Skip to main content
x

ልጅ እንዳልካቸው መኰንንን የዘከረው ዲቪዲ

ከሦስት ምታመት በፊት የነበረ አንድ ከመሳፍንት ወገን የሆነ ጸሐፊ (ራስ ስምዖን ዘሀገረ ማርያም) ‹‹መጽሐፈ ምዝጋና›› በሚለውና በግዕዝ በተጻፈው ድርሳኑ እንዲህ አስፍሮ ነበር፡፡፡ ‹‹ኢትዮጵያውያን ለምን ታሪካቸውን (ዜናቸውን) አይጽፉም? የውጭዎቹ ይጽፋሉ? የእኛስ? እኔ ግን እጽፋለሁ፤›› በማለት ታሪክን የመጻፍ አስፈላጊነት ያጎላበት ነበር፡፡

የታሪክና የቴዎሎጊያ ፕሮፌሰር ምክረሥላሴ ገብረአማኑኤል (1923 - 2010)

ከአራት ሺሕ ዓመታት የሚያልፈው የኢትዮጵያ ሥነ ጽሕፈት ታሪክ ከድንጋይ ላይ ጽሑፍ ወደ ብራና ላይ ጽሑፍ የተሸጋገረው ቅዱሳት መጻሕፍትን በዘመነ አክሱም ከመጀመርያው እስከ አራተኛው ምታመት መካከል ባሉት ዐረፍተ ዘመናት ውስጥ በመተርጐም ነው፡፡ መጻሕፍቱ ከግሪክና ከሶርያ ከሌሎችም ቋንቋዎች ወደ ግዕዝ ቋንቋ በመተርጐማቸው እስካሁን አገልግሎት እየሰጡ ናቸው፡፡

አነጋጋሪዎቹ የመቅደላ ቅርሶች

መሰንበቻውን ከ150 ዓመታት በፊት በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን በእንግሊዝ ሠራዊት ከመቅደላ አምባ የተዘረፉት ቅርሶች ‹‹ኢትዮጵያ ፍላጎቱ ካላት ለረዥም ጊዜ በውሰት ልንሰጥ እንችላለን›› የሚለውን የቪክቶሪያና አልበርት ሙዚየምን መግለጫ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንደማያውቀው አስታውቋል፡፡

የትንሣኤው ብርሃን

በሔኖክ ያሬድ ‹‹ሽው ሽው ላሌ እሰይ ለዓመት በዓሌ… ታተይ ከቋቱ ላይ ያለው እንቁላል ድመት በላው አንቺ የት ሄደሽ? እኔማ ለገብርዬ ያን እሰጥ ብዬ አግባኝ ሳልለው አግብቶኝ ነጋዴ

‹‹አሳቢው መንግሥቱ ለማ››

‹‹ድሃ፡- እባክዎ ጌታዬ ምፅዋት ያድርጉልኝ ችግር የበዛበት ፍፁም ድሃ ነኝ ጌታ፡- እኪሴ ያለውን የመቶ ብር ኖት እስክመነዝረው ታገሸኝ፤ ድሃ፡- ጌታዬ ይቅርታዎን ልድፈርዎትና ስንት እንደሚሰጡኝ ይንገሩኝ ለገና፤  ጌታ፡- እኔስ የምሰጥህ አንድ ብር ነው ምንዛሪ ታጣ ምን ይሁን ለዛው፤ ድሃ፡- 99 ብር አለኝ በምንቸቴ እዚሁ ይጠብቁኝ መጣሁ በፍጥነቴ ይኼው ይዤ ከተፍ አልኩ አሽከርዎ ኖቱን ይስጡኝና ምላሹን ልስጥዎ፤ ጌታ፡- የኔ ብልፅግና ካንተ ድህነት በአንድ ብር እኮ ነው የሚበልጥበት እንካ ምክር ልስጥህ ሥራ ሥራበት፡፡››

የዲጂታል የምዝገባ ሥርዓት ውስጥ የገባው የቅርስ ጥበቃ

የባህላዊ ቅርሶች የምዝገባና ቁጥጥር ሥርዓት በእንግሊዝኛ አጠራሩ‹‹ ካልቸራል ሔሪቴጅ ኢንቨንተሪ ማኔጅመንት ሲስተም››፣  በቅርቡ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን  ያስመረቀው የመረጃ ቋት (ዳታቤዝ) ሲሆን  ቅርሶች በዲጂታል መንገድ የሚመዘገቡበት ነው፡፡

የግዕዝን ፊደል ለአፋን ኦሮሞ - የምሁራኑ ድምፅ

‹‹አፋን ኦሮሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚናገሩት የኢትዮጵያውያን ሁሉ የሆነ ቋንቋ ነው፡፡ ይኼ ቋንቋ ከኦሮሚያ አልፎ በሌሎች ክልሎች እንደ አንድ ትምህርት መሰጠቱ የበለጠ መግባባትን የበለጠ መቀራረብን የሚያመጣ ብቻ ሳይሆን ቀደም ሲል መደረግ የነበረበት ጉዳይ ነው፡፡››

ባለ ጠልሰሙ

በሰሜን አዲስ አበባ የሚገኘው ገብረክርስቶስ ደስታ የዘመናዊ ሥነ ጥበብ ሙዚየም በጠልሰማዊ ጥበብ ላይ ያተኮረ ዐውደ ርዕይ በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡ የሔኖክ መልካም ዘር ሥራዎችን ያካተተው ዐውደ ርዕይ ከመጋቢት 1 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ እየታየ ነው፡፡

የተክሉ ታቦር ትውስታ

ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን፣ ዜና ለማንበብ አርዕስተ ዜናውን ስጨርስ፣ ስቱዲዮውን በርግደው ወታደሮች ገቡና፣ ‹‹ጣቢያው በቁጥጥር ሥር ውሏል፤›› የሚል ድምፅ አሰሙ፡፡ ቁጥራቸው ወደ አራት ይደርሳል፡፡ ወዲያው ለቴክኒሽያኑ ድምፁን ማስተላለፍ እንዲያቆም ምልክት ሰጠሁት፡፡ የዕለቱ ፕሮግራም አስፈጻሚ ትዕግሥት ንጉሤ ነበረች፡፡ አንደኛው የሻለቃ ማዕረግ ያለው፣ የአርሚ አቪዬሽን መኮንን ይመስለኛል፡፡ ሌላኛውም ስለሺ መኩሪያ ይባል የነበረው የጦር ሠራዊት መኮንን ነበር፡፡