Skip to main content
x

 በታዋቂ ግለሰቦች ማንነት መነገድ

ሰዎች ያዩትንና የተገነዘቡትን በተፈጥሮ ባገኙት የተፈጥሮ ዕውቀት፣ ወይም በትምህርት በቀሰሙት ጠቅላላ ዕውቀት፣ ወይም በልዩ ሥልጠና በተማሩት ሙያዊ ዕውቀት አስድግፈው ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ በሦስቱ ዕውቀቶች አማካይነት የሚነገሩ ነገሮች ልዩነት ያለመርቀቅ ጥሬነትና የመርቀቅ ብስለት ደረጃ ብቻ ነው፡፡

ታሪካዊ አጋጣሚውና ሰዋዊ ስሜቶቻችን

ከ1997 ዓ.ም. ምርጫ ማግሥት ጀምሮ ስለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሒደት ብዙ ተብሏል፡፡ በተለይም እንደ አሜሪካዊው ዶናልድ ሌቪን የመሳሰሉ የጥናትና የጽሑፍ አትኩሮታቸውን በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያደረጉ ‹‹የመከኑት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ዕድሎች›› የሚሉ ሐተታዎችን ብዙ አንብበናል፡፡

የምግብ ዋስትናችን ለከተማም ለገጠርም እኩል ትኩረት መስጠት አለበት

ኢትዮጵያ በምግብ እህል ራሷን መቻሏን ለአገሯና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ካወጀች ሦስት ዓመታት አልፈዋል። 23ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል በአዲስ አበባ ስቴዲየም ሲከበር የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባሰሙት ንግግር፣ ‹‹ዛሬ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ሕዝባችን ባደረገው እንቅስቃሴ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም.

የኢሕአዴግ የውስጥ ምርጫ ትግል መጠናከርና መጪው ተስፋ

ምርጫ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ሕዝብን በመወከል ውሳኔ የሚያሳልፉ ወኪሎችን የመምረጥ ሒደትን የሚያመለክት ሲሆን፣ የተሻሻለው የምርጫ ሕግ አዋጅ 532/1999 በአንቀጽ 1(4) ላይ እንደደነገገው ‹‹ምርጫ›› ማለት በፌዴራልና በክልል ሕገ መንግሥታት፣ እንዲሁም በሌሎች አግባብ ባላቸው ሕጎች መሠረት የሚካሄድ የጠቅላላ የአካባቢ የማሟያ ወይም የድጋሚ ምርጫን የሚያመለክት ነው፡፡

ኢፍትሐዊነትና ሙስና ዋነኞቹ የአገር ጠላቶች በአፋጣኝ ይዘመትባቸው

መሰንበቻውን ኢሕአዴግ ሊቀመንበሩን መርጧል፡፡ ተመራጩ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡ በዚህ ወሳኝ ጊዜ ላይ ሆኖ መጪውን መተንበይ ባይቻልም፣ የአገራችን ጠንቅ ከሆኑት መሠረታዊ ችግሮች መካከል ኢፍትሐዊነትና ሙስና ናቸው ብሎ ለማሰብ፣ እንዲሁም የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስተዳደር ትኩረት ይሆናሉ የሚል እምነት ስላለኝ እንዲህ አቀርባለሁ፡፡

ይድረስ ለክቡራን ሹማምንትና የካቢኔ አባላት

ክቡራን የክልል ፕሬዚዳንቶች፣ የካቢኔ አባላትና ከዚያ በታች የምትገኙ ባለሥልጣናት እነሆ ‹‹ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ›› የሚሉ፣ ‹‹ኢትዮጵያ በሕዝቦቿ ታፍራና ተከብራ ትኖራለች›› የሚሉ፣ ‹‹ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ›› የሚሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመካከላችሁ ብቅ ብለዋል፡፡ ጸሐፊው ‹‹ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ›› የሚል ቅዱስ ቃል እየሰማ ‹‹እንዴት ከእናንተ መሀል እንደዚህ ያለ ሰው ይፈጠራል? እንዴትስ ይሆናል?›› ብሎ ለመጠየቅ አይፈልግም፡፡

ከዓብይ ምን ዓብይ ጉዳይ እንጠብቅ?

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ከሳምንት በላይ የቆየ ስብሰባ አድርጎ የድርጅቱን ሊቀመንበር መርጧል፡፡ ፓርላማውም ሦስተኛውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሰይሟል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ  ሥልጣን መልቀቅ መፈለግ ከተሰማበት ጊዜ አንስቶ ከቀረቡት ዕጩዎች ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በማኅበራዊ ሚዲያና በአንዳንድ ሰዎች አስተያየት ሚዛን የደፉ እንደነበር  ለማየት ተችሏል፡፡ ወደ ሥልጣን እንደመጡ ሲሰማ ከወዲሁ ብዙ እንድንጠብቅ አድርገውናል፡፡

የምን መፍረክረክ ነው?

ፌዴራሊዝም በዓለም ላይ በዋናነት ከሚታወቁ ሌሎች ሁለት መንግሥታዊ ቅርፆች አንዱ ነው፡፡ አንድ ወጥ የሆነ መንግሥት (Unitary State)፣ ፌዴራላዊ መንግሥት (Federal State) እና ኮንፌዴሬሽን (Confederal State) የሚባሉት ናቸው፡፡

የተጠናወቱን ችግሮች የሚፈቱት ማስተዋል በተሳነው ረብ የለሽ መፍትሔ አይደለም

ኢትዮጵያ በብዙኃንነት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ ቁጥርም ትልቅና ሰፊ የምትባል አገር ነች፡፡ ከ80 የማያንሱ የራሳቸው ባህል፣ ቋንቋና ማንነት ያላቸው ብሔር ብሔረሰቦችና በጥቂት ዓመታት ውስጥ 100 ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ ያላት አገር መሆኗን ያስታውሷል፡፡ እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ የዓለም ጭራ ደሃ አገር፣ በጦርነትና በኋላ ቀርነት የኖረች ምሥራቅ አፍሪካዊት ቀደምት ምድር የሚል ስያሜ ተሰጥቷት ቢቆይም፣ አሁን አሁን በሌላ ገጽታ ስሟ እየተነሳ ይገኛል፡፡

በመደማማጥ ወደ ዴሞክራሲያዊነት እንመለስ!

አገራችን የረዥም ዘመን ታሪክ ውስጥ ብዝኃነትን በማያስተናግዱ ሥርዓቶች ምክንያት ለእርስ በርስ ግጭቶች ስትዳረግ መቆየቷ አይታበልም። በተለያዩ ዘመናት  ረዥም ጊዜን የወሰዱ፣ የሰው ሕይወትና ሀብት ያወደሙ ጦርነቶችም ሲስተናገዱ ነበር። ይህ እውነት ለዘመናት ተጫጭኖን ስለነበርም ለድህነት ምንጭ ሆኖብን እንደቆየ   አይዘነጋም። በእርስ በርስ ግጭቶቻችንና በድህነታችን ምክንያትም ለውጭ ጠላቶች  ተጋላጭ የሆንንባቸው ወቅቶችም በርካታ ናቸው።