Skip to main content
x

የፌዴራል መንግሥት በውክልና የወሰደውን የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለሥልጣን መልሶ አስረከበ

የፌዴራል መንግሥት በውክልና ተረክቦ ያስተዳድር የነበረውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን መልሶ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስረከበ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ረቡዕ ታኅሳስ 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ከአምስት ዓመታት በላይ ተለይቶ የቆየውን የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣንን፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክና ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሞገስ ባልቻ ተረክበዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ ለነባሩ የኢዴፓ አመራር በድጋሚ ዕውቅና መስጠቱ ተቃውሞ አስነሳ

ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ ጋር እየተደረገ ባለው ድርድር ምክንያት በኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) አመራሮች ዘንድ የተፈጠረውን አለመግባባት የመረመረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ አዲሱ አመራር የተመረጠበት መንገድ የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ያላደረገ በመሆኑ እንደማይቀበለው አስታወቀ፡፡

እስከ 15 ዓመት የሚያስቀጣ የአደገኛ ቆሻሻ ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

 

 

በዮናስ ዓብይ

የአደገኛ ኬሚካልና ቆሻሻ ወደ አገር ውስጥ አገባብ፣ አጠቃቀምና አወጋገድ ለመቆጣጠር አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡

ረቂቅ ሕጉ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል በተባለለት የቁጥጥር ዕርምጃ፣ ጥፋተኛ በሚባሉ አስገቢዎችና አምራቾች ላይ እስከ 15 ዓመት የሚደርስ እስራትና እስከ አምስት ሚሊዮን ብር የሚደርስ የገንዘብ መቀጮ በድንጋጌው ውስጥ አስፍሯል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና ዓቃቤ ሕግ ላቅርብ ባለው ተጨማሪ ማስረጃ ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

ዶ/ር መረራ ጉዲና የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ካሰማቸው የደረጃ ምስክሮች በተጨማሪ የኦዲዮ፣ የቪዲዮና የፎቶግራፍ ማስረጃዎችን እንዲያቀርብ ለፍርድ ቤት ያቀረበውን ጥያቄ በመቃወም አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገው፡፡

በእነ አቶ በቀለ ገርባ የመከላከያ ምስክሮች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ቀጠሮ ተሰጠ

በአቶ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ የተካተቱት እነ አቶ በቀለ ገርባ (አራት ተከሳሾች) በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሯቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለፍርድ ቤት በሰጡት ምላሽ ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት፣ ለታኅሳስ 27 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ በቀለ ገርባ ክስ ላይ ተጠርተው ሳይገኙ በቀሩ ምስክሮች ላይ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ተበተነ

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ አራተኛ የወንጀል ምድብ ችሎች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎች በእነ አቶ በቀለ ገርባ መዝገብ ለተከሰሱ ታሳሪዎች ለምስክርነት ተጠርተው ባልቀረቡ ምስክሮች ላይ ትዕዛዝ ያስተላልፋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ትዕዛዝ ሳይሰጥ ለሌላ ጊዜ በቀጠሮ ተበተነ፡፡

በእነ አቶ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ላይ በምስክርነት የተጠሩት የኦሮሚያ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ተለዋጭ ቀን እንዲሰጣቸው ኦሕዴድ ጠየቀ

በእነ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ ለተከሰሱ 22 ሰዎች የመከላከያ ምስክር ሆነው እንዲቀርቡ መጥሪያ የደረሳቸው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዓቢይ አህመድና (ዶ/ር) የለገዳዲ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በተጠሩበት ቀን ለምስክርነት መቅረብ ስለማይችሉ ተለዋጭ ቀን እንዲሰጣቸው የኦሕዴድ ጽሕፈት ቤት ፍርድ ቤቱን በአክብሮት በደብዳቤ ጠየቅ።

የደቡብ ሱዳን አዲሱ የተኩስ አቁም ስምምነትና የተደቀነው ሥጋት

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ የፖለቲካ ኃይሎች ወደ እርስ በርስ ጦርነት ካመሩ አራት ዓመታት አለፉ፡፡ ይህ ግጭት ቆሞ በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ሁለቱ ኃይሎች ያነገቡትን መሣሪያ በመጣል፣ ወደ ጠረጴዛ ውይይት እንዲመጡ ተደጋጋሚ ጥረት በማድረግ ተጠቃሽ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ ላይ ከግብፅ ጋር ብቻ የሁለትዮሽ ምክክር አይደረግም አለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ከግብፅ አቻቸው ሳሜህ ሹክሪ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሲወያዩ፣ ኢትዮጵያ ሱዳን ያልተካተተችበት የሁለትዮሽ ምክክር በህዳሴ ግድቡ ላይ እንደማታደርግ አስታወቁ፡፡

የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡትን ጥሪ እሳቸውና የኢሕአዴግ አመራሮች ድርጅታዊ ምላሽ እየሰጡበት ነው

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ወቅታዊ የአገሪቱ የፖለቲካ ውጥረቶችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምላሽ እስኪሰጧቸው ድረስ መደበኛ ስብሰባዎችን እንደማይሳተፋ በመግለጻቸው ምክንያት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሌሎች የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ጋር በመሆን የፓርላማ አባላቱን በድርጅታዊ መዋቅር እንዳነጋገሩ ተሰማ።