Skip to main content
x

የሳምንቱ ገጠመኝ

በዚህ ጉደኛ ዘመናችን ውስጥ የምናስተውላቸው አንዳንድ ገጠመኞቻችን ከዘመናት በፊት ጥለን የመጣናቸውን የፊውዳሎች የአኗኗር ዘይቤ ያስታውሱናል፡፡ መሬት በጥቂት ፊውዳሎች ተይዞ ብዙኃኑ አርሶ አደሮች ከባርነት ባልተናነሰ ሁኔታ ገባር በሆኑበት በዚያ ዘመን፣ ሹመት ፈላጊ የዘመኑ ሰዎች የንጉሣዊያኑንና የገዢዎችን ችሎቶች ያጣብቡ ነበር፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከሜክሲኮ አደባባይ የተሳፈርኩበት ታክሲ ወደ ፒያሳ እያመራ ነው፡፡ ታክሲውን እጭቅ አድርገው የሞሉት ወያላና ሾፌር በዕድሜ ተቀራራቢ በመሆናቸው በማይገባን የንግግር ዘዬ እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

የዛሬ ሁለት ዓመት የኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል ከመድረሱ በፊት አንድ ወር ገደማ ቀደም ብዬ፣ አክሱምን ለመጀመርያ ጊዜ ስረግጥ የነበረኝን ስሜትና እጅግ መልካም የሆኑ ትውስታዎቼን በሌላ መጽሔት በቅርብ ጊዜ ጽፌ ነበር፡፡ ይሁንና ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ የሪፖርተርን ድረ ገጽ ሳማትር ‹‹አስተያየት›› በሚለው ዓምድ ሥር ስለዓደዋና አካባቢው የተጻፈውን፣ ‹‹ጆሮዬን ወይስ ዓይኔን?›› በሚል ርዕስ በአንዲት ኢትዮጵያዊት የተጻፈውን እውነተኛ ትዝብት በማንበቤ ምክንያት ነው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

የዚህ ገጠመኝ ጸሐፊ መኖሪያዬ ኮተቤ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡ እዚህ ሠፈር ተከራይቼ ከገባሁ አንድ ዓመት አልፎኛል፡፡ የምኖርበት ግቢ የባለንብረቶቹን ጨምሮ ሰባት ቤቶች ይገኙበታል፡፡ የአባወራው ተለቅ ያለ ቪላ ቤትና መደዳውን የተሠሩ ስድስት ባለ ሁለት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች ማለት ነው፡፡ ከእኔ በስተቀር ሁሉም ተከራዮች ባለትዳሮች ናቸው፡፡ የእኔ ወንደላጤ መሆን የማይመቻቸው አባወራው ባገኙኝ ቁጥር ማግባት እንዳለብኝ ያስገነዝቡኛል፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በመስከረም 1998 ዓ.ም. የመስቀል በዓል ሲከበር በመስቀል አደባባይ ተገኝተን ነበር፡፡ በዚያን ወቅት የአዲስ አበባ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ኢሕአዴግን በምርጫ ካርድ ያሰናበተበት ጊዜ በመሆኑ፣ በኢሕአዴግና በተቃዋሚዎች ንትርክ የተነሳ አዲስ አበቤዎች አኩርፈን ስለነበር የመስቀል በዓል ሲከበር ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ ተቃውሞ አጋጠመ፡፡

የቃል ኪዳን ካርታ

ለዚህ ጽሑፍ መነሻ ከሆኑ ነገሮች ዋነኛው የዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአደራ ቃል ነው፡፡ መጀመርያ ቃል ነበር እንዲል ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዳግማዊ ምኒልክ ግንቦት 10 ቀን 1901 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስመልክቶ ያስተላለፉት ቃልኪዳን ነበር፡፡ የቃል ኪዳኑ መልዕክት የንጉሡን ብልኃት፣ ጥበብና የመሪነት ሚናቸውን የሚያሳይ ነው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከሳምንት በፊት በአንዱ ቀን በማለዳ ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚያመራው ሐይገር ባስ ውስጥ ተሳፈርኩ፡፡ የመጨረሻው መቀመጫ ላይ በስተቀኝ በኩል ያለው መስኮት አጠገብ ከመቀመጤ፣ አንዲት ሴት አራስ ሕፃን ታቅፋ አጠገቤ ቁጭ አለች፡፡ ዞር ብዬ ሳያት በጣም ለጋ ወጣት ናት፡፡ ከ20 ዓመት አይበልጣትም፡፡ ተመቻችታ ከተቀመጠች በኋላ፣ ‹‹ተመስገን!›› የሚል የምሥጋና ቃል አሰማች፡፡ አሁንም ዞር ብዬ ሳያት ያቺ ለጋ ወጣት ፊቷ ከመገርጣቱም በላይ ድካም ይታይባታል፡፡ ሕፃኗ እናቷ እቅፍ ውስጥ ሆና ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ናት፡፡ እናቲቱ በእጇ ይዛ የነበረውን የተቋጠረ ኩርቱ ፌስታል እግሮቿ መሀል ካሳረፈች በኋላ አሁንም ‹‹ተመስገን!›› አለች፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ባለፈው ሳምንት በሆቴል አዳራሽ የተዘጋጀ የሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ የሚታደም አንድ ዘመዴን አድርሼው እየወረደ ሳለ፣ አንድ ረዥም ቀይ ሰው በእጁ ወደ እኔ አቅጣጫ እያመላከተ ይጣራል፡፡ እኔ ደግሞ ዘመዴን ከመኪናው አስወርጄው እየተሰናበትኩት ነው፡፡ ይኼ የማላውቀው ሰው ማን ነው? ወይስ ሌላ ሰው ነው የሚጣራው? ገልመጥ ገልመጥ ብል ከእኔ በቀር ማንም የለም፡፡ ሰውዬው በረዥም ቅልጥሙ እየተሳበ መጥቶ መኪናዬ አጠገብ ቆሞ መሳቅ ይጀምራል፡፡ ይኼ ደግሞ ማን ነው? ግራ እንደተጋባሁ ገብቶት ኖሮ በጎርናና ድምፁ፣ ‹‹ዓምደ ወርቅ ረሳኸኝ እንዴ?›› ሲል በዕውኔ ሳይሆን በህልም ውስጥ ያለሁ መሰለኝ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በጎልማሳነቴ ዘመን የማያቸው በርካታ ነገሮች ከድሮው የወጣትነቴ ዘመን ያን ያህል ፈቅ ባለማለታቸው በጣም ይገርመኛል፡፡ ለምሳሌ ድሮ ተማሪዎች በነበርንበት ጊዜ ‘የተማሪ ተንኮል’ ውጤት የሆኑ በርካታ ድርጊቶች ይፈጸሙ ነበር፡፡ አንደኛው የሆነ ነገር ፈጥሮ ማስወራት ነው፡፡ አንድ ጊዜ የ11ኛ ክፍል የእንግሊዝኛ ቋንቋ አስተማሪያችን ክፍል ውስጥ ፈተና እየሰጡን ሳለ፣ ማን እንደ ጻፈው የማይታወቅ በአራት ማዕዘን ቅርፅ የተጻፈ ጽሑፍ ተሠራጨ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ጊዜው እንዲህ ሳይራቀቅ፣ ይቅርታ መላ ቅጡ ሳይጠፋ፣ ወላጆቻችን ኪሳቸው ውስጥ ሃያ ብር ካለ ዓለም አበቃላት ይባል ነበር፡፡ ያኔ ድሮ ያኔ፡፡ በተለይ በበዓል ሰሞን እኔ ነኝ ያለ ሙክት በአሥር ብር ተገዝቶ ተጎትቶ ሲመጣ የሠፈሩ ሰው የመጀመርያ ጥያቄ፣ ‹‹በስንት ብር ተገዛ?›› የሚል ነበር፡፡ በእርግጥ አሁንም ይህ ጥያቄ እንዳለ ነው፡፡ መልሱ ቢለያይም፡፡