Skip to main content
x

ስሜታዊነት የሰላም ጠንቅና የአዕምሮ እንከን ነው

በዚህ ጽሑፍ ስሜታዊነት የሚለው ቃል ከራሳችን በስተቀር የተለየ አስተሳሰብ፣ አካሄድ፣ ፍልስፍና፣ አስተምህሮት ያላቸውን ባለመቀበል፣ በመጥላት፣ በማጥላላት፣ በዚህም ምክንያት በሚቻል መንገድ ሁሉ ተቀባይነት እንዳያገኙ ተፅዕኖ በማሳደር በአንደበት፣ በገጽታ፣ በድርጊት፣ በጽሑፍ፣ የሚገለጥ ባህርይ ነው፡፡ ይህ ስሜታዊነት በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት ሲሆን፣ አንዱ ጠባብነት ነው፡፡

ታማሚዋ ኢትዮጵያ አገራችን የሚታደጋት ባለመድኃኒት ትሻለች

አንድ የኦሮሚፋ ተረት ከሞላ ጎደል እንዲህ ይነገራል፡፡ አንድ ፈሪ ሰው ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆነው መንገድ ይጓዛሉ፡፡ በመንገድ ላይ መሽቶባቸው ካሰቡበት ቦታ ሳይደርሱ ጫካ ውስጥ ለማደር ይገደዳሉ፡፡ ጫካ ደግሞ አውሬ አያጣውምና ፈሪው ከአውሬ ራሱን ለመደበቅ እኔ የምተኛው ከመሀላችሁ ነው በማለት ጓደኞቹን ከግራና ከቀኝ አድርጎ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፡፡ ሌሊት ላይ የተፈራው ደርሶ ጅብ ይመጣና በግርጌ በኩል መሀል የተኛውን ፈሪውን ከእግሩ ይጀምረዋል፡፡ ፈሪው እየተበላና እየሞተም ዘራፍ አስጥሉኝ ብሎ ጮክ ብሎ መናገሩንም ይፈራና ጥርሱን ነክሶ መበላቱን ይቀጥላል፡፡

እየተናጠ ካለው የዓረቡ ዓለም ምን እንማር?

የመካከለኛው ምሥራቅና የሰሜን አፍሪካ ቀጣና ከዛሬ ሰባት ዓመት ጀምሮ ነበር በተቃውሞ ሠልፎች፣ አመፆችና በተደራጁ የትጥቅ ትግል ሥልቶች እንደ አዲስ መናጥ የጀመረው፡፡ የእነዚህ እንቅስቃሴዎች ዋና ዓላማ ዜጐች በየአገሮቻቸው ጉዳዮች በባለቤትነት መንፈስ በመሳተፍ አምባገነናዊ ሥርዓቶችን ማስወገድ የነበረ ሲሆን፣ ስኬቱና ውጤቱ ግን አከራካሪ ሆኖ አሁንም ቀጥሎ ይገኛል፡፡ የዓረቡ ዓለም አብዮት እንቅስቃሴ ሲታወስ በፍጥነት ወደ አዕምሮ የሚመጡት አገሮች ቱኒዚያ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ የመንና ሶሪያ ሲሆኑ፣ ሌሎቹ አገሮች የተነሱባቸውን ሕዝባዊ ተቃውሞዎች በተለያዩ ዘዴዎች በማዳፈን ለጊዜውም ቢሆን ጋብ እንዲል አድርገዋቸዋል፡፡

የመንግሥትና የጋራ ቤቶችን ማን ይቆጣጠራቸው?

ብዙ ጊዜ የመንግሥት የሚባሉ ነገሮች ሁሉ የጋራ ንብረት ስለሆኑ እንደ ግል ይዞታ ባለቤት ያላቸውና የሚጠበቁ አይደሉም፡፡ እኛን በመሰሉ አገሮች ደግሞ ከሕዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ባህሉ ለጋነትና የእኔነት ስሜት አለመዳበር በመነሳት፣ እንዲሁም የሕዝቡ ንቅተ ህሊናም ስለሚገድብ የዜጎች የባለቤትነት መንፈስ ተዳክሞ መታየቱ አይቀርም፡፡ እንዲያውም አሁን አሁን እየመጣ ያለው መሻሻል መኖሩ እንጂ በነባሩ አስተሳሰብማ የጋራ ሀብት (የሕዝብ መጠቀሚያም ቢሆን) እንደ ባላንጣ ይዞታ የመቁጠሩ ችግር የከፋና የገነገነ ሆኖ መቆየቱ የታመነ ነው፡፡

የኢሕአዴግ ዕጣ ፈንታ በድርጅታዊ ፊዚክስ ዓይን

አንድ የሆነ ነገር ‘እንዴት ነው የሚሠራው?’ ብሎ መሠረታዊ መርሆች ላይ ለመድረስ መጣር ዘመን አመጣሽ አዲስ ፍላጎት ሳይሆን፣ የሰው ልጆች በዚህ ምድር መኖር ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ የነበረ ይመስለኛል። ሰዎች እሳትን ለመጀመሪያ ጊዜ ካዩበት ቅጽበት ምናልባትም እንዴት ነው የሚሠራው ብለው ከመጠየቃቸው በፊት አስቀድሞ የሌሎች ነገሮችን አሠራር እንዴትነት ሲጠይቁ ነበር።

ዓባይና የካይሮ ዲፕሎማሲ

ባለፈው ሳምንት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳላኝ የተመራ ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን በግብፅ ካይሮ በመሪ ደረጃ ውይይት አድርጎ ተመልሷል፡፡ ይኼ ምክክር ቀደም ሲል መርሐ ግብር የተያዘለት በናይል ውኃ አጠቃቃምና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዊ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ በተጨማሪም በአገሮቹ መካከል መተማማንና ትብብርን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጸዋል፡፡

ፌዴራሊዝምና የሲቪል ፖለቲካ እንቅስቃሴ

በአገራችን ኢትዮጵያ፣ በተለይም የፌዴራል ሥርዓቱ በተግባር ላይ ከዋለ በኋላ ባሉ ዓመታት፣ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ አንዳንድ ጊዜ ሕዝባዊነት ያላቸው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በመንግሥት መሥራቹ ፓርቲ ውስጣዊ ግጭት ምክንያት የተነሱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ይስተዋላሉ፡፡ በ1960ዎቹ አብቦ ቀጥሎም በተሰነዘረበት ያልተመጣጠነ ዕርምጃ ከስሞ የቆየው የሲቪል ፖለቲካ እንቅስቃሴም፣ ከወታደራዊው መንግሥት መውደቅ በኋላ እንደገና ሕይወት ዘርቶ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ የራሱን ሚና እየተጫወተ አሁን ያለንበት ደረጃ ደርሰናል፡፡

በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው መግለጫ ላይ አንዳንድ ነጥቦች

አራቱን ብሔራዊ ድርጅቶች በማጣመር የተዋቀረው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ድፍን 17 ቀናትን እንደፈጀ በተነገረለት ታሪካዊ ስብሰባው ማግሥት፣ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን የዳሰሰ አንድ ሰሞናዊ መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግለጫው ትኩስና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች አማካይነት በቅብብሎሽ ላይ ያለ በመሆኑ ለብዙ አንባቢያን አዲስ እንደማይሆንባቸው ከወዲሁ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

በዩኒቨርሲቲዎቻችን ፀጥታን ለማስፈን ሳይሆን ሰላምን ለማረጋገጥ  እንትጋ!

ሰላምና ፀጥታ ደጋግመን የምንሰማቸውና የምንጠቀምባቸው ቃላት ናቸው። በመካከላቸው ልዩነት የሌለ እስከሚመስለን ድረስ አጣምረን እንጠቀምባቸዋለን። በዚህ ጽሑፌ በሁለቱ ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት ለመጠቆም እሞክራለሁ። ይህን የማደርገው ግን ከወቅታዊ አገራዊ ሁኔታችን በመነሳት በዩኒቨርሲቲዎቻችን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመዳሰስና መፍትሔ በሚያሻቸው ጉዳዮች ላይ የግል አስተያየቴን ለማስፈር እንጂ፣ በቃላቱ አጠቃቀም ላይ አቃቂር ለማውጣት ወይም ደግሞ የትርጉም ንድፈ ሐሳብ ለማቅረብ አይደለም።

ሚዛናዊ ተራማጅነት

የተሻለ፣ ከዛሬው ይልቅ መልካም፣ ያሁኑን ያህል ያልከፋ፣ ክፋቱና መጥፎነቱ የቀነሰ፣ በጎ ጎኑና መልካምነቱ የላቀ  ማኅበረሰብ እንፈልጋለን፡፡ ነገሮችና ሁኔታዎች በጐና አዎንታዊ በሆነ መልክ እንዲለወጡ እንፈልጋለን፡፡ የተሻለ ቀን፣ የተሻለ ማኅበረሰብና አገር፣ መልካም የሆነ ለውጥ እንዲመጣ መፈለግ ለወጣቶችና የዛሬው ቀንና ሁኔታ ላልተመቸው ሁሉ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ የተጐሳቆለ፣ ሆድ የባሰውና የከፋው ለውጥ ቢፈልግ አይገርምም፡፡