Skip to main content
x

አትየኝ አልይህ ምን ይሉት ፈሊጥ ነው?

​​​​​​​ሰላም! ሰላም! የተወደዳችሁና የተመረጣችሁ ውድ ወዳጆቼ እንደምን ቆያችሁልኝ፡፡ እኔማ ይኸው ባሻዬ እንደሚሉት፣ ‹‹የቆምነው በእግሮቻችን አይደለም፣ በእግዜሩ ምሕረት አንጂ፤›› ብለው ነበር፡፡ ልክ ብለዋል ባሻዬ፡፡ ሺሕ ዓመት ኑሩልን፡፡

ራስን ፈርቶ ሌላውን ተዳፍሮ ይቻላል እንዴ?

ሰላም! ሰላም! ከቁም ነገሩ ይልቅ የወሬና የአሉባልታ መሐንዲሱ ባሰብን እኮ? አይገርምም ግን! በአሉሽ አሉህ ተጠምደን እያደር ሲብስብን ምን ይሉኝ? ምን ይሉን? ምን ተባለች? ምን አደረገች? የሰው ሰው ግምገማ አገር ይገነባል እንዴ? የቸገረ ነገር እኮ ነው!

እስኪ እንወራረድ!

ሰላም! ሰላም! እንዴት ነው ገበያው? መልሱን አንዴ ያዙትና በአንድ ቀልድ’ እንንደርደር። ጎልማሳ አርሶ አደር ገበያ ሄዶ ፍየል ገዝቶ ወደ ቤቱ ማዝገም ይጀምራል። እንዳሁኑ ‹ሚሊየነር ልማታዊ አርሶ አደሮች› ሳናፈራ መሆኑን ልብ በሉልኝ። ታዲያ ፍየሉን በገመድ አስሮ ከኋላ ከኋላው እያስከተላት ይጓዛል።

መልሶ ማልማትስ አስተሳሰብን ነው!

ሰላም! ሰላም! ሰላም! በያላችሁበት ይሁን፡፡ በዚህ ክፉና ደግ እንደ ዘይትና ውኃ በተቀላቀሉበት ዘመን ሰላምን አስቀድመን ለጋራ ደኅንታችን ካላሰብን፣ እኔ ደላላው አንበርብር ምንተስኖት ሥጋት ይገባኛል፡፡ ይኼንን ሥጋቴን የምትጋራው ውዷ ባለቤቴ ማንጠግቦሽ (በእርግጥም አትጠገብም) ዓይኖቿን ወደ ሰማዩ ልካ ወደ ፈጣሪዋ ታንጋጥጣለች፡፡ አንደኛው የድለላ ሥራ ባልደረባዬ፣ ‹‹ነገረኞች በሚያንጓጥጡበት በዚህ ጊዜ ወደ ላይ ማንጋጠጥ ሳይሻል አይቀርም…፤›› እያለ ሥጋቴን ማባባስ ሲጀምር የማይታክተውን እግሬን ተንቀሳቀስ አልኩት፡፡

ነጥብ ማስቆጠርስ በሐሳብ ብልጫ ነው!

ሰላም! ሰላም! ሰሞኑን ውዷ ባለቤቴ ማንጠግቦሽ ማጉረምረም አብዝታለች። ‹‹ኧረ ምን ብናደርግ ይሻል ይሆን?›› የሚለው ካፏ አይጠፋም። ስወጣ ስገባ ‹‹ማንን ነው?›› እላለሁ። ‹‹ጊዜውን አታይም! እሱም ለነገር አዋጣ የተባለ መሰለበት እኮ!›› ትለኛለች። እኔ ደሞ ‹‹ጊዜው›› ባለችኝ ቁጥር ‘የእኛን ነው ወይስ መጪውን ነው?’ እያልኩ ድንግርግር ይለኛል። ምን ላድርግ በቀኝ እያሳየ በግራ የሚጫወተው መንገዱን ሲሞላው። የእኛ ሰው የምታውቁት ነው። ለምሳሌ አንዱ ባለፈው ሰሞን (ገና ታዳጊ ወጣት እኮ ነው ብታዩት) ‘ቪትዝ’ እያጋዛሁት ‹‹ይኸውልህ ባንተ ዕድሜ ባለንብረት የሚኮንበት ጊዜ ላይ ደረስን።

ማማጥስ አሁን ነው!

ሰላም! ሰላም! ያው እንደ ወትሮዬ ለጎጆዬ መሞቅ ላይ ታች እላለሁ። ታዲያ ሚዛን ካልጠበቃችሁ ላይ ታች ማለቱም እንደ ሎተሪ ዕጣ ብርቅ ነው። ማለቴ በ‘ትራንስፎርሜሽን’ ዕቅዱ ውጤት፣ በራሳችን ስንፍና አልያም በአስፈጻሚዎች ቸልታ ተቋዳሽ መሆን ካልቻልን ለማለት ነው። መቼም በአደባባይ ሚስጥራችን ልንቆዝም መሰለኝ ሳምንት ተቀጣጥረን የምንገናኘው። አይደል እንዴ? ምን ይታወቃል? ሁሉን እያወቅነው ጓሮ ለጓሮ መንሾካሾክ እንጂ በግልጽ መወያየት እንፈራለን ብዬ ነው።

ተናግረን ነበረ ሰሚ አጣን እንጂ!

ሰላም! ሰላም! በቀደም ማክሰኞ ለረቡዕ አጥቢያ በግራ ጎኔ ተኝቼ ማን ወክሎኝ እንደሆነ አላውቅም፣ ማንን እንደ ወከልኩም እንጃ፣ በአንዴ ከደላላነት ወደ ፖለቲከኝነት ተመንድጌ ለምርጫ ስወዳደር በህልሜ ሳይ ቀውጢ ጩኸት ሰማሁ። ‹‹ገና ሳልመረጥ ይኼ ሕዝብ የሚጮህብኝ ምን አድርጌው ነው?›› ስል ማንጠግቦሽ፣ ‹‹ኧረ ውረድ!›› ስትል በሰመመን እሰማታለሁ። ‹‹ገና ሥልጣን ላይ ሳልወጣ ምን ብዬ ነው የምወርደው?›› ስላት ብርድ ልብሱን ገፈፈችኝ። የጥር ስስ ንፋስ ላዬ ላይ ሽው ሲል ብድግ አልኩ። ለካ ጩኸቱ ከጎረቤት ነው። ‹‹ህልምና ቅዠት መምታታታቸው ሳያንስ በምርጫና በተመራጭነት ዕጣ ያለተፈጥሯችን ይጫወቱብን ጀመር ማለት ነው?›› እያልኩ ሮጬ ወጣሁ። ነገር በዝቷል ዘንድሮ። ከነገሩ በጥቂቱ ላጫውታችሁ።

በር ሲዘጋ መስኮት በር ይሆናል!

ሰላም! ሰላም! ‹ሁዳዴ ከመግባቱ በፊት…› እያለ አንዳንዱ ይኼን ቁርጥ ሲቆርጥ ሳይ ቅበላ እየመሰለኝ ተቸግሬያለሁ። ዳሩ ካላንደር ሳይ ገና ብዙ ቀናት ይቀራሉ። ታዲያ ምንድነው እንዲህ በፆም አሳቦ መፈሰክ እያልኩ ግራ እየገባኝ ነው። አቤት ሆድና ሰው ተባለ። ‹ከውስጥ የሚወጣ እንጂ ወደ ውስጥ የሚገባ ሰውን አያረክሰውም› እንዳላለን ቃሉ  ብሎ ብሎ ትዝብትም ወደ ሆድ ገባ። ሰውና አፉ የማይገባበት የለም አትሉም? መቼስ እንደ ዘንድሮ አልተዛዘብንም።

ይኼኔ ነው መሸሽ!

ሰላም! ሰላም! ይኼውላችሁ በቀደም የሠፈራችን ወጣቶች ‹‹ሲቲ ይበላል፣ የለም ዩናይትድ...›› ብለው ብር ለማስያዝ ገና ሳይነጋ ቤቴ ድረስ መጡ። አምላክ ሲወዳችሁ ገና ፊታችሁን ሳትታጠቡ መንቀሳቀሻ አበል አምጥቶ እጃችሁ ላይ ቁጭ ያደርጋል። ‹‹መቼ ነው የምሰጣችሁ? ስላቸው፣ ‹‹ገና በሰኔ የእንግሊዝ ፕሪሚየም ሊግ ሲያልቅ ነው፤›› አለኝ ተወካያቸው። እኔም፣ ‹‹እግዜር ይስጥልኝ፤›› ብዬ አምስት ሺሕ ብሬን ቆጥሬ ተቀበልኩ። ሰው ቀላል ልማታዊ ሆኗል እንዴ? ይኼ የመታደስና አምራች ዜጋ የመሆን ሥልጠና ውጤት ብቻ እንዳይሆን። ዝም ብዬ ስጠረጥር ግን እሱ ይመስለኛል። በየአቅጣጫው እጅግ በጣም አምራች ዜጎች በዝተዋል። የዛሬ ሳምንት ከሰዓት በኋላ የሆንኩትን አልነገርኳችሁም። ጠዋት ጠዋት እያገኛችሁኝ ነዋ ምን ይደረግ?

አገር ሰማንያ አለው እንዴ?

ሰላም! ሰላም! ይኼውላችሁ እኔም በተራዬ ሲጨንቀኝ ሲጠበኝ ጊዜ አንድ ቡቲክ ገብቼ ‹ስኪኒ› ሱሪ ገዛሁ። አገር ተደበላለቀ ነው የምላችሁ። ለነገሩ አገሩም የአገሩ ሰውም ከተደበላለቀ ቆይቷል። ያው የተደባለቀብንና የተደበላለቀብን መለያየት ካልቻልን ድሮስ ምን ልሆን ኖሯል? እና አንበርብር ‹ሲኪኒ› ሱሪ ገዛ ብሎ ሠፈርተኛው ሁሉ ሲያማኝ፣ ገና ምኑን ዓይታችሁ ብዬ ካፖርቴንም አስጠበብኩት። ነገርና ሰው እያደር ሲጠብ ታዲያ እኔ ምን ላርግ? ባይሆን በአለባበስ ልመሳሰላ።