Skip to main content
x

የግብፅና የሱዳን መሪዎች በህዳሴ ግድቡ ላይ መወያየታቸው በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጥረው ሥጋት እንደሌለ ተነገረ

የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲና የሱዳን አቻቸው ኦማር ሐሰን አል በሽር በህዳሴ ግድቡ ላይ መወያየት፣ በኢትዮጵያ ላይ ሥጋት እንደማይፈጥር መንግሥት አስታወቀ፡፡

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አለው የተባለው ተከሳሽ የመከላከያ ምስክሮቹን አሰማ

ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለውና ከድርጅቱ መሪ ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) ጋር በመገናኘት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ተደርሶበታል ተብሎ ክስ የተመሠረተበት ተጠርጣሪ፣ ሦስት የመከላከያ ምስክሮቹን አሰማ፡፡

‹‹የሕገወጥ መሣሪያ ዝውውር እየተበራከተ የመጣበት ዋነኛ ምክንያት በአገር ውስጥ ያለውን የሁከትና ግርግር እቅስቃሴ በጦር መሣሪያ ለማስደገፍ ታልሞ ነው››

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንድ ወር አስቆጥሯል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሰላመ መደፍረስ ተስተውሏል፡፡ በተፈጠረው ቀውስ ሳቢያም ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዜጎች ለሞትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል፡፡ እንዲሁም በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል፡፡

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጀመረ

የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ከማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ መካሄድ ጀመረ፡፡ የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመጋቢት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ጀምሮ በዝግ ሲመክር መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ስብሰባውን ሰኞ መጋቢት 10 ቀን 2010 ዓ.ም. አጠናቋል፡፡ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ግማሽ ቀን ዕረፍት ካደረጉ በኋላ የምክር ቤቱ ስብሰባ በዝግ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ዘንድሮ መካሄድ የሚገባው የአካባቢና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ምርጫ በተመለከተ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

ዘንድሮ መካሄድ በሚገባው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮችና የአካባቢ ምርጫን በተመለከተ የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑ ታወቀ፡፡ ምርጫው መካሄድ የነበረበት በሚያዝያ ወር 2010 ዓ.ም. የነበረ ቢሆንም፣ በአገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ምርጫውን በወቅቱ ማከናወን አይቻልም ተብሏል፡፡

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት የዋልድባ ገዳም መነኮሳት ላይ ምስክርነት ለመስማት ቀጠሮ ተያዘ

በተጠረጠሩበት የሽብር ተግባር ወንጀል ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ ገዳም ሁለት መነኮሳት ላይ፣ ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግርና በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚኖረው ተፅዕኖ

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ከሚሠሩ አገሮች አንዷ ነች፡፡ በሶማሊያ የመሸገውንና ራሱን ‹‹አልሸባብ›› ብሎ የሚጠራውን ቡድን ከመመከትና ከማዳከም ባሻገር፣ በሱዳንና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ከላይ ታች ስትል ነበር፡፡

በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወጣቱ ተሳታፊ ባለመደረጉ ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወጣቱ ትውልድ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን ባለመደረጉ፣ አሁን አገሪቱን ዋጋ እያስከፈለ ነው ሲሉ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ርስቱ ይርዳ ተናገሩ፡፡ ሚኒስትሩ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት፣ ወጣቱ በአገሪቱ የለውጥ ጉዞ ባለቤትና ተጠቃሚ ባለመሆኑ በፖለቲካዊ ጉዳዮችም ንቁ ተሳታፊ እንዳይሆን እንዳደረገው አስረድተዋል በዚህ የተነሳም ዛሬ ዋጋ እያስከፈለ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

ሦስቱ አገሮች ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ሊወያዩ ነው

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ተቋርጦ በነበረው የህዳሴ ግድብ ላይ በካርቱም ውይይት ሊያደርጉ እንደሆነ ታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ሐሙስ መጋቢት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ እንደተናገሩት፣ ሦስቱ አገሮች በህዳሴ ግድቡ ላይ የሚያደርጉት ውይይት ከመጋቢት 26 እስከ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በካርቱም ይካሄዳል፡፡