Skip to main content
x

የምንዛሪ ለውጡ ምስቅልቅሎሽ

መንግሥት የብር የመግዛት አቅም ከዶላር አኳያ በ15 በመቶ እንዲቀንስ በመወሰን ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ አድርጓል፡፡ በዚህም በርካታ የገበያ ውዥንብር ተፈጥሯል፡፡ እንደ መንግሥት ማብራሪያ፣ የተደረገው ለውጥ እንዲያመጣ ከሚጠበቁበት መሻሻሎች አንደኛው የአገሪቱን የወጪ ንግድ ተወዳዳሪ ማድረግ ነው፡፡

ዘመን ባንክ አዲስ ፕሬዚዳንት ይሰይማል ተብሎ እየተጠበቀ ነው

የዘመን ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኩን ላለፉት አምስት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ ፀጋዬ ተጠምቀን ለመተካት፣ ዕጩ ያደረጋቸውን ፕሬዚዳንት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ምንጮች ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት ቦርዱ ባንኩን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ይችላሉ የተባሉ የባንክ ባለሙያዎችን ጭምር በማነጋገርና በመደራደር ላይ ቆይቷል፡፡ ለቦታው ብቁ ይሆናሉ የተባሉ የመጨረሻዎቹን ሁለት ዕጩዎችን በመለየትም በአንዱ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሳያሳልፉ እንዳልቀረ የምንጮች መረጃ ያስረዳል፡፡

እየቀነሰ የመጣው የገቢ ንግድ

በአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ መካከል ያለው ሰፊ ልዩነት አሁንም እንደቀጠለ ቢሆንም፣ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው ወጪ ቅናሽ እያሳየ መሆኑ ተመለከተ፡፡ የአገሪቱን የወጪና ገቢ ንግድ ዓመታዊ ተከታታይ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በተለይ ባለፉት አሥር ዓመታት የገቢ ንግዱ በአማካይ ከ20 በመቶ እያደገ ቢሆንም፣ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ አገሪቱ ለገቢ ንግድ የምታውለው የውጭ ምንዛሪ በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ ነው፡፡ ሰሞኑን ይፋ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የ2009 ዓመታዊ ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውም፣ በ2009 በጀት ዓመት ለወጪ ንግድ የወጣው ወጪ ከቀደመው በ5.5 በመቶ ቀንሷል፡፡ 

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ሀብት 50 ቢሊዮን ብር ደረሰ

አነስተኛ ብድር በማቅረብ አገልግሎት የሚሰጡ 35 የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት አጠቃላይ የሀብት መጠናቸው 50 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተመለከተ፡፡ የአገሪቱን የ2009 ዓ.ም. ኢኮኖሚያዊ ክንውኖችና የፋይናንስ ተቋማትን አፈጻጸም የተነተነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ሪፖርት፣ አስተኛ የገንዘብ አቅራቢ ወይም የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በወቅቱ የደረሰቡት አጠቃላይ የሀብት መጠን 50 ቢሊዮን ብር ከመድረሱ ባሻገር፣ በ2008 ዓ.ም. ከነበራቸው ሀብት አኳያ የ35.1 በመቶ ዕድገት ማስመዝገባቸውን ሪፖርቱ አስፍሯል፡፡

የግል ባንኮች ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ በማበደር ግማሽ ዓመቱን አጠናቀዋል

በአገሪቱ በተፈጠረው የፖሊቲካና የፀጥታ ችግር ሳቢያ የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸው ብቻም ሳይሆን፣ የብድር አሰጣጥ ገደብ መጣሉ የባንኮችን እንቅስቃሴ ክፉኛ እንደፈተነው ሲነገር ቆይቷል፡፡ ይህ ይባል እንጂ የአገሪቱ ባንኮች እንደወትሯቸው ውጤታሜ እንቅስቃሴ ከማድረግ ባሻገር በአትራፊነታቸው እንደቀጠሉና ለተበዳሪዎች የሰጡት የገንዘብ መጠንም ጭማሪ ማሳየቱ ታውቋል፡፡

የብሔራዊ ባንክ ውሳኔን የሚጠብቀው የባንክ ዳይሬክተሮች ሹመት

የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት በአገሪቱ ሕግ መሠረት ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴያቸውን የሚያሳይ ሪፖርት በማጠናቀር በውጭ ኦዲተሮች ተመርምሮ የተመሰከረ የሒሳብ ሪፖርታቸውን ባለአክሲየኖች ለሚታደሙበት ጠቅላላ ጉባዔ ያሰማሉ፡፡ የፋይናንስ ተቋማቱ ከሌሎች የአክሲዮን ኩባንያዎችና በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ ከተመለከተው ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕግጋትና መመርያዎችን የተከተሉ ጉባዔዎችን የማካሄድ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡

አይኤምኤፍ የልማት ባንክ የተዛባ ብድር አሰጣጥን ለማስተካከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥል አለ

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክን የተዛባ ብድር አሰጣጥን ለማስተካከል፣ በመንግሥት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት አለ፡፡ አይኤምኤፍ ረቡዕ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ከገመገመ በኋላ ባወጣው መግለጫ፣ መንግሥት የልማት ባንክን ለማስተካከል የጀመረውን ጥረት በመደገፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የልማት ባንክን የተበላሸ ብድር ለማስተካከል ግብረ ኃይል ተቋቋመ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ካበደረው ገንዘብ ውስጥ 25.3 በመቶ የሚሆነው የተበላሸ ብድር በመሆኑ፣ ይኼንን የተበላሸ ብድር ምጣኔ ወደ ገደቡ ለመመለስ በባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታሁን ናና የሚመራ ግብረ ኃይል አቋቋመ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተበላሸ ብድር ምጣኔ ከአምስት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት ገደብ ያስቀመጠ ቢሆንም፣ የልማት ባንክ የተበላሸ ብድር መጠን 25.3 በመቶ መድረሱ ተመልክቷል፡፡

ከዓመታት ቆይታ በኋላ አዲስ የግል ባንክና የመድን ኩባንያ ምሥረታ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የግል ባንኮችን ለማቋቋም የሚጠይቀውን የተከፈለ ካፒታል ከ100 ሚሊዮን ብር ወደ ግማሽ ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲደረግ በማለት ያወጣው መመርያ ሥራ ላይ ከዋለ ስድስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የኢንሹራንስ ኩባንያ ለማቋቋም ከሃያ ዓመታት በፊት በወጣው ድንጋጌ መሠረት ይጠየቅ የነበረው የተከፈለ ካፒታል ለጠቅላላ የኢንሹራንስ ሽፋን ሦስት ሚሊዮንና ሰባት ሚሊዮን ብር ብቻ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ችላ የተባለው የካፒታል ገበያ

እ.ኤ.አ. ግንቦት 18 ቀን 2012 ላይ በዓለም ትልቁ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያ ፌስቡክ የአክሲዮን ገበያውን ለመጀመርያ ጊዜ መቀላቀሉ ይፋ ተደረገ፡፡ እርግጥ ነው ፌስቡክ ከዚያ በፊት የኩባንያውን አክሲዮን መሸጡ አልቀረም፡፡ የኩባንያው ትልቁ ድርሻ ያለውና የፌስቡክ መሥራች ማርክ ዙከርበርግ እ.ኤ.አ. ከ2012 በፊትም ቢሆን እንደ ጎግል ላሉ ኩባንያዎች የተገደበ የአክሲዮን ሽያጭ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን 2012 ላይ ፌስቡክ በተወሰኑ ባለአክሲዮኖች ባለቤትነት ሥር መቆየት እንደማይችል፣ ይህም በተገደበ ሁኔታ እየሸጠ የቆየው አክሲዮን ከ500 ባለአክሲዮኖች በላይ ሊያስጨምረው እንደማይችል በመረዳቱ ነበር፡፡ የአሜሪካን ሴኩሪቲስ ኤንድ ኤክስቼንጅ ኤጀንሲ ባወጣው መመርያ መሠረት ፌስቡክ አክሲዮኑን ለሕዝብ ክፍት ማድረግ ያለበት ደረጃ ላይ ደርሶም ነበር፡፡