሰራጯቸው መልዕክቶችና የሬዲዮና የቴሌቪዥን ሥርጭት ዋነኛ አጀንዳዎች ሆነዋል፡፡ የቴሌቭዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎቹ የመንግሥትንም የግልንም የሚመለከቱ ናቸው፡፡

በከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች በዋስ የመለቀቅ መብት  ከሕገ መንግሥቱ አንፃር እንዴት ይታያል?

በተሻሻለው የፀረ ሙስና ልዩ ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 434/97 ዓ.ም. ማናቸውም ከአሥር ዓመት በላይ በሚያስቀጣ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሰው በዋስ የመለቀቅ መብት እንደሌለው ይደነግጋል፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19(6) ላይ ቃል ለቃል እንደሚከተለው ተደንግጓል፤ “የተያዙ ሰዎች በዋስ የመፈታት መብት አላቸው፡፡ ሆኖም በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ላለመቀበል ወይም በገደብ መፍታትን ጨምሮ በቂ የሆነ የዋስትና ማረጋገጫ እንዲቀርብ ለማዘዝ ይችላል፡፡”

ተፈናቃይ ዜጎች ካሳ የማግኘት መብትና የመንግሥት ፍትሐ ብሔር ተጠያቂነት

በየትም አገር ቢሆን ዜጎች በተለያዩ ሕግጋት ጥበቃ የተደረገላቸው ወይም ከሕግ የሚመነጩ ሥፍር መብቶች እንደሚኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ መብቶቻቸውንም ለማስከበር ሲባል ተቋማት የመኖራቸውም ጉዳይ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ የመብት ጥሰት ባጋጠመ ጊዜ ማን ምን ማድረግ እንዳለበትም ተግባርና ኃላፊነትን የሚዘረዝር ሕግ መኖሩ አይቀሬ ነው፡፡

ሕገ መንግሥታዊ ዴሞክራሲን ለማሻሻል የቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት ተግዳሮቶች

ሕገ መንግሥቱ እንደ መገለጫ ወይም ባሕርይ በማድረግ ከወሰዳቸው አንዱ ዴሞክራሲያዊ መሆን ነው፡፡ ዴሞክራሲያዊ መሆኑ የሚታወቀው ደግሞ አገሪቱ ሉዓላዊ የሥልጣን ባለቤቶች የሆኑት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ራሳቸው በቀጥታ ወይንም በመረጧቸው ተወካዮች አማካይነት ሲሳተፉ፣ ሲወስኑና ሲወከሉ ነው፡፡