Skip to main content
x

ሕገ መንግሥታዊነትን የማረጋገጥ ጫናና ዝግጁነት

የ1987 ዓ.ም. የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ሥራ ላይ ከዋለ 22 ዓመታት አለፉ፡፡ ሕገ መንግሥቱ ከመሠረታዊ መብቶች ጋር ስምሙ የሆነ የሕግና የፖለቲካ ሰነድ እንደሆነ ብዙዎች ቢስማሙም፣ በተግባር ላይ ስለመዋሉ ወይም ሕገ መንግሥታዊነቱ ስለመረጋገጡ፣ ወይም ለሰብዓዊ መብት መረጋገጥ ዋስትና የመሆኑ ጉዳይ ግን አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ሜቴክ የያዛቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች መጓተት የፈጠረው ውዝግብ

• ‹‹አሻጥሮች እየተፈጸሙብኝ ነው›› ሜቴክ • ‹‹ይህንን መስማት ያማል›› ስኳር ኮርፖሬሽን • ‹‹ሕዝቡም እምነት እያጣ ነው እኛም ወደ መሰልቸት ደርሰናል›› የፓርላማ አባል የኢትየጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) የያዛቸው ግዙፍ የስርኳና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተት ላለፉት ዓመታት ሲፈጥር የነበረው ውዝግብ አሁንም መፈታት ባለመቻሉ፣ የፕሮጀክቶቹ ባለቤቶች በሆኑት የመንግሥት ተቋማትና በሜቴክ መካከል ውዝግቡ በድጋሚ ባለፈው ሳምንትም ተደምጧል፡፡

አቶ መላኩ ፈንታ አፋጣኝ ውሳኔ ለማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ አልጠብቅም አሉ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ፣ አራት ዓመት ከሰባት ወራት ሲታሰሩ የፍትሕ ፍንጭ ስላላሳያቸው ፈጣሪያቸውንም እንደሚጠራጠሩ ገልጸው፣ የተፋጠነ ውሳኔ ማግኘት እንጂ ፍትሐዊ ፍርድ እንደማይጠብቁ ተናገሩ፡፡

ረቂቅ የሊዝ አዋጁ አዳዲስ ለውጦች ይዟል

አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች መሬት በምደባ የማቅረብ ጉዳይ አልለየለትም የሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲያፀድቀው ወረፋ የተያዘለት የከተማ ቦታ በሊዝ ስለመያዝ የወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 በድጋሚ ለማሻሻል የተዘጋጀው ረቂቅ፣ ቀደም ሲል ያልነበሩ አዳዲስ ለውጦች ተደርገውበታል፡፡

ግብፅ ለህዳሴ ግድቡ ጥናት መነሻ የቅኝ ግዛት ስምምነት እንዲሆን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ተደረገ

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተፅዕኖ ግምገማ፣ የውኃ ሙሌትና አለቃቀቅ ጥናት ላይ ድርድር እያደረጉ ቢሆንም፣ ግብፅ የቅኝ ግዛት ዘመኑን እ.ኤ.አ. የ1959 ስምምነት ግድቡ ሊያመጣ ለሚችለው ጉዳት መነሻ እንዲሆን ያቀረበችው ጥያቄ በኢትዮጵያና በሱዳን ውድቅ ተደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ክስ ተመሠረተባቸው

96.6 ሚሊዮን ብር ዕዳ እንዲከፍሉ ጥያቄ ቀርቧል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አልሳም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በገቡት ውል መሠረት ግዴታቸውን አልፈጸሙም ተብለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ በሁለቱም ላይ የፍትሐ ብሔር ክስ የመሠረተው ሲንጋፖር የሚገኘው ዊልማር ትሬዲንግ ቻይና ፒቲኤ ሊሚትድ ነው፡፡

የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለማስገደል ሙከራ አድርገዋል የተባሉት የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት አዲስ ክስ ቀረበባቸው

አራጣ ማበደርና ሌሎች የተለያዩ 39 የወንጀል ድርጊቶችን ፈጽመዋል ተብለው ክስ የተመሠረተባቸው የአዲስ ቪው ሆቴል ባለቤት፣ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮችን የማስገደል ሙከራ ፈጽመዋል ተብለው አዲስ ክስ ቀረበባቸው፡፡

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበር ፕሬዚዳንት ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ

ኢትዮጵያና ኤርትራን ለማደራደር የተነሳው የምሥራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባዔዎች ማኅበር (አሜሰያ) /Association of Member Episcopal Conferences in Eastern Africa (AMECEA)/፣ ፕሬዚዳንትና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ኤርትራ እንዳይገቡ ታገዱ፡፡

የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ችግሩ መፍትሔ ሲያገኝ ወደ ቀድሞ ዩኒቨርሲቲያቸው እንደሚመለሱ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የሁለቱ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየክልሎቻቸው እንዲመደቡ የተደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እንጂ በክልሎች ጣልቃ ገብነት አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌቴ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡