Saturday, Jul 31st

English Version

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግማሽ ዓመት ትርፍ 1.5 ቢሊዮን ብር ደረሰ

E-mail Print PDF
User Rating: / 1
PoorBest 

(በኃያል ዓለማየሁ)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ68 ዓመት ታሪኩ ከፍተኛ የሆነ 1.5 ቢሊዮን ብር የግማሽ ዓመት ትርፍ ማስመዝገቡን ምንጮች ለሪፖርተር ገለፁ፡፡ ባንኩ በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ ያስመዘገበው ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ጭማሪ አስመዝግቧል፡፡

በአሁኑ ወቅት ባለ 42 ፎቅ ህንጻ ለማስገንባት በዝግጅት ላይ የሚገኘው ይኸው ንግድ ባንክ ባለፈው በጀት ዓመት በታሪኩ ትልቁ የሆነውን 2.7 ቢሊዮን ብር ማትረፉ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ የባንኩ የተጣራ የዓመት ትርፍም 1.9 ቢሊዮን ብር መድረሱ ይታወቃል፡፡

በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ ከዓመት ዓመት የባንኩ ትርፍ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ከተጠቀሰው ከፍተኛው የባንኩ የግማሽ ዓመት ትርፍ በተጨማሪ የባንኩ የተበላሹ ብድሮች መጠን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 3.1 በመቶ መውረዱም ታውቋል፡፡

ከስድስት ዓመት በፊት የባንኩ የተበላሹ ብድሮች መጠን 50 በመቶ ደርሶ የነበረ ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ባንክ ጤናማ ሊባል የሚችለው የተበላሸ የብድር መጠኑ ከ10 በመቶ በታች ሲሆን እንደሆነ ከሚያመለክተው ገደብ እጅግ ከፍ ያለ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባለፈው ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ለጋዜጠኞች ግልፅ እንዳደረገው የባንኩ ካፒታልና ተቀማጭ ገንዘብ እ.ኤ.አ በ2008/09 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ 5 ቢሊዮን ብር ደርሶ የነበረ ሲሆን የተጣራ ግምቱ ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ ነበር፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ ከሚገኘት 208 ቅርንጫፎች በተጨማሪ በደቡብ ሱዳን ጁባ አዲስ ቅርንጫፍ መክፈቱ የሚታወስ ነው፡፡