| 11 April 2018 ‹‹የታኅሣሥ ንቅናቄ የተጀመረው ንጉሠ ነገሥቱን በመጥላት ሳይሆን ኢትዮጵያ እንድትሻሻልና ከሌላው ጋር እኩል እንድትሆን በማሰብ ነው›› ብርጋዴር ጄኔራል ደስታ ገመዳ በክብር ዘበኛ ጦር አካዴሚ ሠልጥነው ከወጡ የመጀመርያው ዙር ተመራቂዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ መታሰቢያነቱ እሳቸውን ጨምሮ የአካዴሚው የመጀመርያ ኮርስ የጦር መኰንኖች የሆነና ታሪካቸውን የሚያወሳ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 4 April 2018 ሮቦትን በኢትዮጵያ የማስረፅ ጉዞው አቶ ሰናይ መኰንን የአይከን ኢትዮጵያ ሮቦቲክስ ኤዱኬሽን ኤንድ ኮምፒቲሽን ማዕከል መሥራች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. በ2011 የተመሠረተው አይከን ኢትዮጵያ ታዳጊዎችን በዲዛይን ኢንጂነሪንግና ፕሮግራሚኒንግ የማብቃት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የማስቻል ሥራ ይሠራል፡፡ ድርጅቱ ለታጊዎቹ መሠረታዊ የሮቦቲክስ ጽንሰ ሐሳብና ሌሎች ወሳኝ ቀመሮችን ካስተማረ በኋላ እርስ በርስ እንዲወዳደሩ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ወጥተው በሌላው የዓለም ጫፍ ከሚገኙ አቻዎቻቸው እንዲወዳደሩ ያደርጋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 28 March 2018 የኢትዮጵያዊው ሳተላይት በአፍሪካ ሕዋ ውስጥ አቶ ኖኅ አዝሚ ሳማራ በሳተላይት ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚሠራና አዝሚ ዩኤስኤ ኤልኤልሲ ኩባንያ መሥራች፣ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ተወልደው ያደጉት እዚሁ አዲስ አበባ ሲሆን፣ የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመርያና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ተወልደው ባደጉበት ከተማ አዲስ አበባና ዳሬሰላም ታንዛኒያ ውስጥ ነው፡፡ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ እንግሊዝ አገር አቅንተው የመሰናዶ ትምህርታቸውን ተከታተሉ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 21 March 2018 የወንድማሞቹ ስጦታ አቶ ሙላት ፎጌ የአማጋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ድርጅታቸው በማምረት፣ በትራንስፖርትና በወጪና ገቢ፣ እንዲሁም በሌሎች የንግድ ዘርፎች ላይ የተሠማራ ድርጅት ነው፡፡ ድርጀቱም በቤተሰብ የተቋቋመ ነው፡፡ በጣና ሐይቅ ላይ የተንሰራፋውን የእንቦጭ አረም ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ድርጅታቸው ‹‹ለመጀመርያ ጊዜ›› የእንቦጭ አረም መከላከያ ማሽን ከቻይና ከሁለት ሚሊዮን ብር በመግዛት አገር ውስጥ አስገብቷል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 14 March 2018 የአምስት ዜና መዋዕሎች ትሩፋት በግእዝ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ሁነኛ ሥፍራ ያለው የነገሥታት ውሎና ጉዞ የሚያትተው ዜና መዋዕል በተለይ ከ14ኛው ምዕት ጀምሮ ከሙያ መዋሉ ይገለጻል፡፡ ይሁን እንጂ ቀደም ባሉት ዘመናት በአክሱም ከመጀመርያ መቶ ዘመን ወዲህም ታሪክ ጠቀስ ጽሑፎች በድንጋይ ላይም ሆነ በብራና ላይ ለመጻፋቸው ማስረጃዎች አሉ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 7 March 2018 ባንክ ለማቋቋም የሰነቀው የጥቃቅንና አነስተኛ አሠሪዎች ፌዴሬሽን የጥቃቅንና አነስተኛ አሠሪዎች ፌዴሬሽን ራሱን ችሎ በፌዴሬሽን ደረጃ የተቋቋመው አምና 2009 ዓ.ም. ነበር፡፡ በመላው አገሪቱ በጥቃቅን፣ ታዳጊና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተደራጁ 2000 ማኅበራት አማካይነት የተመሠረተ ነው፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 28 February 2018 ‹‹የመስተንግዶ አገልግሎት ባለው መልኩ ከቀጠለ ሆቴል መገንባቱ ዋጋ የለውም›› አቶ ዜናዊ መስፍን የሆቴል ባለቤቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዚዳንት ናቸው፡፡ ወደ መስተንግዶ (ሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ) የተቀላቀሉት በአጋጣሚ ነበር፡፡ በባህር ማዶ የተከታተሉትን ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ አውስትራሊያ በሚገኘው ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተቀጠሩ፡፡ በሆቴሉ ቆይታቸው በኦዲተርነትና በዋና ኃላፊነት መሥራት ችለዋል፡፡ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ከዘጠኝ ዓመት በፊት ሲሆን፣ እንደመጡ የኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 21 February 2018 ‹‹ሌላው ዓለም የቡናን ጥራት እንዴት መጠበቅ እንዳለበት ራሱን ሲያሻሽል እኛ ግን ቆመናል ›› አቶ አማን አድነው፣ የመታድ እርሻ ልማት ድርጅት ባለቤት አቶ አማን አድነው ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ባደረገው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ አቅራቢ ድርጅት በዲኤች ኤልና እዛው በሚገኘው በኖርዝ ዌስት አየር መንገድ በኃላፊነት ደረጃ የሠሩ ሲሆን፣ በተባበሩት መንግሥታትና በኢትዮጵያ የኢሲኤክስ ቺፍ ኦፕሬተር በመሆን ሠርተዋል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 14 February 2018 ‹‹አንድ ድርጅት አክሬዲቴሽን ሲሰጠው ያለምንም ጥርጥር ተቀበለው የሚል መልዕክት አለው›› አቶ አርአያ ፍሥሐ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት የተቋቋመው በ2003 ዓ.ም. ሲሆን፣ በጀት ተመድቦለት መንቀሳቀስ የጀመረው ግን በ2004 ዓ.ም. ነው፡፡ መሥሪያ ቤቱ ራሱን ችሎ እንዲወጣ የተደረገው መሠረታዊ የሥራ ሒደት ለውጥ በተጀመረበት ወቅት ነበር፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ
| 7 February 2018 ‹‹የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሕይወት ትልቅ ዋጋ እንድሰጠው አድርጎኛል›› ወጣት መላኩ ኃይሉ ተወልዶ ያደገው፣ የመጀመሪያና የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን የተከታተለው አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ በሶሺዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በተለያዩ ዘርፎች በበጎ ፈቃድ ሥራና የበጎ ፈቃደኞች መሪና አስተባባሪ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡ እያበረከተ ካለው አገልግሎትና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ታደሰ ገብረማርያም አነጋግሮታል፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ