Skip to main content
x

አገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰላም እንድትሸጋገር ለማድረግ የቀረበ የመነሻ ሐሳብ

ኢትዮጵያ አገራችን አሁን የምትገኘው የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በሕገ መንግሥቱ በተቀመጠው መሠረት የማይከበሩበት፣ ይህን ለማድረግ የሚያስችል የፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር የሚጠበቅባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በፍፁም መንቀሳቀስ ያልቻሉበትና የአንድ ፓርቲ ፍፁም አምባገነን ኢዴሞክራሲያዊ አገዛዝ በሠፈነበት ሁኔታ ነው፡፡

ወደ ኋላ ሳያዩ ወደ ፊት መሄድ ይቻላል ወይ?

ይህች አገር ምናባዊ ሆናለች፡፡ በደራሲው ላይ እንደሸፈተ ገጸ ባህሪ መነሻውን እንጂ መድረሻውን ለመገመት አዳጋች ነው፡፡ አበቃላት ተብሎ ደረት ሲደቃ ድንገት ትባንናለች፡፡ ደግሞም ደህና ሆነች ሲባል ተመልሳ ታስጨንቃለች፡፡ በተቃዋሚው ጎራ ለአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ተጠያቂ የሚደረገው በብሔር ላይ የተመሠረተ ፌዴራሊዝም፣ በእነዚህ ወገኖች በሚወደስ ሌላ መድረክ ላይ ሲሞገስ እንሰማለን፡፡

በሕዝብ ውስጥ የጥላቻና የጥርጣሬ ስሜት መፍጠር መወገዝ አለበት

ምትክ ከማይገኝላቸው የተወሰኑ ነገሮች ውስጥ አገርና እናት ይገኙባቸዋል፡፡ ስለዚህም እኛ አገርን እንደ እናት ስለምንቆጥር ኢትዮጵያን እናት አገሬ ብለን እንጠራታለን፡፡ እነዚህን ሁለቱን በሌላ ለመተካት እንኳን ብንሞክር በእንጀራ እናትና በሌላ በምንኖርበት አገር ነው፡፡ እነዚህ ደግሞ እናትም አይደሉም፣ አገርም አይደሉም፡፡ ታዲያ እነዚህ ሁለቱም የሚከበሩትና የሚታፈሩት በልጆቻቸው ነው፡፡ የልጆቻቸው ማንነት ህልውናቸውን ይወስነዋል፡፡

የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እንካ አትንካ ጨዋታ አይደለም

በልማት ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ብዙ ቢሊዮን ብሮችን ያከሰሩ ፕሮጀክቶች ላይ ምንም ዓይነት መንጫጫት ሳይፈጠር አንድ የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ስለተነደፈ በየቤቱ፣ በየመጓጓዣ ሥፍራውና በገበያ ቦታው ብዙ ሕዝብ ተንጫጫ፡፡ መንግሥት የልማት ኢኮኖሚ ስትራቴጂዎቹ አልቀውበት ወደ የገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ እየተንደረደረ ስለሆነ ገና ወደፊት ብዙ እንንጫጫለን፡፡

ቀደም ብለን ስለምርጫ ብንነጋገርስ?

በዳግም አሳምነው ገብረ ወልድ

ሰሞኑን የአገሪቱ የምርጫ ሥርዓት የአብላጫ ድምፅና የተመጣጣኝ ውክልውናን ያቀፈ ‹‹ቅይጥ ትይዩ›› እንዲሆን ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች መስማማታቸው ተሰምቷል፡፡ ለጊዜው ዝርዝሩ ላይ ለመነጋገር ባይቻልም ምርጫን በተመለከተ አንዳንድ ሐሳቦችን ማንሳት ጠቃሚ ነው፡፡

የልማት ኢኮኖሚ ሰው በቅጽበት የገበያ ኢኮኖሚ ሰው አይሆንም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከጥቅምት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በቁጠባ ወለድ መጣኝና በውጭ ምንዛሪ መጣኝ ላይ ማስተካከያ አደረገ ተብሎ በመገናኛ ብዙኃን ተነገረ፡፡ በመርህ ደረጃ ማስተካከያው አስፈላጊ መሆኑን፣ ብዙ ጊዜ በባለሙያዎች አስተያየት ሲሰጥበት እንደነበርና መንግሥት ጆሮ ዳባ ብሎት እንደከረመ ማስታወስ ይቻላል፡፡

አቶ አባዱላ ገመዳና ወቅቱን ያልጠበቀ ከሥራ የመልቀቅ ውሳኔያቸው

ኦሕዴድ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜያት ድረስ የኦሮሞን ሕዝብ በማታገልና በመምራት፣ ለኢትዮጵያ ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ የመጣና እያደረገ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ክቡር አቶ አባዱላ ገመዳም ኦሕዴድን ከውልደቱ እስከ ዕድገቱ  የመሩት፣ ያታገሉትና ፈተናዎችን አልፎ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡

የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች እባካችሁ የልዩነት አጥሩን አፍርሱ

በ፳፩ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ ላይ ዓለም በሥልጣኔ እየገሰገሰ፣ የሳይንስ ሥነ ምርምር የዕደ ጥበብ ግኝቶችን በብዛት እያዥጎደጎደና ተዓምር የሚባሉ እምርታዎችን እያስከተለ ባለበት ወቅት፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት መካከል ግን ከ18 ዓመታት በላይ የዘለቀ ግጭትና አለመግባባት ውስጥ እየዳከሩ ይገኛሉ፡፡