Skip to main content
x

የምሁራን አሥራፂነት የሚሻው ቴክኒክና ሙያ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና (ቲቪኢቲ) በሠለጠኑ አገሮች የስማቸው መጠሪያ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የተናቀ ሙያ ተደርጎ ሲወሰድ ኖሯል፡፡ ከዚህ አኳያ ሙያው ተወዶና ተከብሮ እንዴት ነው መሥራት የሚቻለው በሚለው ዙሪያ ከኅብረተሰቡ ጋር ለመወያየት የሚያስችል ብዙ የንቅናቄ ሥራዎች ወደፊት እንደሚኖር የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደረሱለት ታዳጊ

ከደቂቃዎች በፊት ሲቦርቅ ሲጫወት የነበረ ሕፃን ከአፍታ በኋላ እንደዋዛ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ የማይችልበት ከእርሶ የራቀ የዝምታ ዓለም ውስጥ ሆኖ ቢያገኙት ምናልባት ቅዠት ይሆን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እውነታውን አምኖ መቀበል እንኳንስ ለወላጅ ለሌላም ከባድ ይሆናል፡፡ ችግሩ የተፈጠረው ደግሞ ብዙም አስጊ ያልነበረን ነገር ግን ምቾት የነሳውን የጤና እክል አክመው ያድኑታል ብለው ባመኑባቸው ሐኪሞች ሲሆን፣ ሐዘኑም ቁጭቱም ድርብ ይሆናል፡፡

ለገርቢ ግድብ ፕሮጀክት መሬት ማስረከብ ባለመቻሉ ከቻይና የተገኘ 146 ሚሊዮን ዶላር ጥቅም ላይ ሳይውል ቀረ

ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ለታሰበው የገርቢ ወንዝ ግድብ ፕሮጀክት፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስፈላጊውን መሬት በወቅቱ ባለማቅረቡ ከቻይና መንግሥት የተገኘው ብድር መጠቀሚያ ጊዜ አለፈበት፡፡ ይህ ገንዘብ ከአንድ ዓመት በፊት ሥራ ላይ መዋል የነበረበት ቢሆንም፣ መሬቱን ማግኘት ባለመቻሉ ተመላሽ ሆኗል ተብሏል፡፡

ከስምንት ሺሕ በላይ የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት 38 ሔክታር መሬት ተሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ተጨማሪ 8,428 የ40/60 ቤቶችን ለመገንባት፣ 38 ሔክታር መሬት ከአስተዳደሩ መረከቡን አስታወቀ፡፡ ባለ 15 እና 13 ፎቅ 54 ሕንፃዎችን ለመገንባት የዲዛይን ማጣጣም ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን፣ በኢንተርፕራይዙ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሒደት መሪ በአቶ ዮሐንስ አባይነህ ተፈርሞ ወጪ የተደረገው ደብዳቤ ያስረዳል፡፡

ልሂቅ ፕሮፌሰር ዓቢይ ፎርድ  (1927- 2010)

በ1920ዎቹ ዓመታት በማርክስ ጋርቬይ መሪነት ተራማጅ አስተሳሰብ ያራምድ በነበረው የሐርለም ፓን አፍሪካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱ ራባይ አርኖልድ ጆሹዋ ፎርድ ይጠቀሳሉ፡፡ በማርከስ ጋርቬይ የተመሠረተው ዩኒቨርሳል ኔግሮ ማኅበርም የሙዚቃ ዳይሬክተር ሆነው ከማገልገላቸው ባሻገር ‹‹ወደ አፍሪካ እንመለስ›› በተሰኘው ንቅናቄ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ በማቅናት ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ሲከበር የሙዚቃ ሥራቸውን አቅርበዋል፡፡

ዘንድሮ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ

በኢትዮጵያ አገር አቀፍ ፈተና መስጠት ከጀመረበት 1938 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ ጊዜው ሁኔታ የሚለዋወጡ የፈተና አስተዳደር ሥራዎች ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡ ከዓመት ዓመት እየጨመረ ከሚሄደው የተማሪ ቁጥር አንፃር በየወቅቱ የሚሰጡ ፈተናዎች በሙሉ ተመሳሳይ የፈተና አስተዳደር ሒደትን አይከተሉም፡፡ የኅትመት ሒደቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ያሉ የፈተና ዝግጅት ሒደቶችን ጨምሮ ያሉ ሒደቶች ፈተናው ተጠናቆ የመስጠት ያህል ቀላል እንዳልሆነም መገመት ይቻላል፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

መንግሥት ከፍተኛ የገንዘብና የእስራት ቅጣት የሚጥል ሕግ ያወጣ ቢሆንም፣ በተደራጀና ኃላፊነት በተሞላበት ሁኔታ ሕጉን ተግባራዊ ሊያደርግ ባለመቻሉ በሕገወጥ ደላሎች የሰዎች ዝውውር ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ፡፡ ከአራት ዓመታት በፊት በተለይ በሳዑዲ ዓረቢያ በቤት ሠራተኝነትና በሌሎች ሥራዎች ተሠማርተው በነበሩ ኢትጵያውያን ላይ በደረሰው ግድያ፣ አካል ማጉደልና ከፍተኛ እንግልት ምክንያት መንግሥት ዜጎች ወደ መካከለኛው ምሥራቃዊ አገሮች እንዳይጓዙ ዕግድ ጥሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አገልግሎት የማይሰጡ የወጣት ማዕከላት መበራከታቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሦስት ሺሕ የወጣት ማዕከላት መካከል በተለያዩ አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ችግሮቸ ሳቢያ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት 998ቱ ብቻ እንደሆኑ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በአሁኑ ወቅት 183 የወጣት ማዕከላት ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት ያቆሙ ሲሆን፣ 10 ማዕከላት መፍረሳቸውን፣ አምስት ለሌላ አገልግሎት መዋላቸውን የማዕከላቱ አገር አቀፍ አሀዛዊ መግለጫ ያሳያል፡፡ አብዛኞቹ የፈረሱ ማዕከላት በገጠራማው የትግራይ ክፍል የሚገኙ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

የትራፊክ አደጋ በሚበዛባቸው መስመሮች የአልኮል መመርመርያ መሣሪያ ሊሠራጭ ነው

የአዲስ አበባ መንገድ ትራፊክ ማኔጅመት ኤጀንሲ አደጋ በሚበዛባቸው አሥር ዋና ዋና መንገዶች፣ አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን መቆጣጠር የሚያስችል መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊያውል ነው፡፡ በፍጥነት ምክንያት ከሦስት ሰው በላይ ሕይወት የሚቀጥፉ አሥር መንገዶች በጥናት የተለዩ መሆናቸውን ኤጀንሲው ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ዕውቅናን ለናፈቀው ጋዜጠኝነት

በየሽርፍራፊ ደቂቃ በተለያዩ የዓለም ጥጎች የሚከሰቱ ሁነቶችን ጋዜጠኛው ምንም ሳይቀር ከጆሮዎ በማድረስ፣ በዓይኖ በማሳየት ባሉበት ሆነው ማንኛውም መረጃ እንዲያገኙ የማድረግ ሚና ይጫወታል፡፡ በየፈርጁ የሚከናወኑ አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ክስተቶች፣ በእርስ በርስ ጦርነት የሚተላለቁ ዜጎችን አሳዛኝ ገፅታ በካሜራው አስቀርቶ በቴሌቪዥን መስኮት ያስቃኝዎታል፣ በዓይነ ህሊናዎ ምስል መፍጠር የሚችል ገላጭ ጽሑፍ ቀምሮ በጋዜጣ ያስነብቦታል፣ በሬዲዮ ያስደምጦታል፡፡