Skip to main content
x

የት ይደርሳል የተባለ የት ተገኘ ነው ያሉት?

እነሆ መንገድ። ከሃያ ሁለት ወደ ካዛንቺስ፡፡ ጎዳናው እያደር ይጠባል፡፡ መንገደኛው እርስ በርሱ እየተጠላለፈ ይራኮታል፡፡ ባለማወቅ ይሁን በሌላ ማፈር ተረስቷል፡፡ በጡንቻ ጥንካሬ፣ በትከሻ ስፋት ካልሆነ በቀር የሚከባበር ቀንሷል፡፡ ይኼኛው መንገድ ትናንት የሄድኩበት ነው? ብለው ዘወር ሲሉ የሚያዩት የሚተን ትዝታ ነው። ትናንትና እዚያ ጥግ ቆመን እውነት አውርተናል? ብለው የመተከዝ ዕድል ሳይኖርዎ በትንሹ ሦስት አልፎ ሂያጅ ይገጭዎታል፡፡

አልበዛም እንዴ?

እነሆ መንገድ! ከሽሮ ሜዳ ወደ አራት ኪሎ። ‹‹አንተ ልጅ ይኼን የማጅራት ገትር ክትባት ተከትበሃል ለመሆኑ?›› ሾፌሩ ነው ወያላውን የሚጠይቀው። ‹‹ኤድያ እኛ እኮ የሚያስፈልገን የማጅራት መቺ ክትባት ነው!›› ብለው ጣልቃ የሚገቡት ደግሞ አንዲት ወይዘሮ ናቸው። ‹‹ምነው እማማ? የማጣት ልክፍቱን ሴት ሲላከፍ የሚያባርር የሚመስለው በእርስዎም ደረሰ እንዴ?›› ሾፌሩ ሊግባባቸው ይጀምራል። ‹‹ተወኝ እስኪ! እኔ የማወራው ስለገበያው ነው። ምን ይለክፈኛል እንደ ቀትር ጋኔን ያላልኩትን አለች ሊለኝ፤››

‹እስኪ ከብለል ከብለል . . .›

እነሆ መንገድ ከመሪ ወደ መገናኛ ልንጓዝ ነው። ‹‹ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቆጣጠር የውይይት መድረክ ተዘጋጀ፤›› ይላል የሬዲዮ ጋዜጠኛው። ‹‹ዝንት ዓለም ውይይት ዝንት ዓለም ስብሰባ! በስብሰባ ለእግረኛ ቅድሚያ ይሰጣል እንዴ? ወይስ ፍጥነት ተቆጣጥሮ ይሾፈራል? ሁሉም ችግር የሚፈታው በክትባትና በወሬ ይመስላቸዋል፤›› ይላሉ አንድ አዛውንት። ‹‹እና እርስዎ ምን መደረግ አለበት ነው የሚሉት?›› አላቸው ገና ተሳፍሮ አጠገባቸው የተቀመጠ ወጣት። ‹‹ዘመኑ የፍጥነትና የውድድር ነው እያልን ፍጥነትና ውድድርን ሁሉ ነገር ውስጥ ማስገባት መተው፡፡

እንተላለፍ እንጂ?

እነሆ ጉዞ ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ። ምድር ትውልድን በትውልድ እየተካች የደከመውን በሞት ሸኝታ ለጋውን እያሳደገች ፋታ አሳጥታ ታራውጠናለች። ተስፋ አይሞትምና እውነት ለመሰለን ሁሉ እየደከምን በባዶ እንደመጣን በባዶ እስክንሸኝ እንደክማለን። እርቃናችንን እንደመጣን እርቃናችንን እንቀበራለን።

ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ባንሰጣጥስ?

እነሆ መንገድ! ታክሲያችን በወሬና በጫጫታ ደምቃለች። ወያላችን ደጋግሞ ፀጥታ እያለ ተንሸራታቹን በር ይደልቀዋል። ‹‹ምንድነው ነገሩ? ቤተ መጻሕፍት የገባን መሰለው እንዴ ሰውዬው?›› ይነጫነጫሉ ሦስተኛው ረድፍ ላይ የተሰየሙ ወጣቶች። ‹‹ምናለበት አንዴ ወሬ ብንሰማ? ድምፅ ስጠው አቦ፤›› ወያላው ቀንድ ሊያበቅል ምንም አልቀረውም። ሾፌራችን የሬዲዮኑን ድምፅ ይጨምራል። ‹‹አሁን እኮ ጥያቄው ምርጫው ይራዘም? ወይስ አይራዘም ነው? አድማጫችን በዚህ ዙሪያ ምን ይላሉ?›› ጋዜጠኛው ይጮሃል።

ከባዶ ጭንቅላት ባዶ ኪስ ይሻላል!

እነሆ መንገድ! ከፒያሳ ወደ ሜክስኮ ልንጓዝ ነው። ሰው ብርቱው በመጓዝ ምኞቱ መንገድ አበጅቶ መራመድ አይታክተውም። ወዲያ ይመጣል ወዲያ ይሄዳል። የመገንባት ጥረቱ ሳይነጥፍ የማፍረስ ጥበቡም አይቅርብኝ እንዳለ በመንታ ማንነት ይወዛወዛል። “ታክሲ! ታክሲ!” ይጮሃል አንድ ሰው። ወደ መጨረሻው አካባቢ አንድ ጎልማሳ ያላማቋረጥ ስልክ እያወራ ነው።

ምነው ተናካሹ በዛ?

እነሆ መንገድ! እነሆ ጉዞ! ከወሎ ሠፈር ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። መንገድ አልቆ መንገድ ልንጀምር፣ ዕድሜ ጨርሰን ዕድሜ ልንቀጥል እንራመዳለን። ወያላው፣ ‹‹የሞላ ሁለት ሰው›› እያለ ይጮሃል። ‹‹ምንድነው የሚያወራው?›› አንዱ ተሳፋሪ ይጠይቃል። ታክሲው ባዶ ነበር። ‹‹የመዋሸትን መብት ለመንግሥት ብቻ የሰጠው ማን ነው? ትገቡ እንደሆነ!›› ግቡ ይላል ወያላው የሰውየውን መደናገር ግልጽ አደርጋለሁ እያለ ነገር ያወሳስባል።

ለመውጣት ግፊያ ለመውረድ ግፊያ!

እነሆ ጉዞ እነሆ መንገድ! ከጀሞ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። መስኮቶች ተከፋፍተዋል። በተከፈቱት መስኮቶች ተሻግሮ እየነፈሰ የሚገባው አየር ግን የተዘጋ ነው። እንዲያ ነው! “የቆጡን እናወርዳለን ብለው የብብታችንን አስጣሉን እኮ እናንተ?” ይላል አንዱ። ደንዳና ሰውነቱ መተማመኛ ዛኒጋባ እንዳጣ ያስታውቅ ነበር። ‘እንዴት? እነማን  ናቸው እነሱ?’ መሰል ተመሳሳይ ጥያቄዎች የሚጠይቀው ሰው አጠገቡ የለም። ውለውም ሆነ አድረው ተጠያቂዎቹና ተተችዎቹ ተመሳሳይ ናቸው። በምንመላለስበት ጎዳና ሁሉም የሰው ጉድፍ ጠቋሚ ነው።

እንዲያው በጨረፍታ ልባችን አይምታ!

እነሆ መንገድ ከመገናኛ ወደ አያት። ‹‹የቆጡን እናወርዳለን ብለው የብብታችንን አስጣሉን እኮ እናንተ!›› ይላል አንዱ። ደንዳና ሰውነቱ መተማመኛ ዛኒጋባ እንዳጣ ያስታውቅ ነበር። ‘እንዴት? እነማን ናቸው እነሱ?’ መሰል ተመሳሳይ ጥያቄዎች የሚጠይቀው ሰው አጠገቡ የለም። መንገዱ ተወጥሮ ከአሁን አሁን ተነፈሰ እያስባለ ያራምደናል።

አዋቂ ሲጠፋ ታዋቂ ይበዛል!

እነሆ ከፒያሳ ወደ አራት ኪሎ ልንጓዝ ነው። ዕቅድ በማይገዛው አንዳንዴም ድካም መሪውን ጨብጦ የማስተዋል ቀልብ በሚከዳን ጎዳና ላይ ዛሬም በእንፉቅቅ እንጓዛለን፡፡ ሳይጀመር የሚያልቀው፣ ሳይወጠን የሚከሽፈው፣ ሳይታለም የሚፈታው ነገር ብዛት የእኔ ቢጤውን አዝሎታል። ዝለቱ ይመስላል ጎዳናውን የሽሙጥና የትችት አውድማ ያደረገው።