Skip to main content
x

ኢራፓ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ራሱን አገለለ

አገር ዓቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአንድ ዓመት ያህል ከኢሕአዴግ ጋር እያደረጉት ካለው ድርድር የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ራሱን እንዳገለለ አስታወቀ፡፡ ኢራፓ ይህንን ያስታወቀው ዛሬ ጥር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ፓርቲዎቹ በፀረ ሽብር ሕጉ ላይ ለመወያየት በተሰበሰቡበት ወቅት ነው፡፡

‹‹እስካሁን ባደረግነው አጠቃላይ የድርድር ሒደት የምናቀርበው ሐሳብ ተቀባይነት እያገኘ ባለመምጣቱ ኢራፓ እየተካሄደ ካለው የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር ራሱን አግልሏል፤›› ያሉት የፓርቲው ተወካይ፣ ከዛሬ በኋላ በድርድሩ ላይ አንገኝም በማለት ከመሰብሰቢያ አዳራሹ ወጥተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የግብፅ ጉብኝት ፋይዳ

የኢትዮጵያና የግብፅ ግንኙነት በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ገጽታዎች እንደነበራት ታሪክ ያስረዳል፡፡ ሁለቱ አገሮች ጥንት የጦር መሣሪያ የተማዘዙት ጊዜ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ በ2003 ዓ.ም. የህዳሴ ግድቡን የመሠረት ድንጋይ ከጣለችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ግብፅ የተለያዩ ፖሊሲዎችን ስትከተልና የተለያዩ ሐሳቦችን ስታራምድ መቆየቷን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ በፊት የነበሩት መሐመድ ሙርሲ መሪዎች ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡን ግንባታ እንድታቆም ከማስፈራራት ባሻገር፣ ግብፅ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ብድርም ሆነ ድጋፍ እንዳያደርጉ ስትወተውት ቆይታለች፡፡ አብዱልፈታህ አልሲሲ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህም ቢሆን የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ የተለያዩ አወዛጋቢ አስተያየቶችን ሲሰጡ ተደምጧል፡፡ ‹‹የናይል ወንዝ ለግብፃውያን የሞትና ሽረት ጉዳይ ነው፤›› ከማለት ባሻገር፣ ‹‹በግብፅ የውኃ ሀብት ላይ ማንም ጣልቃ እንዲገባ አልፈቅድም፤›› ሲሉ መደመጣቸው አይዘነጋም፡፡

ፌዴራል ዋና ኦዲተር በኤሌክትሪክ አገልግሎት ላይ የሚታዩ ችግሮችን በፅኑ ተቸ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከአሥር ዓመታት በላይ እየተንከባለሉ የመጡ ያልተከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎችን መሰብሰብ እንዳልቻለ፣ ለማስከፈልም ምንም ዓይነት ዕርምጃዎች እንዳልተወሰዱ አስታወቀ፡፡ ይህ የተባለው የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በአገልግሎቱ ከ2006 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም. የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋነትንና ውጤታማነትን ለመገምገም ያካሄደውን ኦዲት ሪፖርት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ጥር 9 ቀን 2010 ዓ.ም. ባቀረቡበት ጊዜ ነው፡፡

ከንፋስ አመጣሽ ታክስና ከልማት ድርጅቶች ሽያጭ የሚገኝ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ሆኖ ቀረበ

የብር ምንዛሪ ተመን እንዲቀንስ በመደረጉ የአገሪቱ ባንኮች ከነበራቸው ተቀማጭ የዶላር ክምችት ካገኙት ድንገተኛ ትርፍ ላይ መንግሥት በንፋስ አመጣሽ ታክስ ከሚያገኘው ገቢ፣ እንዲሁም ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሽያጭ እንደሚገኝ የታሰበ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት በጀት እንዲሆን ተጠየቀ፡፡ ባለፈው ሳምንት የሚኒስትሮች ምክር ቤተ ያፀደቀው ይህ የተጨማሪ በጀት፣ ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ፓርላማው እንዲያፀድቀው ቀርቧል፡፡

የአፍሪካ መሪዎች በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ በአዲስ አበባ ይመክራሉ

ከጥር 14 እስከ ጥር 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 30ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያካሄድ፣ ኢትዮጵያም ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስከብርባቸው ውይይቶች እንደሚደረጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት ወደ ሥልጣን ከመጡ ለመጀመርያ ጊዜ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ ነው፡፡ በአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የአኅጉሪቱን የተለያዩ ችግሮች ከመፍታት አንፃር ጠቃሚ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ገልጸው፣ መሪዎቹም በዋነኝነት በአምስት ቁልፍ አጀንዳዎች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ አስረድተዋል፡፡

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰባት ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ተማሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት፣ ሰባት ተማሪዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አዳነ ኃይሌ (ዶ/ር) ማክሰኞ ጥር 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በተፈጠረው ግጭት በሰባት ተማሪዎች ላይ ጉዳት በመድረሱ ወደ ሆስፒታል ተልከዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል በአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ረቂቅ አዋጅ ላይ ለፓርላማ ያቀረበው የሕጋዊነት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

የኦሮሚያ ክልል በፌዴራል መንግሥት ተረቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ረቂቅ አዋጅ ሕገ መንግሥታዊ  አለመሆኑን በመጥቀስ እንዳይፀድቅ በተደጋጋሚ ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ፣ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከፍተኛ ማሻሻያ ተደርጎ በፓርላማው ፀደቀ። የኦሮሚያ ክልል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ረቂቅ አዋጁ በሕገ መንግሥቱ ለክልሎች የተሰጠውን ሥልጣን ከግምት ያላስገባና ለመተግበር አስቸጋሪ ሆኖ በመዘጋጀቱ ሊፀድቅ እንደማይገባው በመጥቀስ የሕግ ሰነዱን ላመነጨው የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለሥልጣን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር እየተመለከተ ለነበረው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ አቤቱታውን በደብዳቤ በተደጋጋሚ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል።

በወልዲያ ከተማ በተቀሰቀሰው ግጭት የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በወልዲያ ከተማ ቅዳሜ ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. ታቦት አጅበው ሲሄዱ በነበሩ ወጣቶችና በወቅቱ በሥምሪት ላይ በነበሩ የፀጥታ ኃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት፣ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ ተከስቶ በነበረው ግጭት ከሰባት ሰዎች ሕይወት ሕልፈት በተጨማሪ፣ የከተማዋን ከንቲባ መኖሪያ ቤት ጨምሮ የተለያዩ የንግድ ተቋማት በእሳት መውደማቸው ሲረጋገጥ፣ በግጭቱ ምክንያት የአንድ የፀጥታ አባልና የስድስት ግለሰቦች ሕይወት መጥፋቱም ታውቋል፡፡

በሱዳንና ሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር መንግሥት እንቅስቃሴ ጀመረ

በፈጸሙት ወንጀል ተፈርዶባቸው በሱዳንና በሳዑዲ ዓረቢያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ ለማዘዋወር፣ መንግሥት እንቅስቃሴ መጀመሩን የሪፖርተር ምንጮች አመለከቱ፡፡ ለጉዳዩ በጣም ቅርብ የሆኑ የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት ፍርደኛ ኢትዮጵያውያኑን ከሱዳንና ከሳዑዲ ዓረቢያ እስር ቤቶች ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤቶች ለማዘዋወር በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው፣ ሕጋዊ ሥልጣን ያለው የአገሪቱ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ተቋም ነው፡፡

በገቢዎች ጽሕፈት ቤት ቃጠሎ ምክንያት የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ከምክትላቸው ጋር ከሥልጣን ተነሱ

ኅዳር 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ጽሕፈት ቤት በእሳት ቃጠሎ ከወደመ በኋላ፣ ተገቢውን ዕርምጃ አልወሰዱም በሚል ምክንያት የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ አኬኔ ኦፓዳ እና ምክትላቸው አቶ ጀምስ ኬች ከሥልጣናቸው ተነሱ፡፡ የጋምቤላ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋሕዴን) ለሳምንት ያህል ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቶ፣ ጥር 10 ቀን 2010 ዓ.ም. የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባና ምክትላቸው ጥፋተኞች ናቸው በማለት ከሥልጣናቸው ማንሳቱ ታውቋል፡፡