ውይይት በ‹‹ለገሃነም ጸሎት›› ላይ
ሚዩዚክ ሜይዴይ ኢትዮጵያ የመጻሕፍት ንባብ እና ውይይት ክበብ ዛሬ ሚያዝያ 2 ቀን 2003 ዓ.ም. ‹‹ለገሃነም ጸሎት›› በተሰኘው የደራሲ ግዛቸው ገብረ እግዚአብሔር መጽሐፍ ላይ ውይይት ያካሒዳል፡፡
አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በሚካሔደው ውይይት መነሻ ሐሳብ የሚያቀርቡት፣ ደራሲ አቶ ገዛኸኝ ሀብቴ ሲሆኑ፣ አቶ በፍቃዱ ዓባይ መድረኩን ይመሩታል፡፡
***************
ዐውደ ርዕይ
የኢትዮጵያ ኮንቴምፖራሪ አርት ጋለሪ ያዘጋጀው የወጣት ሠዓሊ ዮናስ ሚሊዮን የሥዕል ዐውደ ርዕይ ከመጋቢት 16 ቀን ጀምሮ በመታየት ላይ ነው፡፡
***************
ፊልም፣ ዐውደ ርዕይና ውይይት
ሩሲያዊው ዩሪ ጋጋሪን ወደ ጠፈር የመጠቀበትን 50ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል ማክሰኞ ሚያዝያ 4 ቀን 2003 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡45 ጀምሮ ልዩ መርሐ ግብር እንደሚያቀርብ አስታወቀ፡፡
በመርሐ ግብሩ ስለ ጠፈር በረራ ውይይትና የዩሪ ጋጋሪን ሕይወት የሚዳስስ ፊልምና ዐውደ ርዕይ እንደሚቀርብበት ማዕከሉ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ገልጿል፡፡ መርሐ ግብሩን ማዕከሉ ከኢትዮጵያ የጠፈር ሳይንስ ማኅበር ጋር በመተባበር ያዘጋጀ መኾኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡


