አቶ ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለአፍሪካዊ አየር መንገድ መሥራት የሚያስደስታቸው በመሆኑ ሹመቱን ተቀብለዋል፡፡ አክለውም የሩዋንዳ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተባብሮ በሚሠራበት ሁኔታዎች ላይ እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
አቶ ግርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለ40 ዓመታት ያህል ካገለገሉ በኋላ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ጡረታ ወጥተዋል፡፡ ቀድም ሲል በዲኤችኤልና በገልፍ ኤር በከፍተኛ ኃላፊነት ማገልገላቸው ይታወሳል፡፡ አቶ ግርማ የአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴልና የኅብረት ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ናቸው፡፡


