Skip to main content
x

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ 771 ሰዎች ከእስር ተፈቱ

በሽብርተኝነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት እነ አቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ፣ 771 ተከሳሾችና ፍርደኞች በይቅርታና ክስ በማቋረጥ ከእስር እንዲፈቱ ተደረገ፡፡

‹‹ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ተመሳሳይ ሪፖርት እያቀረብኩ ስለሆነ እንድትሰሙኝ እፈልጋለሁ›› ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ

ከተሾሙ አንስቶ ለዘጠነኛ ዓመታት ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርታቸውን ለፓርላማ ያቀረቡት ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ፣ ለዘጠነኛ ዓመት ተመሳሳይ ሪፖርት እያቀረቡ መሆኑን በመጥቀስ የፓርላማ አባላት እንዲሰሟቸውና ግፊት እንዲያደርጉ ጠየቁ፡፡

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር አዲስ አበባ ከባድ የውኃ እጥረት ያጋጥማታል ተባለ

በውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና አመዳደብ ችግር ምክንያት አዲስ አበባ ከተማ ከአንድ ዓመት በኋላ ከበድ ያለ የንፁህ ውኃ አቅርቦት ችግር ሊገጥማት ይችላል ተባለ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 46 ሚሊዮን ዶላርና ስድስት ሚሊዮን ዩሮ ቅድሚያ ተሰጥቶት እንዲቀርብለት በተደጋጋሚ ቢጠይቅም ምላሽ እንዳልተሰጠው አስታውቋል፡፡

አገር በቀል አምራቾች ብሔራዊ ባንክ እነሱን ያገለለ ለውጭ ኩባንያዎች ብቻ የሚስማማ መመርያ ተግባራዊ ማድረጉን ተቃወሙ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የውጭ አቅራቢዎች የዱቤ ሽያጭ መመርያ፣ አገር በቀል አምራቾችንን ያገለለና የውጭ ባለሀብቶች እንደ ልባቸው ጥሬ ዕቃና ሌሎችም ግብዓቶችን ማስገባት እንዲችሉ የሚያስችላቸው ነው ሲሉ የአገር ውስጥ አምራቾች ተቃውሞ አሰሙ፡፡ በመመርያው መደናገጣቸውን በመግለጽ ጭምር አቤቱታቸውን ለመንግሥት አቅርበዋል፡፡

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ሠራተኞች ግድያ ሰባት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

በቅርቡ በዳንጎቴ ሲሚንቶ ሠራተኞች ላይ ከተፈጸመው የግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ሰባት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ታወቀ፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በወንጀሉ የተጠረጠሩ ሰባት ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋለ ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ አንዱ የዳንጎቴ ሲሚንቶ የከባድ መኪና አሽከርካሪ እንደሆነ፣ የተቀሩት የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ምንጮች አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ሩዋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ የመጀመርያው የአገር መሪ በመሆን ለሦስት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙትን የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜን፣ ዓርብ ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. በታላቁ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ሐሙስ ዕለት ምሽት አዲስ አበባ ሲገቡ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ሲኖትራክ ለመግዛት የከፈሉትን ገንዘብ የተጭበረበሩ 98 ሰዎች የፍትሕ ያለህ እያሉ ነው

ከሁለት ዓመታት በፊት ዙና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ በሦስት ወራት ውስጥ ሲኖትራክ ገልባጭ መኪና ገዝቶ እንዲያስረክባቸው ተስማምተው ሙሉና ግማሽ ክፍያ ከከፈሉት በኋላ፣ መጭበርበራቸውን ያወቁ 98 ግለሰቦች የፍትሕ ያለህ እያሉ ነው፡፡ ግለሰቦቹ ግማሽ ክፍያና ሙሉ ክፍያ ፈጽመው ተሽከርካሪያቸውን ለመረከብ በመጠባበቅ ላይ እያሉ የማኅበሩ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን ጌታሰው ከአገር መውጣታቸውን እንደሰሙ፣ ያለውን ንብረትና ተሽከርካሪዎች እንዳይሸጡ፣ እንዳይለወጡና ለሦስተኛ ወገን እንዳይዘዋወሩ ክስ መሥርተው አሳግደው እንደነበር ይናገራሉ፡፡

የእነ አቶ መላኩ ፈንታና የእነ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ ክስ እንዲቋረጥ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ቀረበ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአዋጅ ቁጥር 943/2008 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ በሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የእነ አቶ መላኩ ፈንታና የእነ አቶ ዓለማየሁ ጉጆ መዝገብ ተከሳሾች ክስ እንዲቋረጥ ለፍርድ ቤት አቀረበ፡፡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታና ምክትላቸው አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ ከነባለቤታቸው፣ ከነጋዴዎች የአቶ ከተማ ከበደ፣ የእነ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር፣ የአቶ ጌቱ ገለቴና ሌሎችም ክስ እንዲቋረጥ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ቀርቧል፡፡

‹‹አዲሱን ትውልድ በአሮጌ አስተሳሰብ መምራት አይቻልም›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ግንቦት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ ማይንድሴት ኮንሰልት በተባለ ድርጅት የተዘጋጀው የአዲስ አስተሳሰብ ዝግጅት ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ አዲሱን ትውልድ በአሮጌ አስተሳሰብ መምራት አይቻልም አሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሳዑዲ ዓረቢያ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀው ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እንደ ደረሱ በቀጥታ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሲመጡ፣ ዝግጅቱን ለመታደም ለተገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ድንገተኛ ነበር የሆነባቸው፡፡

አቶ ጌታቸው አምባዬ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆነው ተሾሙ

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የነበሩት አቶ ጌታቸው አምባዬ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሕግ አማካሪ ሆነው ተሾሙ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዲሱ ካቢኔ ባለመካተታቸው ርዕሰ ጉዳይ ሆነው የቆዩት አቶ ጌታቸው፣ ከግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆነው መሾማቸውን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡