- የማኅበሩ አመራሮችም በፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ
- አያት ከ86 ሚሊዮን ብር በላይና የኮንስትራክሽን መሣርያዎች እንዲወረሱበት ተወስኗል
በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በተመሠረቱባቸው 23 ክሶች ለሦስት ዓመታት ከተከራከሩ በኋላ በቅርቡ በ21 ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት አያት አክሲዮን ማኅበርና ሦስት አመራሮች፣ በዛሬው ዕለት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል ችሎት ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትና ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው፡፡
“ወንበር ለማሞቅ አይደለም… አልቻልንም ብለን እናስረክባለን” የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የመንግሥትን ገንዘብ ማስመለስ ባልቻለው የፕራይቬይታይዜሽንና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ኃላፊዎችን በመጥራት ወቀሰ፡፡
- የናዝሬትና የሚሌ ጉምሩክ ሥራ አስኪያጆች ተካተውበታል
- ተጠርጣሪዎች በድብደባና በግዳጅ ቃል እንዲሰጡ መደረጋቸውን ተናገሩ
ከሕገወጥ ነጋዴዎች፣ አስፈጻሚዎችና ከትራንዚት ድርጅቶች ጋር በመመሳጠር በሕገወጥ መንገድ ከናዝሬት ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ሳይፈተሹ እንዲያልፉ በማድረግ፣ ሕገወጥ ጥቅም በማግኘትና ሀብት በማከማቸት የተጠረጠሩ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የአዳማና የሚሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጆችን ጨምሮ በጠቅላላው 54 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽንና በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ትብብር በቁጥጥር ሥር የዋሉ ባለሥልጣናት፣ ነጋዴዎች፣ ደላሎችና የጉምሩክ ሥርዓት አስፈጻሚዎች የባንክ ሒሳባቸውን እንዳይንቀሳቀስ ኮሚሽኑ ለባንኮች ደብዳቤ መላኩን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡
- እስካሁን በርካቶች አልተገኙም
ከጣና ሐይቅ ቁንዝላ ወደብ ወደ ጐንደር አቅጣጫ ወደ ዳልጊ ወደብ ባለፈው ሰኞ ምሽት ሲያመራ የነበረው ፋሲለደስ ተብሎ የሚጠራው ጀልባ፣ ወደ ወደቡ ለመድረስ 100 ሜትር ያህል ሲቀረው በመገልበጡ ካሳፈራቸው ከመቶ በላይ መንገደኞች ውስጥ ስድስት ያህሉ መሞታቸውን፣ ከክልሉ ከተገኘው መረጃ ማወቅ ተችሏል፡፡
ሚድሮክ በኦሮሚያ ክልል ደርባ አካባቢ ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ ከመገንባቱ በፊት፣ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን አካባቢ ያቋቋመው የሲሚንቶ ፋብሪካ ሥራ አቁሟል፡፡
የዛሬ ዓመት ግንቦት 20 ቀን ሥራውን በይፋ የጀመረው ጂኤች ኢንዱስትሪያል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በኤሌክትሪክ ኃይልና በውኃ አቅርቦት እጦት ምክንያት ሊዘጋ መቃረቡን አስታወቀ፡፡
‹‹በቤኒሻንጉል የአማራ ተወላጆችን ያፈናቀሉ 35 አመራሮች ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርገዋል›› የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
-መረጃ የተገኘባቸው 12 አመራሮች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ተባለ
-ተመሳሳይ ማፈናቀል በደቡብ ክልል መከሰቱ ተጠቆመ
የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ክልል ተወላጆችን ያፈናቀሉ 35 የክልሉ አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውንና ተፈናቃዮቹን በግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቁ መደረጉን አስታወቀ፡፡
• በዘጠኝ ወራት 2.1 ቢሊዮን ዶላር ከሐዋላ ተገኝቷል
ከሐዋላ (ሬሚታንስ) እየተገኘ ያለው የውጭ ምንዛሪ ከአገሪቱ የወጪ ንግድ እየተገኘ ካለው የበለጠ የዕድገት መጠን እየታየበት መሆኑ ተመለከተ፡፡
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ በቅርቡ በጥናት በማስደገፍ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ የፖለቲካ ፕሮግራሙንና አንዳንድ መሪዎቹን በመንቀፉ ምክንያት ጠንከር ያለ አለመግባባት ተከስቷል፡፡
