በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ግዥ ስምምነት ታኅሳስ 10 ቀን 2010 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ተፈርሟል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርቤቲ ጂኦተርማልና ቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ከተባሉ ሁለት የኢንቨስትመንት ኩባንያዎች፣ ከከርሰ ምድር እምቅ የእንፋሎት ኃይል የሚያመነጩትን 1,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለ25 ዓመት ለመግዛት ተስማምቷል፡፡ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ዲፕሎማቶችና የኩባንያዎቹ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡