Skip to main content
x

ሆሄ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ጸሐፊዎችን ያወዳድራል

ሆሄ ዓመታዊ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ግጥምና ወግ የሚያስነብቡ ጀማሪ ጸሐፊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም አስታውቋል፡፡ ዓምና የመጀመሪያው ዙር ውድድር የተካሄደው በረዥም ልቦለድ፣ በልጆች መጻሕፍትና በግጥም ዘርፍ ሲሆን፣ ዘንድሮ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ታክሎበታል፡፡ በ2009 ዓ.ም. በማኅበራዊ ድረ ገጽ (በዋነኛነት በፌስቡክ) ከቀረቡ ግጥሞችና ወጎች በተጨማሪ ታትመው ለንባብ የቀረቡ የወግ መጻሕፍትም በውድድሩ ይካፈላሉ፡፡

ግባቸውን መፈተሽ የሚያሻቸው የመጽሐፍ ምረቃዎች

ዮናታን በላይ (ስሙ ተቀይሯል) የሥነ ጽሑፍ ምሩቅ ሲሆን፣ ሥነ ጽሑፍን ያማከሉ ዝግጅቶችን አዘውትረው ከሚታደሙ አንዱ ነው፡፡ የመጽሐፍ ምረቃና ውይይት ይከታተላል፡፡ አንድ ደራሲ ጽሑፉን ለንባብ ለማብቃት የሚያልፈውን ውጣ ውረድ ከግምት በማስገባት፣ ጽሑፉ የሕትመት ብርሃን ሲያይ የላቀ ደስታ ይሰማዋል፡፡

የሥነ ጽሑፍ ባለውለታው

የተለያዩ ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ወይም ትምህርታዊ መጣጥፎችን ጽፎ ለሕዝቡ ለማድረስ ቆዳ ፍቆ፣ ብራና ዳምጦ ማዘጋጀት ከዚያም መከተቢያ ቀለም መቀመም ግድ ይላል፡፡ ይህም የጽሑፍን ሥራ እጅግ አድካሚና ሥራውም ለተመረጡ ትጉኃን የተሰጠ ያስመስለው ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡