Skip to main content
x

ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት የአገሪቱን ፖለቲካዊ ችግሮች ይፈታል?

በ2008 ዓ.ም. ከተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣና አለመረጋጋት በኋላ በተከፈተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ንግግር ለማድረግ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር)፣ የአገሪቱን የምርጫ ሥርዓት እስከ ማሻሻል የሚደርስ ተሃድሶ መንግሥት እንደሚያከናውን ቃል ገብተው ነበር፡፡

‹‹ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትን የመጠበቅ ጉዳይ የማይገረሰስ የኢሕአዴግ መርህ ነው›› ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ

አፈ ጉባዔ አባዱላ የድርጅቱን ውሳኔ የመቀበል ግዴታ አለባቸው ብለዋል በአገሪቱ ከሚታዩ የፖለቲካ ክስተቶች በተቃራኒ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አሁንም ጥብቅ የሆነውን ዴሞክራሲያዊነቱን ጠብቆ እንደሚገኝ፣ ይህንንም ማዕከላዊነት ጠብቆ የማቆየት ጉዳይ የማይገረሰስ የገዥው ፓርቲ ምሰሶ እንደሆነ የፓርቲው ሊቀመንበርና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አስታወቁ፡፡

ፓርቲዎች በምርጫ ሥርዓቱ የመቶኛ ድርሻ ስምምነት ላይ ደረሱ

ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና የአገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድርድር ፓርቲዎቹ የአገሪቱ የምርጫ ሥርዓት ቅይጥ እንዲሆኑ በመስማማታቸው፣ 80 በመቶው በአብላጫ 20 በመቶው ደግሞ በተመጣጣኝ እንዲሆን ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

አገር የግለሰቦች መፈንጫ አትሁን!

የሕግ የበላይነት ባለበት ማንም ሰው ከሕግ በላይ መሆን አይችልም፡፡ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ሕግ ሲጥሱና ራሳቸውን ከሕግ በላይ ሲያደርጉ ግን አገርን ያመሰቃቅላሉ፡፡ ሕገወጥነት እንዲስፋፋና ሥርዓተ አልበኝነት እንዲነግሥ ያደርጋሉ፡፡ በሕገ መንግሥት አማካይነት የቆመ ሥርዓት ሳይቀር ከማፈራረስ አይመለሱም፡፡

ሰንደቅ ዓላማን የጋራ የማድረግ ፈተና

ሰንደቅ ዓላማ የአገራዊ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ትዕምርት (ምልክት) ነው፡፡ ሁለት አገሮች ወደ ጦርነት ወይም ወደ ጠብ ሲገቡና ዜጎች ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሚያደርጓቸው የተቃውሞ ሠልፎች ላይ ባንዲራ ማቃጠል በፊት በፊት እንደ ፋሽን ይታይ ነበር፡፡

በሴራ ፖለቲካ አገር አይታመስ!

ግልጽነት በሌለበት አገር በርካታ ብሔራዊ ጉዳዮች ሚስጥር ይሆናሉ፡፡ ሚስጥራዊነት በበዛ ቁጥር እውነቱን ከሐሰት፣ ተጨባጩን ከምናባዊው መለየት ስለማይቻል መላምቶች ይበዛሉ፡፡ የመረጃ ፍሰቱ የተገደበ ስለሚሆንም ሐሜትና አሉባልታ የበላይነቱን ይይዛሉ፡፡ አሁን በኢትዮጵያ የተንሠራፋው ችግር ይህ ነው፡፡

ከአገርና ከሕዝብ በላይ ምንም ነገር የለም!

የአገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካ ትኩሳት ከአገርና ከሕዝብ ዘለቄታዊ ህልውና ጋር ሲነፃፀር፣ በግራ መጋባትና በውዥንብሮች መሞላቱ ግልጽ ነው፡፡ በተለይ በገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች መካከል መቃቃር ተፈጥሯል ተብሎ በአደባባይ መሰማት ከጀመረ መሰነባበቱ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ በቀናት ልዩነት ውስጥ የድርጅቱ ነባር አመራሮች ከያዙት ኃላፊነት በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸው መሰማቱ በድርጅቱ ታሪክ አዲስ ቢሆንም፣ በአባል ድርጅቶች መካከል የነበረው መስተጋብር ግን እንደ በፊቱ እንዳልሆነ ግን ግልጽ እየሆነ ለመምጣቱ ሌላው ማሳያ ነው፡፡

ደኢሕዴን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመፍታት ችግሮች እንደነበሩበት ገለጸ

የኢሕአዴግ አባል ድርጅት የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን)፣ ባለፈው ዓመት በክልሉ ውስጥ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን  በወቅቱ የመፍታት ችግሮች እንደነበሩበት አስታወቀ፡፡

ሁለንተናዊ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታት ፈተና

ባለፉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ቀውስ ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከ2008 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 2010 ዓ.ም. መግቢያ ድረስ በአገሪቱ እየተከሰተ ያለው ተቃውሞና ግጭት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ወደ ሥልጣን ከመጣ ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ በአገሪቱ ለረጅም ጊዜ ተቃውሞና ግጭት ሲከሰት ይኼ የመጀመሪያው እንደሆነ፣ የፖለቲካ ተንታኞች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡