Skip to main content
x

ደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ፋብሪካ በሠራተኞች አድማ ሥራ አቆመ

ደርባ ሚድሮክ ከታኅሳስ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በሠራተኞች አድማ ምክንያት ሥራ አቆመ፡፡ አድማው ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባበት ዕለት ድረስ የቀጠለ ሲሆን፣ የደርባ ሚድሮክ ማኔጅመንትም ሆነ የኦሮሚያ ክልል አድማውን ማስቆም አለመቻላቸው ታውቋል፡፡

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያልተለመዱ ግምገማዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት በጉጉት እየተጠበቀ ነው

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለ17 ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ዝግ ስብሰባ አጠናቆ በመጨረሻ ባወጣው መግለጫና አራቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት ታኅሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችና ሌሎች ግለሰቦች እንደሚፈቱና ‹‹ማዕከላዊ›› በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማዕከል እንደሚዘጋ ማስታወቃቸውን ጨምሮ ‹‹ያልተለመዱ›› የተባሉት ግምገማዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊነት በጉጉት እየተጠበቀ ነው፡፡

በአገሪቱ የተከሰተውን ቀውስ ለማስቆም የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ

በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ቀውስ ለማስቆም፣ በርካታ የሚቀሩ ሥራዎች እንዳሉ ተጠቆመ፡፡ የአገር መከላከያ ሚኒስትርና የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ጸሐፊ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ የፌዴራልና የክልል የፀጥታ ምክር ቤቶች የተካሄደው የጋራ ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን ያሉት፡፡ ከአንድ ወር በፊት በአገሪቱ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት በፌዴራልና በክልሎች የጋራ ምክር ቤት ዕቅድ ወጥቶና መግባባት ተፈጥሮ ወደ ሥራ በመግባት በርካታ ለውጦች ቢመዘገቡም፣ ሕገወጦችን በቁጥጥር ሥር ከማዋል አኳያ የሚቀሩ ሥራዎች አሉ ብለዋል፡፡

የቻይናዊውን የምስክርነት ቃል በአግባቡ አልተረጎሙም የተባሉ አስተርጓሚ ታሰሩ

ግብርና ታክስ በማጭበርበር ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩ የቻይናዊው ባለሀብት ድርጅት በሆነው ‹‹ሲሲኤስኮም ሰርቪስ ሶሉዩሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሠራተኞችን ክስ ለማቋረጥ፣ አምስት ሚሊዮን ብር ጉቦ ተቀብለዋል ተብለው ክስ በተመሠረተባቸው ተከሳሾች ላይ በምስክርነት የቀረቡ ቻይናዊ ምስክርነት ቃልን በአግባቡ አልተረጎሙም የተባሉ አስተርጓሚ ታሰሩ፡፡

በዶ/ር መረራና በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ቀጠሮ ተሰጠ

ክሳቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የሚታየው የመድረክና የኦፌኮ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ እንዲሁም በአራተኛ ወንጀል ችሎት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ ቀጠሮ ተሰጣቸው፡፡

ዋና ኦዲተር ታክስና ግብር መርምሮ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን እንዳልተሰጠው ለፍርድ ቤት ተነገረ

ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኩባንያዎችን ሒሳብ መርምሮ የግብርና የታክስ ውሳኔዎችን ለመስጠት ሥልጣን እንደሌለውና ግብር ከፋዩ በግብር አዋጅ ላይ የተሰጡትን መብቶች እንዳይጠቀም የሚያግድ መሆኑን፣ አንድ የተፈቀደለት የሒሳብ አዋቂና የታክስ አማካሪ ኤክስፐርት ለፍርድ ቤት ተናገሩ፡፡

የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የተወሰነው በውጭ ተፅዕኖ እንዳልሆነ ተገለጸ

ኢሕአዴግ አንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትንና ሌሎች ግለሰቦችን ለመፍታት የወሰነው፣ በውጭ ተቋማትና መንግሥታት ተፅዕኖ እንዳልሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ኢሕአዴግ የወሰዳቸው ዕርምጃዎች በተፅዕኖ የመጡ አይደሉም፡፡

በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትና አመራሮች በሁለት ቀናት ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ተባለ

በምሕረትና የክስ ሂደታቸው ተቋርጦ ይፈታሉ የተባሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር እስረኞች፣ ዓርብ ታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ወይም ቅዳሜ ታኅሳስ 28 ቀን 2010 ዓ.ም. ሊፈቱ ይችላሉ ሲሉ የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ ሥራ ጀመሩ

የሕዝቤ ክብር በመነካቱ አሁን ባለሁበት ደረጃ ሥራዬን ለመቀጠል የማያስችሉኝ ሁኔታዎች ስላሉና ፍላጎቱም ስለሌለኝ በማለት ከአፈ ጉባዔነታቸው ለመነሳት ለኢሕአዴግና ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) መልቀቂያ ያስገቡት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ዛሬ ታኅሳስ 26 ቀን 2010 ዓ.ም. መደበኛ የፓርላማ አፈ ጉባዔነት ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡

በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱ ተገለጸ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞች እንደሚፈቱና ‹‹ማዕከላዊ›› በመባል የሚታወቀው የምርመራ ማዕከል እንደሚዘጋ ዛሬ አስታወቁ፡፡ አራቱ የኢሕአዴግ ብሔራዊ ድርጀቶች ሊቃነ መናብርት በጋራ በሰጡት መግለጫ እዚህ ውሳኔ ላይ መደረሱን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡