Skip to main content
x

ጉዞ ወደ ቅበላ!

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት ረዥሙና 55 ቀኖችን የሚይዘው ዐቢይ ጾም (ሑዳዴ) የካቲት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በምዕመናኑ ዘንድ ተጀምሯል፡፡ ዋዜማው እንደሁሌው በቅበላነቱ በሥጋና በወተት በቅቤም ተዋጽዖዎች ታጅቦ አልፏል፡፡ በሥነ ቃል የተመዘገበው፣

የሞ ኢብራሂምን ሽልማት ያሸነፉት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ

የቀድሞዋ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ በመልካም አስተዳደር ለሚመረጡ የአፍሪካ መሪዎች የሚሰጠውን እ.ኤ.አ. የ2017 የሞ ኢብራሂም ሽልማትን አሸንፈዋል።  ዶቼ ቬሌ በድረ ገጹ እንደዘገበው፣ ሽልማቱ በ10 ዓመት ውስጥ የሚከፈል 5 ሚሊዮን ዶላርና ከዚያ በኋላም በየዓመቱ የሚሰጥ 200 ሺህ ዶላርን ያካትታል። የሚሰጠውም በአፍሪካ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው በተለየ መንገድ አገራቸውን ለመሩና የሥልጣን ዘመናቸው ሲያበቃም ከኃላፊነታቸው ለወረዱ መሪዎች ነው።

ፀጉራሙ ባለ መንጃ ፈቃድ

 ወጣቱ የመንጃ ፈቃድ ስላወጣ መኪናቸውን መጠቀም ይችል እንደሆነ ካህን አባቱን ጠየቃቸው፡፡ “አባቱም የትምህርት ውጤትህን ካሻሻልህ፣ መጽሐፍ ቅዱስህን ካጠናህ ፀጉርህን ከተስተካከልክ በጉዳዩ ላይ ልንገጋገር እንችላለን” አሉት፡፡       ልጅየው ከወር በኋላ ነገሮችን አስተካክሎ መኪናቸውን መጠቀም ይችል እንደሆነ በድጋሚ ጠያቃቸው፡፡

የወቅቱ እንቆቅልሽ

በልዊስ ካሮል ‹‹Alice in Wonderland›› በሚለው መጽሐፍ ውስጥ፣ አሊስ ከአንድ ባርኔጣ አምርቶ ከሚሸጥ የተጃጃለ እብድ ጋር ሐሳብ በማንሳት ሲከራከሩ ይታያል፡፡ አሊስ ‹‹አንድ ነገር በዚህ መልኩ ማመን አይገባህም በፍጹም የሚቻል ነገር አይደለም፡፡›› ብላ አስተያየት ስትሰጠው፡፡ ይህ ባርኔጣ አምራች ወፈፌ በኩራትና በመጀነን፤ ‹‹ከንቱ የሆንሽ ነገር!›› እኔ ሁሌም ጧት ጧት ቁርስ ከመብላቴ በፊት ቢያንስ ሁለት የማይቻሉ እምነቶች በማዳበር ለውጤት በማብቃት ልምድ አካብቻለሁ›› በማለት መልስ ስጣት፡፡

‹‹ዝናብ ታቆማለህ ዝናብ ታዘንባለህ››

ወጣቱ ባለቅኔ ኤፍሬም ሥዩም ተሰማ ከቀደምት የኢትዮጵያ ነገሥታትና ሊቃውንት የተወጣጡትን የግእዝ ቅኔያት አዛምዶና አፍታቶ አንድም እያለ የተረጐመበት መጽሐፉን ከዓመታት በፊት ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ ‹‹ተዋነይ ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና›› በማለት በሰየመው መጽሐፉ ፵፱ኛው (49ነኛው) ደጃፍ፣ የሊቀ አእላፍ ልብሰ ወርቅ አየለ ዘደብረ መዊእ ባለ ሁለት መስመር (ስንኝ) ዕዝል ጉባኤ ቃና፣ ‹‹ጽድቅ ውእቱ አውርዶ ወአቅሞ ዝናም በዕፅ በተኪለ ዕፀው ይመልዕ አኮኑ ዘዝናመ ሰማይ ሕፀፅ፡፡›› እንዲህ አፍታትቶ ተርጒሞታል፡፡

ቆርጣችሁ ጣሉት

እውቁ ባለቅኔና ደራሲ አቤ ጉበኛ ‹‹መስኮት›› ባላት መድበሉ፣ በግእዝ ቅኔ በ‹‹ለዓለም›› ስልት ከ44 ዓመታት በፊት እንዲህ ተቀኝቶ ነበር፡- ጉቦሂ ተራጋጭ ላም፡ የክፉ ሹሞች ጥገት፡ ወተት ፍጻሜን ትነፍጋለች፡

40 ኩንታል ብርቱካን የሰረቁ ግለሰቦች ታሰሩ

ሲቪላ በተባለችው ትልቋ የስፔን ከተማ ከቀናት በፊት የተከሰተ ነው፡፡ ጉዳዩ ብዙዎችን ፈገግ ያሰኘና በድርጊቱ የተሳተፉን ደግሞ ያሳሰረ ነበር፡፡ በከተማዋ ጎዳና ላይ ጥርጣሬ በሚያጭር መልኩ ሲበሩ የነበሩ ሁለት መኪኖችን አንድ ፖሊስ ያስቆማል፡፡ አንደኛውን መኪና ከኋላ ባለው ቦታ ላይ ምን ጭኖ እንደሆነ ለማወቅም ፖሊሱ የኋላውን በር ከፈተው፡፡

የአራት ሺሕ ዓመቱ የግብፅ መካነ መቃብር

የጥንታዊ ሥልጣኔ መነሻ መሆኗ የሚነገርላት ግብፅ በውስጧ አስደናቂ ቅርሶችን ይዛለች፡፡ ከሁሉ በተለየ ሁኔታ ገኖ የወጣው የፒራሚድ ጥበቧ ደግሞ ረቂቅ የኪነ ሕንፃ ጥበብ የሚታይበት፣ ዕንከን የለሽ አወቃቀሩ ደግሞ በሰዎች ሳይሆን ምጡቅ በሆኑ የሌላ ዓለም ፍጥረቶች የታነፀ ተደርጎ እንዲታሰብ ሁሉ የሚያስገድድ ነው፡፡

…እጅህ የጣለው

የሰማይ መላእክት ገደብ ሳለባቸው ገፍቶም ሳት ብሏቸው ÷ ከቶም ይዞላቸው ኪሩቤ‘ም ባይናቸው ÷ ገልጠው አሏዩዋቸው፤ ሱራፊም በእጃቸው ÷ ነቅሰው አለዩዋቸው፤