Friday, Sep 03rd

English Version

Reporter - Amharic Version

ቴሌ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል የተባለው የሞባይል ፍሪኩዌንሲ ሀሰተኛ መረጃ ነው አለ

E-mail Print PDF
User Rating: / 4
PoorBest 

ሰሞኑን ማንነታቸው ከማይታወቁ የሞባይል መስመሮች፣ ድረ ገጾች፣ ኤሜልና የሞባይል አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS) አደገኛ የሞባይል ፍሪኩዌንሲ በጤና ላይ አደጋ ያደርሳል ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ መሠረተ ቢስ መሆኑን፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡ ኮርፖሬሽኑ ዛሬ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ሆን ተብሎ ሽብር ለመፍጠር የታሰበ በመሆኑ፣ ተጠቃሚው ኅብረተሰብ ምንም ዓይነት ስጋት እንዳይሰማው አሳስቧል፡፡

Read more...

የምርጫው ጊዜያዊ ውጤት ዛሬ ምሽት ይፋ ይደረጋል

E-mail Print PDF
User Rating: / 18
PoorBest 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ጊዜያዊ ውጤት ዛሬ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ይፋ ያደርጋል፡፡ ጊዜያዊ ውጤቱ ይፋ የሚደረገው በቦርዱ ዋና ጽ/ቤት አዳራሽ ነው፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2003 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚወጣ ማንኛውንም ማስታወቂያ እንዳይተላለፍ ከለከለ፡፡

E-mail Print PDF
User Rating: / 5
PoorBest 

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2003 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል የሚወጣ ማንኛውንም ማስታወቂያ በቴሌቪዥን፣ በሬድዮ ወይንም በጋዜጣ እንዳይተላለፍ ከለከለ፡፡

Read more...

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ግዮን ሆቴልን በሰባት ቢሊዮን ብር ሊገነቡ ነው

E-mail Print PDF
User Rating: / 10
PoorBest 

- ባለአራትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ይገነባሉ
- የሄሊኮፕተር ማረፊያ ይኖዋል
- ግንባታው በሦስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል
- መንግሥት የ20 በመቶ ድርሻ አለው
- ዓለም አቀፉ ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴሉን ያስተዳድራል
- ሆቴሉ  ለፕሬዚዳንቶች ልዩ ማረፊያዎች ይኖሩታል

Read more...

“ምርጫው ነፃና ፍትሀዊ አይደለም” መድረክ “የዘንድሮ ምርጫ የልጅ ጨዋታ ይመስላል” መኢአድ “የተቃዋሚ ፓርቲዎች ክስ ትክክል እንዳልሆነ አጣርተናል” ምርጫ ቦርድ

E-mail Print PDF
User Rating: / 12
PoorBest 

“ምርጫው ነፃና ፍትሀዊ አይደለም”
መድረክ
“የዘንድሮ ምርጫ የልጅ ጨዋታ ይመስላል”
መኢአድ
“የተቃዋሚ ፓርቲዎች ክስ ትክክል እንዳልሆነ አጣርተናል”
ምርጫ ቦርድ


ዛሬ በመላ አገሪቱ እየተካሄደ ባለው ብሔራዊ ምርጫ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ትችት ቀርቦበታል፡፡ የመድረክ ከፍተኛ አመራር ኢንጅነር ግዛቸው ሽፈራው ድምፃቸውን በሰጡበት ወረዳ 17 ቀበሌ 17 የምርጫ ጣቢያ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ምርጫው ነፃና ፍትሐዊ አይደለም ብለዋል፡፡ ኢንጅነር ግዛቸው እንደተናገሩት፣ የመድረክ ታዛቢዎች በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከምርጫ ጣቢያዎቹ እየተባረሩ ነው ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በባሌ አካባቢ የመድረክ ታዛቢዎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ታግተው እንግልት ከደረሰባቸው በኋላ መበተናቸውን ኢንጅነሩ ገልፀው፣ በአማራ ክልልም በተለያዩ ቦታዎች የመድረክ ታዛቢዎች ከምርጫ ጣቢያዎች ተባረዋል ብለዋል፡፡

Read more...

Page 1 of 161

  • «
  •  Start 
  •  Prev 
  •  1 
  •  2 
  •  3 
  •  4 
  •  5 
  •  6 
  •  7 
  •  8 
  •  9 
  •  10 
  •  Next 
  •  End 
  • »