Skip to main content
x

በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚደረገው ውይይት በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ይካሄዳል

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርጉት ውይይት በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ እንደሚካሄድ ታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ውይይት ለማድረግ ቀነ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡ ሦስቱ አገሮች የሚያደርጉት ውይይትም በተያዘለት ቀን እንደሚካሄድ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

ቀዳማዊ ቤተሰብ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር፣ በሕዝብ ዘንድ ትኩረትን ከሳቡት ጉዳዮች መካከል የቤተሰብ ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ የሰባት ዓመት ልጅ እያሉ ሩቅ፣ ጥልቅና ረቂቅ ራዕይ በውስጣቸው የተከሉትን፣ ያሳደጓቸውንና ለፍሬ ያበቋቸውን ወላጅ እናት ለማመሥገን እንዲፈቀድላቸው ሲጠይቁ ብዙዎች ልባቸው ተነክቷል፡፡ እናታቸው ከሌሎቹ ቅን፣ የዋህና ጎበዝ ኢትዮጵያውያን እናቶች እንደ አንደኛቸው የሚቆጠሩ፣ ቁሳዊ ሀብትና ዓላማዊ ዕውቀት እንደሌላቸው፣ በእናታቸው ውስጥ ሁሉንም የኢትዮጵያ እናቶች ዋጋና ምሥጋና እንደ መስጠት በመቁጠር፣ ‹‹ዛሬ በሕይወት ከአጠገቤ ባትኖርም ውዷ እናቴ ምሥጋናዬ ከአፀደ ነፍስ ይደርሳት ዘንድ በክብር ላመሠግናት እወዳለሁ፤›› ብለዋል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ወደ ተግባር እንዲቀየር አሳሰቡ

ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቃለ መሐላ የፈጸሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በፓርላማው ያደረጉት ንግግር ይዘት፣ በአብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ዘንድ ተስፋን የጫረ እንደሆነና ወደ ተግባር እዲቀየርም ጠየቁ፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የምትደራደረው ባድመ ከተመለሰላት ብቻ እንደሆነ አስታወቀች

ኤርትራ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ያላትን የፖለቲካ ልዩነት በማጥበብ ልትደራደር የምትችለው፣ ባድመ ከተመለሰላት ብቻ እንደሆነ አስታወቀች፡፡ የኤርትራ መንግሥት ይህን ያለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከተሰየሙ በኋላ፣ ባደረጉት ንግግር ለኤርትራ መንግሥት ላቀረቡት ጥሪ በሰጠው ምላሽ ነው፡፡

‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ይገባናል ያስፈልገናል››

ሰኞ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝን በመተካት በጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሰየሙት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲና ነፃነት የሚያስፈልግ ብቻ ሳይሆን የሚገባ እንደሆነ ተናገሩ፡፡ ‹‹እኛ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ይገባናል፣ ያስፈልገናል፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ ‹‹ዴሞክራሲ ያለ ነፃነት አይታሰብም፣ ነፃነት ደግሞ ከመንግሥት ለሕዝብ የሚበረከት ስጦታ አይደለም፤›› ሲሉ ለፓርላማ አባላትና በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ለተከታተሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ

መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ሊቀመንበር በመሆን የተመረጡት ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰየሙ፡፡

በኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ሥር የዋሉት 1,108 ግለሰቦች መሆናቸው ተገለጸ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአዋጁ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በኮማንድ ፖስቱ የታሰሩት 1,108 ሰዎች መሆናቸውን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ አስታወቀ፡፡ ከታሳሪዎቹ ውስጥ 20 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አቢሲኒያ ባንክ በተከሰሱበት የፍትሐ ብሔር ክስ ላይ ሰበር ችሎት ትዕዛዝ ሰጠ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አቢሲኒያ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ያላግባብና ከሕግ ውጪ ፈጽመዋል በተባለ የመጋዘን ጨረታና ሽያጭ፣ በናይል ቡና ላኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የቀረበባቸውን የፍትሐ ብሔር ክስ ላለፉት 13 ዓመታት ሲከራከሩ ከርመው ጉዳዩ ሰበር ሰሚ ችሎት የደረሰ ቢሆንም፣ ችሎቱ ጉዳዩ በሥር ፍርድ ቤት በድጋሚ መታየት እንዳለበት ገልጾና የመከራከርያ ነጥቦችን ለይቶ በማስቀመጥ ውሳኔ ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

ከበሻሻ እስከ አራት ኪሎ

ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት እኩለ ሌሊት እየተቃረበ እያለ የተሰማው ሰበር ዜና በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ያነጋገረ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ ተተኪያቸው ማን ይሆን የሚለው በመላ አገሪቱ ዋነኛ መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተለይ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተተኪውን የግንባሩን ሊቀመንበር ለመምረጥ ስብሰባ የተቀመጠው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ለአንድ ሳምንት በመቆየቱ፣ በርካቶች በመላ ምቶችና በሴራ ንድፈ ሐሳቦች እንዲጨናነቁ አድርጓቸዋል፡፡