Skip to main content
x

የሳምንቱ ገጠመኝ

‹‹ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም›› የሚለው የቆየ ምሳሌ ትዝ ያለኝ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ውስጥ ነው፡፡ አንዳንድ አግራሞት የሚያጭሩብን ጉዳዮች ከመብዛታቸው የተነሳ ስንት ቁምነገር የሚሠራበት ጊዜ በዋዛ ፈዛዛ ማለፉ ያንገበግበኛል፡፡ እዚህ አገራችን ውስጥ ጊዜ ተፈብርኮ ለዓለም እየተቆነጠረ የሚታደል ይመስል፣ ለታላላቅ ተግባሮች የምናውላቸው እጅግ በጣም ውድ የሆኑ ጊዜዎቻችን የሌሎችን እንቶ ፈንቶ ስንሰማባቸው ይባክናሉ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ እየተጓዝኩ ነበርኩ፡፡ ድሬዳዋ የሄድኩበትን ጉዳይ ቶሎ አከናውኜ ወደ አዲስ አበባ የማደርገው ጉዞ የፈጠነው፣ በነጋታው ለሌላ አስቸኳይ ጉዳይ ወደ ጎንደር ስለምሄድ ነበር፡፡ ከድሬዳዋ የጀመርነውን ጉዞ እያገባደድን አዋሽ አካባቢ ስንደርስ የተሳፈርንበት አውቶቡስ ጎማ ፈንድቶ ቆምን፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

የተሳፈርንባት በጥሩ ሁኔታ የተያዘች ናት፡፡ በዚያ ላይ በማስታወቂያዎች ደምቃለች፡፡ ከአሮጌ ዕቃዎች እስከ ኮምፒዩተር የምንፈልጋቸውን ነገሮች የሚጠቁሙ ማስታወቂያዎች ተገጥግጠውባታል፡፡ ሃይማኖታዊና ዓለማዊ ጥቅሶችም በየፈርጃቸው ተሰድረዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ፣ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ የቦብ ማርሌና የቴዲ አፍሮ ፎቶግራፎችም ሥፍራቸውን ይዘዋል፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

ከእለታት አንድ ቀን በአንድ አገር ንጉሡ ሕዝብ ስለሳቸው ምን እንደሚል ለማወቅና የተለያዩ ትኩስ ወሬዎችን ለመስማት በማሰብ አንድ ዕቅድ ያወጣሉ፡፡ በዕቅዳቸው መሠረት ሕዝቡ ውስጥ የሚነገሩትን ነገሮች በሙሉ ልቅም አድርጎ የሚያመጣላቸው ሰው ይሾማሉ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

እጅግ በጣም ባለፀጋ የነበረ አሜሪካዊ ሞቱ መቃረቡን ሲረዳ ካከማቸው ገንዘብ ላይ ለሕፃናት ማሳደጊያ፣ ለአረጋውያን መጦርያ፣ ለወጣቶች ንባብ ቤትና ለሴቶች ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በሚገባ ይሰጥና 90 ሚሊዮን ዶላር ይተርፈዋል፡፡ ላለፉት በርካታ ዓመታት ከለፋበት ገንዘቡ ላይ ለራሱ የሚሆን ማስቀረት ፈለገ፡፡ ይኼንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሐኪሙን፣ የንስሐ አባቱንና ጠበቃውን የምሳ ግብዣ አዘጋጅቶ ጠራቸው፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በቀደም ከአራት ኪሎ ወደ ፒያሳ ቀስ እያልኩ ሳዘግም ከኋላዬ ድምፅ ሰምቼ ዞር ስል በሰላሳዎቹ አጋማሽ ውስጥ የምትሆን ሴት አጠገቤ ደርሳለች፡፡ እየሳቀች የምታየኝ ይህች ቆንጆ ሴት በጣም ውድ የሚባሉ አልባሳትዋና መጫሚያዋ ልዩ ሞገስ ሰጥተዋታል፡፡ መነጽሯን አውልቃ እየሳቀች ስትጠጋኝ የት ነው የምንተዋወቀው ብዬ ለአፍታ እንዳስብ ተገደድኩ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትራችን እናት!

አንዳንድ ጊዜ አስገራሚ ጥያቄዎች ወደ አዕምሮአችን በራሳቸው ጊዜ ይመጣሉ፡፡ ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በዓለ ሲመታቸውን ሲያከናውኑ አንድ ነገር አስደሰተኝ፡፡ የተደሰትኩት በሹመቱ አይደለም፣ በነበረው ደማቅ ሥነ ሥርዓትም አልነበረም፡፡ በአንድ ባልተለመደ ክስተት እንጂ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በአንድ ወቅት በተወሰኑ ትምህርት ቤቶችና በወላጆች መካከል መቃቃሮች እየተፈጠሩ በየሚዲያው ሲወነጃጀሉ ይሰሙ ነበር፡፡ ወላጆች ትምህርት ቤቶች ጥራት ያለው ትምህርት አለመስጠታቸውንና የማያቋርጥ የክፍያ ጭማሪ ማስከፈላቸውን ሲወቅሱ፣ ትምህርት ቤቶችም የራሳቸውን ምክንያት ይደረድራሉ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በቀደም ዕለት ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዘውን ‹‹ታታ›› አውቶቡስ የተሳፈርኩት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ላይ ነው፡፡ ሁለት ሰዎች የሚያስቀምጠው ወንበር ላይ አረፍ ከማለቴ ከኋላዬ ተከትለውኝ የገቡ አዛውንት መነኩሴ አጠገቤ ተቀመጡ፡፡ የተለመደውን ሰላምታ ካቀረቡልኝ በኋላ በፀጥታ ውጭ ውጩን ማየት ጀመሩ፡፡

የሳምንቱ ገጠመኝ

በዚህ ጉደኛ ዘመናችን ውስጥ የምናስተውላቸው አንዳንድ ገጠመኞቻችን ከዘመናት በፊት ጥለን የመጣናቸውን የፊውዳሎች የአኗኗር ዘይቤ ያስታውሱናል፡፡ መሬት በጥቂት ፊውዳሎች ተይዞ ብዙኃኑ አርሶ አደሮች ከባርነት ባልተናነሰ ሁኔታ ገባር በሆኑበት በዚያ ዘመን፣ ሹመት ፈላጊ የዘመኑ ሰዎች የንጉሣዊያኑንና የገዢዎችን ችሎቶች ያጣብቡ ነበር፡፡