Skip to main content
x

ኮንትሮባንዲስቶቹ ይራገፉ!

ሰሞኑን በተደራጀ መንገድ ኮንትሮባንድ ሲያጧጡፉ የነበሩ 13 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን መንግሥት ነግሮናል፡፡ የሰዎቹ ማንነት በቀረበው ዜና ላይ ባይገለጽም፣ ተደራጅተው ኮንትሮባንድ የሚያካሂዱ አደገኛ ሰዎች መኖራቸው በራሱ ብዙ ይናገራል፡፡ ሰፊ ሥፍራዎችን በሚሸፍነው በዚህ አደገኛ ድርጊት ውስጥ እየተሳተፉ የነበሩ ግለሰቦች የተጠናከረ ኔትወርክ እንደነበራቸው ነው፡፡ የግለሰቦቹ ማንነት እስኪነገረን ድረስ የችግሩን ጥልቀትና ውስብስብነት አንስተን መነጋገር አለብን፡፡

የፍትሕ መጥፋት አሁንም የአገር ደዌ ነው

‹‹ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት አገር መብታቸው ተከብሮ እንዲኖሩ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በኬንያ በተለያዩ ምክንያቶች በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ያቀረቡት ጥያቄ በኬንያው ፕሬዚዳንት ተቀባይነት ማግኘቱን›› የነገረን (ከሌሎች መካከል)፣ የኢቲቪ የሚያዝያ 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የምሽት ዜና ነው፡፡

ኢወገናዊ በሆኑ ተቋማት ላይ ዴሞክራሲን መገንባት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ግዳጅ ነው

የኢሕአዴግ ‹‹ጥልቅ ተሃድሶ›› መከራውን ሲያይ፣ ሲታሽ፣ ሲተሻሽ፣ ብቅ ጥልቅ፣ ብልጭ ድርግም፣ ሲል ቆይቶ ባልተለመደና ከራሱ ከድርጅቱ ፈቃድና ዕቅድ ውጪ የዶ/ር ዓብይን የአመራር ዘመን አስጀምሯል፡፡ ገና አንድ ወሩን ሚያዝያ መጨረሻ ላይ የሞላው የዓብይ ዘመን የአገሪቱ የዴሞክራሲ ግንባታ ችግር የሆኑትን መሟላት የሚገባቸውን፣ ብዙዎችም የሚፈልጓቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች ይፋ አድርጓል፡

ኢትዮጵያችንንና ኢትዮጵያዊነትን እንዴት እናጠናክር?

የምንተዳደርበትን የኢትዮጵያ ፌዴራሊዝም ‹‹እንከን የሌለው›› (የብሔር እኩልነትንና የብሔር ብሔረሰቦችን የራስ በራስ አስተዳደር የዘረጋ እያሉ) የሚያሞግሱ ሰዎች፣ አሁን ያጋጠመንን የግጭት ችግር ከጥገኞች የጥቅም ግጭትና ከወሰን አለመካለል የመጣ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡

ኢትዮጵያ ሆይ! ይህም አዲስና ውድ ዕድል ያመልጥሽ ይሆን?!

ዛሬ የምንገኘው ማሩኝ ታድሼ እክሳለሁ ባይነት፣ ይህንን ዓይነቱን መሀላ መታገስና በደም ፍላት የታወረ የትግል ዘይቤ አፋፍ ላይ የደረሱበት ወቅት ላይ ነው፡፡  ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙበትና የአያሌ ሕዝቦችና ወጣቶች ድጋፍና ተስፋ ይህንኑ ሰው ሙጥኝ ያሉበት፣ ይህ ወቅት የመጣው ብዙ የቁርጥ ቀናትንም አዝሎ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕዝብን ተስፋና አመኔታ ማሸነፍ ይችሉ ይሆን!?

ኢሕአዴግ አዲስ ሊቀመንበር ከመረጠ፣ ፓርላማውም የኢሕአዴግን ሊቀመንበር አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሰየመ ወዲህ፣ በተለይም የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሲመት ንግግር ከተሰማ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ተስፋ ነፍስ ዘርቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በርታ ግፋ ገና ነው በሉ

አገራችን አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይማለች፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየትኛውም መለኪያ፣ በቃሉ ትክክለኛ ትርጉምና አግባብ እውነትም አዲስ ናቸው፡፡ አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ ከሚያደርጋቸው ነገሮች መካከል አንዱ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ አሸናፊነታቸውን ያረጋገጠው የምርጫ መድረክ ራሱ፣ አለወትሮው አዲስ መሆኑ ያልተለመደ አዲስ ነገር ይዞ መምጣቱ ነው፡፡

አንዳንድ ነገሮች በሊቀመንበሩ ምርጫና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ላይ

ከአርባ ቀን አስቸጋሪ ውጣ ውረድና ታይቶ የማይታወቅ የአሠላለፍ ፍትጊያ በኋላ ኢሕአዴጎች (የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች) ድምፃቸውን ሰጥተው፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆነውን የግንባራቸውን ሊቀመንበር መርጠዋል፡፡ የፓርቲውም ሊቀመንበር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሦስተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ይሰየማል፡፡

ሊቀመንበሩን የሚወልደው ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አደራ ይወስናል

የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሁለቱም ሥልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን (የሚለቁ መሆናቸውን) በድንገት ከገለጹ፣ እነሆ ሳምንቱ መጨረሻ ላይ 38 ቀን ሆነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሥራው ላይ ያሉት፣ ተተኪያቸው እስኪመረጥና ሥልጣኑን እስኪረከብ ድረስ ብቻ መሆኑንም በዕለቱ (የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም.) እና ከዚያ ጀምሮ ሲነገረን ቆይቷል፡፡

የአገራችንና የአኅጉራችን ትኩስ ፈተናዎች

የትራምፕ የአሜሪካ መንግሥት “አሜሪካን ከዓለም እየነጠለ ነው . . . ግሎባላይዜሽንንና ነፃ ገበያን እየተቃረነ ነው . . . በገበያ ጥበቃ የተጠመደ ነው . . . ” እየተባለ ይወረፋል፡፡ በሀብታም አገሮች አካባቢ ይህን መሰሉ ነቀፋ ቢደራ የተነካባቸውን ወይም የተስተጓጎለባቸውን ወይም ሥጋት ያገኘውን የንግድ ጥቅማቸውን ወደነበረበት የመመለስ ትግል መሆኑ ነው፡፡