Skip to main content
x

ሜቴክ በያዛቸው የስኳርና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ላይ መንግሥት የመጨረሻ ውሳኔ እንዲሰጥ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በተደጋጋሚ ጊዜ ቢራዘምለትም ሊያጠናቅቅ ያልቻላቸውን አንድ የስኳርና አንድ የአፈር ማዳበሪያ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ፣ መንግሥት ውሳኔ እንዲሰጥበት ጥያቄ መቅረቡ ተገለጸ፡፡ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ግርማ አመነቴ (ዶ/ር) ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን ለፓርላማ ሲያቀርቡ እንደተናገሩት፣ የጣና በለስ ቁጥር ሁለት የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክት ከሜቴክ ተነጥቆ በአዲስ ኮንትራክተር ሥራውን ለማስቀጠል እየተመከረ ነው፡፡

‹‹ትግራይ ያለ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ያለ ትግራይ ትርጉም የላቸውም›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እያደረጉ የሚገኘውን ጉዞ ዓርብ ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በመቀጠል መቐለ ከተማ ተገኝተው ለከተማው ነዋሪዎች ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸው በዚህም ትግራይና ኢትዮጵያ የተሳሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ‹‹ትግራይ ያለ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያም ያለ ትግራይ ትርጉም የላቸውም፤›› ብለዋል፡፡

በሽብር ወንጀል ተግባር ተጠርጥረው የተከሰሱት የዋልድባ መነኮሳት ከእስር ተፈቱ

ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅት የገንዘብ ዕርዳታ በማድረግና ሌሎች የሽብር ወንጀል ተግባር ተጠቅሶባቸው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት ሁለት የዋልድባ መነኮሳት፣ መንግሥት ክሳቸው እንዲቋረጥ በማድረጉ ዓርብ ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ከእስር ተፈቱ፡፡ የሌሎች 112 ተከሳሾችም ክስ በመቋረጡ ከእስር ተፈተዋል፡፡

ፓርላማው የዘንድሮን ምርጫ ያራዘመበት ሒደት የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዘንድሮ መካሄድ የነበረበትን የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተሞች ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫን ያራዘመበት መንገድ የሕጋዊነት ጥያቄ አስነሳ፡፡ ምክር ቤቱ ሐሙስ ሚያዝያ 4 ቀን 2010 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ ዘንድሮ መካሄድ የነበረበት ምርጫ ለ2011 ዓ.ም. እንዲሸጋገር በስምንት ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል፡፡

በዓድዋ ጦርነት የተሰው ጀግኖችን አፅም በክብር ለማሳረፍ ታሰበ

በዓድዋ ጦርነት የተሰው ጀግኖችን አፅም በጅምላ ከተቀበሩበት ሥፍራ አንስቶ በክብር ማኖር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው ሚያዝያ 5 ቀን 2010 ዓ.ም. በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡ የዚህ ሐሳብ መነሻም በአካባቢው በተደረገ ጥናት ምንድብድብ በሚባል ሥፍራ፣ በጅምላ ተቀብረው የተገኙ የዓድዋ ጀግኖች አፅሞች በቁፋሮ ወቅት እንደ ነገሩ ሆነው በመገኘታቸው ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤምባሲዎችን ካርታ ለማምከን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋገረ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተለያዩ ግንባታዎች መሬት ከሊዝ ነፃ ወስደው ሳያለሙ ለዓመታት አጥረው ያስቀመጡ 18 ኤምባሲዎችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ይዞታ ላይ በሚወሰደው ዕርምጃ ላይ፣ ባለፈው ሳምንት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ተነጋገረ፡፡

የዕርቀ ሰላም ጅማሬ

ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ሶማሌ ክልል ያቀኑት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አጋጥሞ የነበረው ግጭት ‹‹ያልተገባ፣ ከኢትዮጵያዊነት ባህል ያፈነገጠና የሁላችንንም አንገት ያስደፋ የሽንፈት ታሪካችን ነው፤›› በማለት ከኅብረተሰቡ ለተወከሉ የኮንፈረንስ ተሳታፊዎች ንግግር አድርገው ነበር፡፡ ከሁለቱም ክልሎች በርካታ ዜጎች ለሕልፈት የተዳረጉበትን፣ በርካቶች ለአካል ጉዳት የተጋለጡበትንና ከ700 ሺሕ በላይ የተፈናቀሉበትን ግጭት በዕርቀ ሰላም እንዲቋጭም ጥሪ አቅርበዋል፡፡