Skip to main content
x

እነ አቶ መላኩ ፈንታ በሁለት የክስ መዝገቦች ጥፋተኛና ነፃ ተባሉ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተከሰው ከአራት ዓመታት በላይ ሲከራከሩ የከረሙት እነ አቶ መላኩ ፈንታ፣ ዓቃቤ ሕግ ክስ ካቀረበባቸው ሦስት መዝገቦች ውስጥ በሁለቱ መዝገቦች በተወሰኑ ክሶች ጥፋተኛ ሲባሉ በተወሰኑ ክሶች ደግሞ በነፃ ተሰናበቱ፡፡

ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር በሁሉም ክልሎች ሕዝባዊ ውይይቶች ሊካሄዱ ነው

በአገሪቱ ላለፉት ሦስት ዓመታት ያህል የተከሰተውን ችግር ለመቅረፍና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ በሁሉም ክልሎች ሕዝባዊ ውይይቶች ሊካሄዱ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ በመላ አገሪቱ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና በየአካባቢው የሚፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ፣ በሁሉም ክልሎች ሕዝባዊ ውይይቶች እንዲካሄዱ ውሳኔ መተላለፉን አንድ የኢሕአዴግ የምክር ቤት አባል ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ውኃ የሚይዝበትን ቀን ለግብፅና ለሱዳን ማሳወቋ ተሰማ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ ከተጣለ ሰባተኛ ዓመት ላይ፣ ኢትዮጵያ የግድቡ ውኃ የሚይዝበትን ቀን ለግብፅና ለሱዳን ማሳወቋ ተሰማ፡፡ የውጭ ጉዳይ፣ የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊዎች ለሪፖርተር እንዳረጋገጡት፣ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ ሙሌት መቼ እንደሚጀመር ለግብፅና ለሱዳን አስታውቃለች፡፡

‹‹የሥልጣን ፍላጎት ለጥቅም ቡድኖች መፈጠርና መሻኮት የተመቸ ሆኗል›› የኢሕአዴግ ምክር ቤት

የኢሕአዴግ ብሔራዊ ምክር ቤት ዓርብ መጋቢት 21 ቀን 2010 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ አገሪቱ ወደ ቀውስ እንድትገባና አገራዊ ህልውናን የመፈታተን ጠንቅ ያጋጠመበት አንዱ ምክንያት፣ የሥልጣን ፍላጎት ለጥቅም ቡድኖች መፈጠርና መሻኮት የተመቸ ሁኔታ በመፍጠሩ እንደሆነ አስታወቀ፡፡

ኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፖሊሲ እንድታወጣ ተጠየቀ

በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም በችግሮች የተተበተበ ስለሆነ፣ ችግሮቹን ለመፍታት መንግሥት የአጠቃቀም ፖሊሲ እንዲያወጣ ተጠየቀ፡፡ ይህ ጥያቄ የቀረበው ከሁሉም የአገሪቱ ክልሎች ከተውጣጡ ወጣቶች ሐሙስ መጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በጁፒተር ሆቴል የፓናል ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የኢሕአዴግ ጠቅላላ ጉባዔ በነሐሴ እንደሚካሄድ ተገለጸ

በመጋቢት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ጠቅላላ ጉባዔ ለነሐሴ መተላለፉ ተገለጸ፡፡ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ሊቀመንበር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ይህንን የተናገሩት ዛሬ መጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ማን እንዳሰራቸው ፍርድ ቤትን ጠየቁ

በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው ሁለት የዋልድባ መነኮሳት፣ ማን እንዳሰራቸው እንዲገለጽላቸው ለፍርድ ቤት ጥያቄ  አቀረቡ፡፡ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ጥያቄውን ያቀረቡት፣ አባ ገብረ ሥላሴ ወልደ ሃይማኖትና አባ ገብረየሱስ ኪዳነ ማርያም ናቸው፡፡ መነኮሳቱ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ‹‹ማነው ያሰረን?›› ጥያቄ ላይ እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ባሰሙት አዋጅ የተከሰሱበት ጉዳይ ቀርቶ እንዲፈቱ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

ብሔራዊ መግባባት እንዴት?

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በታኅሳስ ወር 2010 ዓ.ም. ለአሥራ ሰባት ቀናት አድርጎት በነበረው ስብሰባ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲ ችግር እንደነበረበት፣ ይኼም ችግር የሕዝብን መብት በማክበርና ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ረገድ ውስንነቶች እንደነበሩ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡ መግለጫው አክሎም በአገሪቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርከት ባሉ አካባቢዎች ሰላምና መረጋጋት እየደፈረሰ፣ ሁከት የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ መምጣቱን አስታውቋል፡፡

ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን በሌላ ሥፍራ ማስፈር እንዲቆም መድረክ ጠየቀ

ለዘመናት ኑሮዋቸውን መሥርተውና ማኅበራዊ ትስስር ፈጥረው ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች ተገደው የተፈናቀሉ ዜጎችን መብት በማስከበር መንግሥት ወደ ቀዬአቸው ተመልሰው እንዲቋቋሙ ማድረግ ሲገባው፣ ተፈናቃዮቹ ወደማያውቋቸው ሩቅ አካባቢዎች ወሰዶ የማስፈር ዕቅድ አንድምታው ለአገሪቱ አንድነትና ለሕዝቡም አብሮነት አደጋ እንዳለው፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) አስታወቀ፡፡

ኢሕአዴግ ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) ሦስተኛው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ምክር ቤት ከማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ባደረገው ስብሰባ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር ዓብይ አህመድን (ዶ/ር) የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ፡፡ ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ከምሽቱ አምስት ሰዓት ከምክር ቤቱ የወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፣ ዶ/ር ዓብይ በምክር ቤቱ በተደረገ ምርጫ ተመርጠዋል፡፡