Skip to main content
x

አቶ በቀለ ገርባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማይቀርቡ ከሆነ በፖሊስ ተገደው እንዲቀርቡ እንዲታዘዝላቸው ጠየቁ

አቶ በቀለ ገርባ በመከላከያ ምስክርነት የተቆጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ፍርድ ቤት የማይቀርቡ ከሆነ፣ በፖሊስ ተገደው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው ፍርድ ቤትን ጠየቁ፡፡

የኢዴፓ አመራሮች ውዝግብ ቀጥሏል

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ብሔራዊ ምክር ቤት እሑድ ታኅሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ባካሄደው ስብሰባ አቶ አዳነ ታደሰን በፕሬዚዳንትነት መረጠ፡፡ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም የተባሉ ጉዳዮችንም ማስተካከሉንና ለቦርዱ ማስገባቱን ለሪፖርተር ቢገልጽም፣ እንደገና ተቃውሞ በመነሳቱ ውዝግቡ ቀጥሏል፡፡

በኦሮሚያና በሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚከሰት ግጭትን መቆጣጠር እንዳልተቻለ ተገለጸ

በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣው ግጭት መቆጣጠር እንዳልተቻለ ተገለጸ፡፡ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር እሑድ ታኅሳስ 15 ቀን 2010 ዓ.ም. ጅግጅጋ በሚገኘው ጽሕፈት ቤታቸው እንደተናገሩት፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች እየተከሰተ ያለውን ግጭት መቆጣጠር አልተቻለም፡፡ ከዚህ በፊት ወሰን አካባቢ ግጭት ሲከሰት በቀላሉ በአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች አማካይነት ግፋ ቢል ደግሞ በወረዳና በዞን አመራሮች ይፈታ ነበር ብለዋል፡፡

የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት አራት ኃላፊዎች ክስ እንዲሻሻል ትዕዛዝ ተሰጠ

የመንግሥትን ሥልጣን በማያመች አኳኋን በመምራት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ የቀረበባቸው የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አራት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ክስ ዓቃቤ ሕግ አሻሽሎ እንዲያቀርብ፣ ፍርድ ቤት ሰኞ ታህሳስ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

እነ አቶ በቀለ ገርባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታስረው ለምስክርነት እንዲቀርቡ ጠየቁ

በእነ አቶ በቀለ ገርባ የክስ መዝገብ የተከሰሱ ታሳሪዎች ለመከላከያ ምስክርነት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ቢጠሩም፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመቅረብ ስላልቻሉ ታስረው እንዲቀርቡ ተከሳሾቹ ጠየቁ፡፡

የሶማሌ ልዩ ኃይል ከኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች ጋር የነበረውን ግጭት አባብሷል መባሉን የክልሉ ፕሬዚዳንት አስተባበሉ

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ነዋሪዎች መካከል የነበረውን ግጭት ለማረጋጋት የሁለቱም ክልሎች የፀጥታ ኃይሎች ሚና ከፍተኛ ነበር አሉ፡፡

ስለአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ዜጎች ምን ይላሉ?

ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ጤና ስለመታወኩ ጥርጣሬ ያላቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ መጀመርያ አካባቢ የተነሱትን ሕዝባዊ ተቃውሞዎችና አመፆች መነሻን ከራሱ አርቆ በውጭ በሚገኙና ውጫዊ በሆኑ ኃይሎች ላይ ጥሎ የነበረው ገዥው ፓርቲም፣ አሁን ጤናማ ላልሆኑት አዝማሚያዎችና ችግሮች ዋነኛ መነሻ ራሱ መሆኑን፣ በውስጡ ያሉ አጥፊ ኃይሎችን በመታገል በድጋሚ ራሱን አድሶ ወደ ቀደመው ማንነቱ እንደሚመለስ እየተናገረ ነው፡፡

የአቶ አባዱላ መልቀቂያ በኢሕአዴግ ተቀባይነት አገኘ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ከአፈ ጉባዔነት ለመልቀቅ ያቀረቡት ጥያቄ በኢሕአዴግ ተቀባይነት ማግኘቱ ታወቀ፡፡ በመስከረም ወር 2010 ዓ.ም. የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ለኢሕአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝና ለኦሕዴድ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ፣ የጥያቄያቸውን ምላሽ እስካለፈው ሳምንት ድረስ ሲጠባበቁ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራትን ጥቅም ለመወሰን የተረቀቀው አዋጅ ላይ የተጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቋርጦ ተላለፈ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና አስተዳደርና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ የሚኖራትን ጥቅም ለመወሰን በተረቀቀው አዋጅ ላይ በጋራ የጠሩት የሕዝብ ውይይት ዓርብ ታኅሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማው ዋና አዳራሽ የተሰየመ ቢሆንም፣ ከኦሮሚያ ክልል በተወከሉ አመራሮች ተቃውሞ ተስተጓጉሏል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ተቋረጠ

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ዓርብ ታኅሳስ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡