Skip to main content
x

የኢትዮጵያና የኤርትራ የወደፊት ተስፋና የወቅቱ ፈተና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር ከጠቀሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታትን ግንኙነት የተመለከተ ነበር፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር አዲስ ማስተር ፕላን እያዘጋጀ ነው

ለረዥም ዓመታት ዕድገቷ ተገቶ የቆየችው የድሬዳዋ ከተማ አዲስ የተዘረጋው የኢትዮ ጂቡቲ የባቡር መስመርና በመገንባት ላይ ያለው ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርክ ሕይወት እየዘራባት በመሆኑ፣ አዲስ የከተማ ማስተር ፕላን በማዘጋጀት ላይ መሆኑን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የቀድሞ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር በስኳር ኮርፖሬሽን ተጠርጣሪዎች ላይ ምስክር ሆነው ቀረቡ

በሚኒስትር ማዕረግ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አማካሪና የቀድሞ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስትር፣ ዓቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ በመሠረተባቸው በኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሸን የኦሞ ኩራዝ 5 ስኳር ፕሮጀክት ተጠርጣሪዎች ላይ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡

በህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም ኃይል ለማመንጨት ዕቅድ አለ

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በመጪው መስከረም 2011 ዓ.ም. ኃይል እንዲያመነጩ ዕቅድ መያዙን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ። የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት የሁለቱን ተርባይኖች ተከላ ለማጠናቀቅ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡ በመሆኑም በመስከረም ወር 2011 ዓ.ም. ተርባይኖቹ ኃይል ማመንጨት እንዲጀምሩ ዕቅድ ተይዟል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ጅግጅጋ አመራ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የተመራ የልዑካን ቡድን ቅዳሜ መጋቢት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ድንበር አካባቢ ላይ ተከስቶ የነበረውን ግጭት በዘላቂነት ለመፍታት ወደ ጅግጅግ አቅንቷል፡፡

የዜጎች ማሰቃያ መሆኑ የሚነገርለት ማዕከላዊ ተዘጋ

ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋና ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ 11 ግለሰቦች ከእስር ተፈቱ፡፡ በጣልያንና በኢትዮጵያውያን መሃንዲሶች እንደተገነባ የሚነገረው በተለምዶ ማዕከላዊ ተብሎ የሚጠራው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል ከመጋቢት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ መዘጋቱ ታወቀ፡፡

በሱዳን ሲካሄድ የነበረው የሚኒስትሮች ስብሰባ ያለውጤት ተበተነ

የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውጭ ጉዳይና የውኃ ሀብት ሚኒስትሮች በህዳሴ ግድቡ ውኃ አሞላልና አለቃቀቅ እንዲሁም የግድቡን አካባቢያዊ ተፅዕኖን በተመለከተ በሱዳን ካርቱም ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ሲካሄድ የነበረው ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቀቀ፡፡

ሪፖርተር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ማረጋገጥ እንደቻለው፣ ስብሰባው ሊቋረጥ የቻለው በዓባይ ውኃ ክፍፍል ላይ ከግብፅ በተነሳ ጥያቄ ምክንያት ነው፡፡

እነ እስክንድር ነጋ የዋስትና መብት ቢከበርላቸውም አልተፈቱም

እሑድ መጋቢት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ዓርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ በመጠቀማቸው ምክንያት በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌና ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ 11 ግለሰቦች በዋስትና እንዲፈቱ ቢፈቀድላቸውም፣ እስካሁን እንዳልተፈቱ ቤተሰቦቻቸው ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ንግግር

ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን ዳሰዋል፡፡ የንግግራቸው ሙሉ ቃል እንደሚተከለው  ቀርቧል፡፡